የከተራ በዓል ተከበረ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 10/2011) የከተራ በዓል ዛሬ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ። ታቦታትም ከአድባራት ወተው በካህናት፣ በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው ወደየ ጥምቀተ ባህሩ ተወስደዋል፡፡ ታቦታት ወደ ማደሪያቸው ጥምቀተ ባህር ከደረሱ በኋላም አዳራቸውን በዚያው አድርገው በካህናትና ዲያቆናት ዝማሬና ሌሎች ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ተከናውነዋል። የከተራ በአሉ በደመቀና በአሰደሳች ሁኔታ እንዲከበር ወጣቶች አካባቢዎቻቸውን በማጽዳት አርአያነት ያለው ተግባር አከናውነዋል። በዓሉ ...

Read More »

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በተቀሰቀሰ ግጭት 900 ያህል ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2011) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንኮ በምርጫ ዋዜማ በተቀሰቀሰ ግጭት 900 ያህል ሰዎች በሶስት ቀናት መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ቢሮ ትላንት እንዳስታወቀው በሰሜን ምዕራብ ኮንጎ በሁለት ጎሳዎች መካከል በተፈጠረው ግጭትና በተከተለው እልቂት ሳቢያ በአካባቢው የሚደረገው ምርጫ እንዲራዘም ምክንያት ሆኗል። ባኑና ባቲንዲ በተባሉ ጎሳዎች መካከል በ4 ቀበሌዎች ውስጥ በተከተለው ግጭት 900 ያህል ሰዎች ከመገደላቸው በተጨማሪ ...

Read More »

በኢትዮጵያ 36 ሚሊየን ህጻናት በከፋ ድህነት እየተሰቃዩ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2011)በኢትዮጵያ እድሜአቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ 36 ሚሊየን ህጻናት በከፋ ድህነት እንደሚሰቃዩ ተገለጸ። በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ባለስልጣንና በዩኒሴፍ ትብብር በተዘጋጀ አንድ ጥናት ላይ እንደተመለከተው ከ41ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ህጻናት 88በመቶ የሚሆኑት በተለያዩ የድህነት መለኪያዎች አደጋ ውስጥ ናቸው። ጥናቱ በዘጠኝ የድህነት ማሳያ መስፈርቶች ውስጥ ቢያንስ በሶስቱ ኢትዮጵያውያን ህጻናት ከፍተኛ ስቃይ ውስጥ እንዳሉ የሚጠቁም እንደሆነ አመላክቷል። በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያ የወደፊት የኢኮኖሚ ብልጽግናና የማህበራዊ ...

Read More »

የአድዋን ድል ኢትዮጵያውያን በየተሰማሩበት መስክ መድገም አለባቸው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2011)የአድዋን ድል ኢትዮጵያውያን በየተሰማሩበት መስክ መድገም እንዳለባቸው አትሌት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ ገለጸች። አትሌት ደራርቱ  የአድዋን ድል ለመዘከር በተዘጋጀው የሩጫ ውድድር ላይ በባዶ እግሯ 500 ሜትር ልትሮጥ መዘጋጀቷንም አስታውቃለች። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከአድዋ ድል መታሰቢያ አንድ ቀን በኋላ በአዲስ አበባ በተዘጋጀው የ10 ኪሎሜትር ሩጫ ላይ አትሌት ደራርቱ የምትሳተፍ ሲሆን 500 ሜትሩን ያለጫማ ለመሮጥ ወስናለች። የዚሁ ውድድር አምባሳደር ተደርጋ ...

Read More »

ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡና ከሃገር እንዳይወጡ እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ቁጥር 7 ሺ ያህል ነው ተባለ

          (ኢሳት ዲሲ–ጥር 9/2011) በቀደሞው የደህንነት ሃላፊ በአቶ ጌታቸው አሰፋ የስልጣን ዘመን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡና ከሃገር እንዳይወጡ እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ቁጥር 7 ሺ ያህል እንደነበር ተገለጸ።           የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንደገለጹት እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ላይ ማጣራት እየተካሄደና ርምጃም እየተወሰደ መሆኑም ታውቋል።           በዚህም በሶስት ሺ ዜጎች ላይ የተጣለው እገዳ መነሳቱ ተመልክቷል።           ከሀገር መውጣትና ወደ ሀገር መግባት ...

