በሃረር የቆሰሉት ሰዎች ቁጥር 9 ደረሰ (ኢሳት ዜና ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓ/ም) በሃረር ከተማ ሃኪም ወረዳ ለኢንቨስተር የተሰጠውን መሬት አርሶአደሮች አናሳጥርም በማለታቸው 9 ሰዎች በልዩ ሃይል አባላት በተተኮሰ ጥይት ቆስለዋል። ህዝቡ ተቃውሞውን በማሰማቱ ቦታው እንዳይታጠር አስደርጓል። በተቃውሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት እህት ያሰራቸው ፎቅ ቤት በድንጋይ ተመቷል።። በአብዛኛው የኦሮሞ ተወላጆች የሚኖሩባቸው ሶፊ ፣ ድሬ ጠያራና የረር ወረዳዎች የሃረሪ ክልል መብታቸውን ሊያስከብርላቸው ...
Read More »የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ተመሰረተ
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ተመሰረተ (ኢሳት ዜና ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓ/ም) በርካታ የክልሉ ተወላጆች በተገኙበት በባህርዳር ከተማ ሙሉአለም አዳራሽ በደመቀ ስነስርዓት የተመሰረተው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (ኢብን) የአማራን ህዝብ “ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥ እና በተለያዩ አካባቢዎች የክልሉ ህዝብ ላይ እየደረሱ ያሉ ጥቃቶችን የመከላከል ዓላማ ይዞ “ መነሳቱን አሳውቋል። የፓርቲው ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ አማራው ሌሎች ወገኖችን በማስተባበር የአገሪቱን ነጻነት ማስከበሩን ...
Read More »በርካታ ኢትዮጵያውያን ዛሬም በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው
በርካታ ኢትዮጵያውያን ዛሬም በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓ/ም) ዶ/ር አብይ ጠ/ሚኒስትር ሆነው ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዷለም አራጌ፣ ጄ/ል ተፈራ ማሞን፣ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሌሎችም በርካታ የህሊና እስረኞች የተፈቱ ቢሆንም፣ አሁንም ቁጥራቸው ቀላል የማይባል እስረኞች በእስር ቤት እየተሰቃዩ ነው። ዛሬም ፍትህ ተነፍጓቸው በእስር ላይ ከሚገኙት መካከል ላለፉት ...
Read More »ጣሊያን ስደተኞችን አገደች
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 4/2010) ጣሊያን በባህር ድንበሯ ተሻግረው ሊገቡ የነበሩ ስደተኞችን አገደች። አዲሱ የጣሊያን የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር እገዳውን ያስተላለፉት በነፍስ አድን ሰራተኞች ከባሕር ላይ ሕይወታቸው ተርፎ ወደ ጣሊያን ሊገቡ የነበሩ 629 ስደተኞችን ነው። ከሊቢያ አቅራቢያ ከተለያዩ ጀልባዎች በነብስ አድን ሰራተኞች ድጋፍ ከአደጋ የተረፉትን 629 ስደተኞች ነው የጣሊያን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደማይቀበል ያስታወቀው። ስደተኞቹ ከ6 የተለያዩ ጀልባዎች በጀርመን የአደጋ ጊዜ ...
Read More »በሰጠመችው ጀልባ የሞቱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 60 ደረሰ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 4/2010) የመን ከመድረሷ በፊት ባለፈው ሃሙስ በሰጠመችው ጀልባ የሞቱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 60 መድረሱ ተገለጸ። አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም እንዳስታወቀው በየዕለቱ በነፍስ አድን ሰራተኞች ፍለጋ ተጨማሪ አስከሬኖች እየተገኙ ነው። 100 ኢትዮጵያውያንን አሳፍራ ባለፈው ረቡዕ ከቦሳሶ የተነሳችው ጀልባ ከመዳረሻዋ የመን የወደብ ዳርቻ ከመድረሷ በፊት የመስጠም አደጋ እንደደረሰባት መዘገቡ ይታወሳል። በወቅቱ የ46 ኢትዮጵያውያን አስከሬን መገኘቱ የተገለጸ ሲሆን በነፍስ ...
