የሶማሌው ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌ፣ ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጣባቸውን መግለጫ እንዲያስተባብል ያስገደዱትን በቅርበ የተፈታ እስረኛ “በበቂ ሁኔታ አላስተባበለም”በማለት ዳግም እንዲታሰር አዘዙ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 3 ቀን 2010 ዓ/ም ) የእስርት ዕዛዝ የወጣበት ሙሀመድ አብዱላሂ ጉዴ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአካባቢው ተሰውሯል።

የሶማሌው ክልል ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌ፣ ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጣባቸውን መግለጫ እንዲያስተባብል ያስገደዱትን በቅርበ የተፈታ እስረኛ “በበቂ ሁኔታ አላስተባበለም”በማለት ዳግም እንዲታሰር አዘዙ። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 3 ቀን 2010 ዓ/ም ) የእስርት ዕዛዝ የወጣበት ሙሀመድ አብዱላሂ ጉዴ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአካባቢው ተሰውሯል። ዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች ከጥቂት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በአቶ አብዲ ኢሌና ...

Read More »

በአማራ ክልል ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቅሬታ እየተሰማ ነው፡፡

በአማራ ክልል ከመሬት አስተዳደር ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቅሬታ እየተሰማ ነው፡፡ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 3 ቀን 2010 ዓ/ም ) በአማራ ክልል ከመሬት ልማት እና አስተዳደር ጋር በተያየዘ ከፍተኛ ቅሬታ እየታየ መሆኑን የክልሉ ቅሬታ ሰሚ አቶ ሰይድ ሁሴን አስታወቀዋል፡፡ አቶ ሰይድ በስድስት ወር ሪፖርታቸው አመቱን ሁሉ የቅሬታ ምንጭ ሁኖ ያለው መሬት ነው ብለዋል፡፡ አመቱን ሁሉ ከይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አሰጣጥ፣ ካሳ አለመሰጠት ...

Read More »

የፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ቡድን ኤርትራ ለመሄድ ጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 3/2010) የፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ቡድን ከአስመራ አቻው ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ጠየቀ። ለኤርትራ እግር ኳስ ፌደሬሽን በተላከ ደብዳቤ ላይ እንደተገለጸው የተጀመረውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር በሁለቱ ከተሞች የእግር ኳስ ክለቦች መሀል በአስመራ የወዳጅነት ግጥሚያ ለማደረግ ተፈልጓል። የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ያስተላለፈው ውሳኔ በከተማው ከንቲባ በአቶ ተቀባ ተባባል ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ የወዳጅነት የእግር ...

Read More »

የዋሽንግተን ዲሲው ኮሚቴ አወቃቀር ላይ ማስተካከያ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 3/2010) ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አሕመድን በዋሽንግተን ዲሲ ለመቀበል በተቋቋመው አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት አወቃቀር ላይ ማስተካከያ መደረጉ ተገለጸ። በኮሚቴው አወቃቀር ላይ ማስተካካያ የተደረገው በአሰራሩ ላይ ከአባላቱ እና ከልዩ ልዩ ወገኖች የተነሳውን ቅሬታ መሰረት በማድረግ መሆኑን አስተባባሪዎች ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ስራውን ከጀመረ አንድ ወር በሆነው የዋሽንግተን ዲሲ አስተባባሪ ኮሚቴ ውስጥ በፊት ያልነበሩና የጠቅላይ ሚንስትሩን የለውጥ እንቅስቃሴ የሚቃወሙ ሰዎች እንዲገቡ ...

Read More »

በድርጅቶች ላይ የተጣለው ፍረጃ ማነሳቱን ሰማያዊ ፓርቲ አደነቀ

(ኢሳት ዲሲ—ሐምሌ 3 /2018)የኢትዮጵያ ፓርላማ በአርበኞች ግንቦት 7 ፣በኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና በኦብነግ ላይ የጣለውን ፍረጃ ማንሳቱን ሰማያዊ ፓርቲ አደነቀ። ፓርቲው ህብረ ብሄራዊ ከሆነው  ድርጅት  አርበኞች ግንቦት 7 ጋር እስከ ውህደት አብሮ ለመስራት ያለውንም ፍላጎት ገልጿል።አፋኝ የሆኑት የሃገሪቱ ህጎች  እንዲሻሩም ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን አቅርቧል። “ሁላችን ለአንዳችን አንዳችን ለሁላችን ስናስብ የማንወጣው። ተራራ የማንሻገረው ገደል አይኖርም ! “  በሚል ርዕስ ሰማያዊ ፓርቲ ...

