(ኢሳት ዜና–ህዳር 5/2010)በጎንደሩ ሕዝባዊ ተቃውሞ በሽብር የተከሰሱት እነ ንግስት ይርጋ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጥፋተኛ ተባሉ። እነ ንግስት ይርጋ ያቀረቡት መቃወሚያ ግምት ውስጥ ሳይገባ እንዲከላከሉ የአገዛዙ ፍርድ ቤት ወስኖባቸዋል። ፍርድቤቱ እነ ንግስት ይርጋን ጥፋተኛ ያላቸው የሰላማዊ ተቃውሞ መገለጫ በሆኑ የሰልፍ እንቅስቃሴዎች ምክንያት ነው። በእነ ንግስት ይርጋ መዝገብ በጎንደሩ ሕዝባዊ ተቃውሞ በጸረ ሽብር ሕጉ የተከሰሱት የሰላማዊ ተቃውሞ አንቀሳቃሾች እንደ ማስረጃ የቀረበባቸው ...
Read More »ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 5/2010)በህወሀት መንግስት የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የወጣው ዕቅድ የስርዓቱ የመጨረሻው ሙከራ በመሆኑ ህዝቡ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል አርበኞች ግንቦት ሰባት ጥሪ አቀረበ። ንቅናቄው ለኢሳት እንደገለጸው በስልጣን ላይ ያለው ስርዓት በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚደረጉት ሁለገብ ትግሎችን ለማፋፋም ተዘጋጅቷል። የህወሃት መንግስት በዕቅዱ ላይ በአሸባሪነት ከወነጀላቸውና ስርዓቱን በማስጨነቅ ብርቱ ፈተና እንደደቀኑ ከተጠቀሱት ድርጅቶች አንዱ አርበኞች ግንቦት ሰባት ...
Read More »በደብል ትሪ ሆቴል ላይ የተጀመረ ምርመራ የለም ተባለ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 5/2010) ከአቶ በረከት ስምኦን ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባው ደብል ትሪ ሆቴል ንብረታቸው ላይ የተጀመረ ምርመራ የለም ሲሉ አቶ ተካ አስፋው ለኢሳት ገለጹ። የሆቴሉን ግንባታ ያካሄዱት ሼህ መሀመድ አላሙዲን ባደረጉላቸው ድጋፍና ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በወሰዱት ብድር መሆኑንም ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደርኩት ገንዘብ 300 ሚሊየን ተብሎ የተጠቀሰውም ስህተት ነው ሲሉ አቶ ተካ አስፋው ተናግረዋል። ኢሳት ምንጮችን በመጥቀስ ባቀረበው ሁለት ...
Read More »በኢራንና በኢራቅ ድንበር በተከሰተው ርዕደ መሬት ከ400 በላይ ሰዎች ሞቱ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 4/2010) በኢራንና በኢራቅ ድንበር በተከሰተውና በሬክተር ስኬር 7 ነጥብ 3 በተመዘገበው ርዕደ መሬት ከ400 በላይ ሰዎች ሲሞቱ ከ7 ሺ በላይ ሰዎች ቆሰሉ። የመገናኛ ብዙሃን እያወጡት እንዳለው መረጃም የሟቾቹም ሆነ በአደጋው የተጎዱት ሰዎች ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር ይችላል። በኢራን መንግስት ስር የሚተዳደረው ፕሬስ ቲቪ እንደዘገበውና እስከ ቱርክና ፓኪስታን ድረስ ተሰምቷል ከተባለው ርዕደ መሬት በኋላ 145 የሚሆኑና መሬትን ከሚያናውጠው አደጋ ...
Read More »በአለም ላይ እጅግ በጣም ጨካኝ የሚባል የፖሊስ ሃይል ከሚገኝባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት ተባለ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 4/2010) በአለም ላይ እጅግ በጣም ጨካኝ የሚባል የፖሊስ ሃይል ከሚገኝባቸው ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን አንድ አለም አቀፍ ጥናት አመለከተ። በጥናቱ ናይጄሪያ በአለም የመጨረሻዋ ሆና ተመዝግባለች። የፖሊስ ሳይንስ ማህበር ከኢኮኖሚና ሰላም ተቋም ጋር በጋራ ይፋ ባደረጉት የጸጥታና ፖሊስ ደረጃ ኢትዮጵያ ከ127 ሀገራት ከስር 115ኛ ሆና ተመዝግባለች። የፖሊስ ብቃትን፣ አሰራሩን እንዲሁም ሕጋዊነቱንና ውጤቱን በመገምገምና በመተንተን ጥናቱን ይፋ የሚያደርገው የፖሊስ ሳይንስ ...
