ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወደብ አገልግሎትና በልዩ ልዩ ዘርፎች ስምምነት ተፈራረሙ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 2/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኤርትራ ለሁለት ቀናት ባደረጉት ጉብኝት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደገና መጀመሩን ጨምሮ በወደብ አገልግሎትና በልዩ ልዩ ዘርፎች ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ጋር ስምምነት ተፈራረሙ። የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ በጉዳዩ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ለመነጋገር ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል። ከ20 አመታት በኋላ ሁለቱ ሃገራት በመሪዎች ደረጃ ያደረጉት ግንኙነትና የነበረው ደማቅ አቀባበል የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ...

Read More »

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ጦርነት ማብቃቱን በይፋ ከማወጅም አልፈው በበርካታ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነቶችን ተፈራረሙ።

ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ጦርነት ማብቃቱን በይፋ ከማወጅም አልፈው በበርካታ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነቶችን ተፈራረሙ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 2 ቀን 2010 ዓ/ም)ነገሮች ሁሉ ህልም እንጂ እውን አይመስሉም።እየሆነ ባለው ተዓምር ብዙዎች እጃቸውን አፋቸው ላይ ጭነዋል።በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን መስዋዕት የሆኑበት ፣ በሚሳይል እና በላውንቸር ሊቋች ያልቻለው እና ለ20 ዓመት ተበግሮ የዘለቀው የጥላቻ ግንብ “ድንበራችን ፍቅር ...

Read More »

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለዶ/ር አብይ አህመድ የሚደረጉ የድጋፍ ሰልፎች ቀጥለዋል

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ለዶ/ር አብይ አህመድ የሚደረጉ የድጋፍ ሰልፎች ቀጥለዋል ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 2 ቀን 2010 ዓ/ም)ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ እንዲሁም ዛሬ ሰኞ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር እየወሰደ ያለውን እርምጃ በማድነቅ ድጋፋቸውን ገልጸዋል። በአርባምንጭ ከተማ ዛሬ በተደረገው የድጋፍ ስልፍ የከተማ ነዋሪዎች አርማ የሌለውን ረጅም ሰንደቅ አለማ በማሰራትና የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ድጋፋቸውን ሲገልጹ ውለዋል። በክብር ...

Read More »

ወደ አማራ ክልል ሊገቡ የነበሩ 25 ኤፍ አንድ ቦንቦች ተያዙ።

ወደ አማራ ክልል ሊገቡ የነበሩ 25 ኤፍ አንድ ቦንቦች ተያዙ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 2 ቀን 2010 ዓ/ም)ቦንቡን በመያዝ ጥቃት ለመፈጸም የተንቀሳቀሱት ግለሰቦች ባለፈው ዓመት ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተመረቁ መሆናቸውን የተናገሩ ሲሆን ፤ወጣቶቹ ከተመረቁ በኋላ በስውር በመመልመል አጭር ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። ሰኔ 26 ቀን 2010 ዓም ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ደጀን ከተማ በመሄድ በጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ዐብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በሚሳተፉ ...

Read More »

ሃብሊ አዲስ መሪዎችን መረጠ

ሃብሊ አዲስ መሪዎችን መረጠ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 2 ቀን 2010 ዓ/ም)የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ሊቀመንበሩ አቶ ሙራድ አብዱልሃዲድ ያጋጠማቸውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የድርጅት ሊቀመንበርነት ቦታቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸውን ተከትሎ አርብ ሰኔ29 ቀን 2010 ዓም ባደረገው የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አቶ ኦድሪን በድሪን ሊቀመንበር ፣ አቶ ነዲል ማሃዲን ደግሞ ምክትል ሊ/መንበር አድርጎ መርጧል። አዲሱ ሊቀመንበር አቶ ኦድሪን በድሪ ቀጣዩ የክልሉ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ ተብሎ ...

Read More »

መሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ የሚታየው የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ንረት በየአካባቢው የሕዝብ ቅሬታዎችን እየፈጠረ ነው፡፡

መሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ የሚታየው የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ንረት በየአካባቢው የሕዝብ ቅሬታዎችን እየፈጠረ ነው፡፡ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 2 ቀን 2010 ዓ/ም) የጤፍ ዋጋ መጨመር፣ የስኳር እና ዘይ አቅርቦት እጥረት መከሰት እና ኮታ ማነስ ዋና ዋና ችግሮች ሆነው ቀጥለዋል፡፡ የአማራ ክልል ንግድ ቢሮ ባወጣው የገበያ ዋጋ ግምገማ በክልሉ በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር፣ በደሴ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተማ፣ በደቡብ ወሎ ...

Read More »

ናዋዝ ሸሪፍ የ10 አመት የእስር ትዕዛዝ ተላለፈባቸው

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010) የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሸሪፍ የ10 አመት የእስር ትዕዛዝ ተላለፈባቸው። ፍርድ ቤቱ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ ውሳኔውን ያሳለፈው ስልጣናቸውን አላግባብ በመጠቀም የሃገሪቱን ገንዘብ መዝብረዋል በሚል ነው። ተዘረፈ በተባለው ገንዘብም በለንደን አራት የቅንጦት መኖሪያ ቤቶችን መግዛታቸውንና ከህዝብ በዘረፉት ገንዘብ የቅንጦት ኑሮ  እየመሩ ነው በሚል ፍርድ ቤቱ ማስረጃውን አቅርቧል። ፍርድ ቤቱ በወንጀሉ ተባባሪ ናት ባላት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ...

Read More »

የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ ስልጣናቸውን ለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010)በሃዋሳ ከተማ ከተነሳው ግጭት ጋር በተያያዘ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀቁ። የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሉሉ አዱላና የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴድሮስ ገቢባ በከተማዋ ተከስቶ ከነበረው የጸጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ ከትላንት ሰኔ 28/2010 ጀምሮ በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀዋል። ሁለቱ ባለስልጣናት በከተማዋ በተከሰተው ግጭት ለደረሰው ጉዳት ሃላፊነት መውሰዳቸውም ተመልክቷል።    

Read More »

ፈላጭ ቆራጭ አመራር እያደገ መጥቷል ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010) በኢትዮጵያ የኢሕአዴግ መርህ እየተተወና ፈላጭ ቆራጭ አመራር እያደገ መጥቷል ሲሉ የሕወሃት አመራሮች ገለጹ። የሕወሃት ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጺዮን ገብረሚካኤልና የድርጅቱ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አለም ገብረዋህድ ከክልሉ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር ተወያይተዋል። በዚሁ ውይይትም ኢትዮጵያ ባለፉት 17 አመታት ካስመዘገበችው እድገት ውጪ አዲስ ለውጥ የለም ሲሉ ገልጸዋል። እኛ የቀን ጅቦች አይደለንም በኢሕአዴግ ውስጥ ግን በአራቱም ...

Read More »

በሶማሌ ክልል እስረኞችን ማሸሽ ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010)የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ የሂዩማን ራይትስ ዎች ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ እስረኞችን በማሸሽ ላይ መሆኑ ተገለጸ። ከፍተኛ ሰቆቃ የሚፈጸምበት ጄይል ኦጋዴን ዛሬ ከ20 አዳዲስ እስረኞች በቀር በሺዎች የሚቆጠሩ ግፍና ስቃይ የደረሰባቸው እስረኞች በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች ወደሚገኙ እስርቤቶች እንዲሸሹ መደረጋቸውን የኢሳት የመረጃ ምንጮች አጋልጠዋል። ጄል ኦጋዴንን ጨምሮ በሶማሌ ክልል ለተፈጸሙ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሆነው ...

Read More »