የኢሮብ ህዝብ በባድመ ውሳኔ ዙሪያ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ

የኢሮብ ህዝብ በባድመ ውሳኔ ዙሪያ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 1 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመሩት መንግስት የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበል ማስታወቁን ተከትሎ ውሳኔው የኢሮብን ህዝብ ከሁለት የሚከፍል ነው በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል። ዛሬ በርካታ የኢሮብ ወረዳ ህዝብ ወደ አደባባይ በመውጣት ውሳኔውን እንደማይቀበለው ገልጿል።
በተቃውሞው ዙሪያ የኦሮብ ተወላጅ የሆነ ግለሰብ ስቱዲዮ ጋብዘናል።
የኤርትራ መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን የሰጠው ይፋዊ መግለጫ የለም። ህወሃት ውሳኔውን እንደተቀበለውና ድርድሩ በድንበር ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ጉዳዮች ላይ ይሆናል ብሎአል።