Read More »ኮከብ የሌበትን የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍ አድርጎ የሰቀለው ወጣት ታሰረ
(ኢሳት ዜና–ህዳር 4/2010)ኮከብ የሌበትን የኢትዮጵያ ባንዲራ በአዲስ አበባ ስታዲየም የመብራት ማማ ላይ ከፍ አድርጎ የሰቀለው ወጣት በፖሊስ ከታሰረ በኋላ አለመለቀቁ ተነገረ። ባንዲራውን ሲያውለበልብ ያረፈደው ወጣት በፖሊስና በእሳት አደጋ ሰራተኞች በክሬን አማካኝነት ከማማው ላይ እንዲወርድ ከተደረገ በኋላ ታስሯል። በሌላ ዜና በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተሰቀለ ኮከብ ያለበትን ባንዲራ ለማውረድ የሞከሩና ግቢውን ጥሰው በመግባታቸው የታሰሩት የዲሲ ግብረ ሃይል ሁለት አባላትም ከጥያቄ በኋላ ከእስር ...
Read More »በመቱ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እስካሁን አለመረጋጋታቸው ተነገረ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 4/2010)በመቱ ዩኒቨርስቲ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ተማሪዎች እስካሁን አለመረጋጋታቸው ተነገረ። በተማሪዎችና በአስተዳደሩ እንዲሁም እርስ በርስ የተከሰተው ግጭት ከፍተኛ ስጋት በመፍጠሩ ከግቢው የወጡ ተማሪዎች እስካሁን አልተመለሱም። የኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ከዩኒቨርስቲው አመራሮች ጋር ሁኔታውን ለማረጋጋት ቢሞክሩም የኦሮሚያ፣የአማራና የትግራይ ተማሪዎች በስጋት ምክንያት ግቢውን ለቀው ወጥተዋል። በኦሮሚያ ነገሌ ቦረናና በጅጅጋ ድንበር አካባቢም ግጭቱ ማገርሸቱ ተነግሯል። በመቱ ዩኒቨርስቲ ለግጭት ...
Read More »በሀገሪቱ ለተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ የግብጽና የኤርትራ መንግስትን ተጠያቂ ተደረጉ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 4/2010) የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ለተከሰተው ሁከትና ብጥብጥ የግብጽና የኤርትራ መንግስትን ተጠያቂ አደረገ። በቅርቡ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ በነበረው ግጭት የጅምላ ጭፍጨፋ መፈጸሙን መንግስት ገልጿል። “ወቅታዊ የሀገራችንን ሁኔታ ትንታኔ መሰረት ያደረገ እቅድ” በሚል ርዕስ በጥቅምት 2010 የወጣውና ለጸጥታና ደህንነት ምክር ቤት የቀረበው ሪፖርት የሀገሪቷን የጸጥታ ሁኔታ ይገመግማል። አዲስ ስታንዳርድ በድረገጹ “ሾልኮ የወጣ” በሚል ባቀረበው ባለ 26 ገጽ ሪፖርት ...
Read More »የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ እንደገና ማገርሸቱ ተሰማ
(ኢሳት ዜና–ህዳር 1/2010)የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ እንደገና ማገርሸቱ ተሰማ። ቀውሱ እንደገና ያገረሸው ባለፈው ቅዳሜ የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣኔን ለቅቄያለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ነው። በኢራን ይደገፋሉ የሚባሉት ሁቲዎች ባለፈው ቅዳሜ ወደ ሳውዲ ያስወነጨፉት የረጅም ርቀት ሚሳኤል ጉዳይም ሌላኛው የውጥረቱ ምክንያት ሆኗል። የሳውዲ ዜግነትን ደርበው የያዙት የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳአድ ሐሪሪ ባለፈው ቅዳሜ ከሳውዲ ሪያድ ሆነው የግድያ ሙከራ ሊደረግብኝ እየተጠነሰሰ ነው በሚል ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ...
Read More »የግራዚያኒ ሀውልት እንዲፈርስ ውሳኔ ተሰጠ
(ኢሳት ዜና–ሕዳር 1/2010)የጣሊያን ፍርድ ቤት ከ5 ዓመት በፊት የተገነባውን የግራዚያኒ ሀውልት እንዲፈርስ ውሳኔ ሰጠ። በላዚዮ ክፍለ ግዛት አፊሌ ከተማ የፋሺስቱ ሮዶልፍ ግራዚያኒ መታሰቢያ ሀውልትን በገነቡት የከተማዋ አመራሮች ላይ የእስርና የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉምም ታወቀ። ዓለም ዓቀፍ ህብረት ለፍትህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ለኢሳት እንዳስታወቀው ይህ የጣሊያን ፍርድ ቤት ውሳኔ ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ድል ነው። ሀውልቱን የገነቡትና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለማክበር ክስ የተመሰረተባቸው የአፊሌ ...
Read More »