Read More »በኢትዮጵያ የገንዘብ እጥረት የኢኮኖሚ ቀውስ እያስከተለ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 4 /2010)የገንዘብ እጥረት ቀውስ የኢኮኖሚ ቀውስ እያስከተለ መሆኑን የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ገለጸ። የ2011 በጀትም 59 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንዳለበት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም ተከስተ ገልጸዋል። የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የገንዘብ እጥረት ቀውስ እንደገጠመው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ገልጿል። እጥረቱ በፍጥነት መፍትሔ ካልተገኘለት ኢኮኖሚውን በመጉዳት ማህበራዊ ችግር ሊፈጥር እንደሚችልም ነው የተገለጸው፡፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትሩ ዶር ...
Read More »ኮሎኔል አበበ ገረሱ አዲስ አበባ ገቡ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 4/2010)በምርጫ 1997 በሕዝብ ላይ የደረሰውን ግድያ በመቃወምና የሕዝብ ድምጽ መሰረቁን በማውገዝ ሰራዊታቸውን ይዘው ኤርትራ ከገቡት ከፍተኛ መኮንኖች አንዱ ኮሎኔል አበበ ገረሱ አዲስ አበባ ገቡ። ስርአቱን አውግዘው በተመሳሳይ ከሃገር የወጡት የኦሕዴድ መስራች አቶ ዮናታን ዲቢሳም በተመሳሳይ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተሰምቷል። ስርአቱን ተቃውመው ከሃገር የወጡትና በትግል ላይ የቆዩት ኮለኔል አበበ ገረሱና አቶ ዮናታን ዲቢሳ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ...
Read More »ስር ነቀል ለውጥ የማያመጣ ከሆነ ጭብጨባው ወደ ጩኽት ሊቀየር ይችላል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 4/2010)የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጉዞ ስር ነቀል ለውጥ የማያመጣ ከሆነ ጭብጨባው ወደ ጩኽት ሊቀየር እንደሚችል ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ገለጸ። በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ለውጥ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ቢያንስ የሞራል ድጋፍ መስጠት እንደሚገባም አመልክቷል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ይህንን የተናገረው ለእሱና ለባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደ የምስጋና ስነ-ስርአት ላይ ነው። ስድስት አመታት ከመንፈቅ በወህኒ ያሳለፈው ጋዜጠኛ እስክንድር በየካቲት ...
Read More »በቡኖ በደሌ 12 የአማራ ተወላጆች በፖሊስ ተደብድበው ታሰሩ
(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 4/2010)በኢሉባቡር ቡኖ በደሌ ባለፈው ቅዳሜ 12 የአማራ ተወላጆች በፖሊስ ተደብድበው መታሰራቸው ተገለጸ። በደዴሳ ወረዳ ሰቦ ቀበሌ የሚኖሩት የአማራ ተወላጆች ድብደባ የተፈጸመባቸው በማሳቸው ላይ ምርት እየሰበሰቡ ባሉበት ወቅት መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ባለፈው ሳምንት በቄለም ወለጋ በአማራ ተወላጆች ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ተፈጽሞ በርካታ ሰዎች መፈናቀላቸውን በመጥቀስ አምነስቲ ኢንተርናሽናል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በቡኖ በደሌ የታሰሩት የአማራ ተወላጆች እንዲፈቱም በመጠየቅ ላይ ...
Read More »የኢሮብ ህዝብ በባድመ ውሳኔ ዙሪያ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ
የኢሮብ ህዝብ በባድመ ውሳኔ ዙሪያ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ (ኢሳት ዜና ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመሩት መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበል ማስታወቁን ተከትሎ ውሳኔው የኢሮብን ህዝብ ከሁለት የሚከፍል ነው በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል። ዛሬ በርካታ የኢሮብ ወረዳ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ውሳኔውን እንደማይቀበለው ገልጿል። በተቃውሞው ዙሪያ የኦሮብ ተወላጅ የሆነ ግለሰብ ስቱዲዮ ጋብዘናል። የኤርትራ መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን ...
Read More »