Read More »

የኢራኑ ፕረስ ቲቪ ጋዜጠኛ በቁጥጥር ስር ዋለች

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2011) የኢራኑ ፕረስ ቲቪ ጋዜጠኛ በቁጥጥር ስር መዋሏን የቴሌቭዥን ጣቢያው አስታወቀ። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ርምጃውን አውግዟል። ዕሁድ ዕለት በሴንት ሉዊስ ከተማ ሴንት ሉዊስ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በቁጥጥር ስር የዋለችው የ59 ዓመቷ አሜሪካዊት ማርዚ ሐሺሚ በምን ምክንያት እንደታሰረች አልታወቀም። በትውልድ አሜሪካዊት የሆነችውና ዕምነቷን ወደ እስልምና ከመቀየሯ በፊት ሜላት ፍራንክሊን በመባል የምትታወቀው ማርዚ ሐሺሚ ለአራት መንግስታዊ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች በእንግሊዘኛ ...

Read More »

የአማራና የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ሰላም ለማምጣት እንሰራለን አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2011) የአማራና የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የሁለቱ ክልል ሕዝብ ወደ ግጭት እንዳይገባ እንደሚሰሩ በሃይማኖት አባቶችና በሃገር ሽማግሌዎች ፊት ቃል ገቡ። የአማራና የትግራይ ክልል ህዝብ አንዱ ለአንዱ ስጋት ሳይሆን አንዱ በሌላው እየኮራ ተከባብሮ የሚኖርበት ታሪክ ነበረው ሲሉ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገልጸዋል። የአማራና የትግራይ ህዝብ በመካከላቸው ችግር የለም ችግሩ ያለው እኛ ፖለቲከኞቹ ዘንድ ነው ያሉት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ...

Read More »

በምዕራብ ኦሮሚያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2011)በምዕራብ ኦሮሚያ በወለጋ የተለያዩ ዞኖች 18 ባንኮችን በመዝረፍ፣መንገድ በመዝጋትና ንብረት በማቃጠል የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። ይህ በእንዲህ እንዳለም ባለፉት 6 ወራት በሕገወጥ መንገድ አዲስ አበባ የገቡ ከ2ሺ በላይ የጦር መሳሪያዎች እንዲሁም 70 ሚሊየን ያህል የኢትዮጵያ ብርና ከመቶ ሺ ዶላር በላይ የውጭ ገንዘብ በቁጥጥር ስር መዋሉም ተመልክቷል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ በወለጋ ...

Read More »

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ወደ አፋር ሊያመሩ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2011)በአፋርና ኢሳዎች መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለማብረድ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት የሚመሩት ቡድን ወደ አካባቢው ሊያመራ መሆኑ ተገለጸ። የኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት በአቶ ሙስጠፋ ዑመር የሚመራው ቡድን ላለፉት 5 ሳምንታት በአፋርና ኢሳ መካከል ያገረሸውን ግጭት በቦታው ተገኝቶ ለመፍታት በዝግጅት ላይ ነው። በሶማሌ ክልል ሽንሌ ዞን አይሻ ከተማ የአፋር ልዩ ሃይል የወሰደውን ርምጃ በመቃውም ሰልፍ ተደርጓል። በአፋር በኩል መንግስት ግጭቱን እንዲያስቆም ...

Read More »

በአማራ ክልል የጸጥታ ችግር እየተባባሰ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 8/2011) በአማራ ክልል ያለው የጸጥታ ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመሻሻል ፈንታ እየተባባሰ በመምጣቱ የህዝቡ ደህንነት ለአደጋ መጋለጡን የክልሉ መንግስት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት በወቅታዊ የክልሉ ጉዳይ ላይ የተሰጠው መግለጫ እንዳመለከተው በተለይም በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጐንደር የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈ፣አካል ያጐደለና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጐችን ንብረትና ቤት አልባ ያደረገ ችግር እየተፈፀመ ይገኛል፡፡ እናም ከዚህ ...

Read More »