Read More »

የህወሃት አባላት ያልሆኑ የጦር ጀነራሎች በአስከፊ ኑሮ ውስጥ ናቸው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 3/2010) በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ማንነትን መሰረት ባደረገ የማግለል ርምጃ  የህዉሐት አባላት ያልሆኑ የጦር ጀነራሎች ከሰራዊቱ ያለጡረታ እየተገፉ በአስከፊ ኑሮ ውስጥ ማለፋቸውን አንድ የጦር ጄኔራል ለኢሳት ገለጹ። በተለያዩ የሰራዊቱ የግምገማ መድረኮች የሕወሃት የበላይነትን በተመለከተ የሚነሱ አስተያየቶች ዋጋ ሲያስከፍሉ መቆየታቸውንም  አስታውሰዋል። በሃገር መከላከያ ሚኒስቴር በመረጃ ዋና መምሪያ የትንተና እና ፕሮዳክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ብርጋዴር ጀኔራል መላኩ ሽፈራው ከኢሳት ...

Read More »

በጃፓን በጎርፍ አደጋ ቢያንስ መቶ ያህል ሰዎች ሞቱ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 2/2010) በጃፓን ምዕራባዊ ክፍል የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ቢያንስ መቶ ያህል ሰዎች መሞታቸው ታወቀ። ከተለመደው በሶስት እጥፍ በጨመረ መልኩ ጥሏል የተባለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍና የመሬት መደርመስ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች የገቡበት አልታወቀም ተብሏል። ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅም የተባለው ይህ ዝናብ ባስከተለው አደጋም አካባቢው ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ውጪ መሆኑ ታውቋል። በአካባቢው ያለው ወንዝ በድንገት ሊገነፍል ይችላል በሚልም 2 ሚሊየን የሚሆኑ ...

Read More »

ከ120 በላይ አዳዲስ ዳኞች ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 2/2010) የፍትህ ስርአቱን ለማሻሻል ያስችላሉ የተባሉ ከ120 በላይ አዳዲስ ዳኞች ተሾሙ። የዳኞቹ ሹመት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ውድቀት ከደረሰባቸው ተቋማት አንዱ የሆነውንና የስርአቱ የፖለቲካ መሳሪያ ነው የሚባለውን የፍትህ ስርአት ለማሻሻል ነው ተብሏል። በሳምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ ፓርላማው ሹመታቸውን ካጸደቀላቸው ዳኞች ውስጥ ከ40 የሚበልጡት ለፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሆነም ታውቋል። ፓርላማው ለእረፍት ከመውጣቱ በፊት በሳምንቱ መጨረሻ ሹመታቸውን ያጸደቀላቸው 123 ዳኞች ናቸው። ከነዚህ ...

Read More »

የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕገ መንግስቱ እየተጣሰ ነው አለ

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 2/2010) የትግራይ ክልል ምክር ቤት ሕገ መንግስቱ እየተጣሰ ነው በሚል መግለጫ አወጣ። የክልሉ ምክር ቤት ሰሞኑን መቀሌ ያካሄደውን ስብሰባ ተከትሎ ባወጣው መግለጫ የፌደራሉ መንግስት ባንዲራ እየተቀደደና እየተቃጠለ ነው በማለት አውግዟል። ከወሰን ጥያቄ ጋር በተያያዘ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ያለው የትግራይ ክልላዊ መንግስት ከኤርትራ ጋር የተጀመረው ንግግር ህዝብን በሚያሳትፍ መንገድ እንዲቋጭም ጥሪ አቅርቧል። በየክልሉ በሚካሄዱ ትዕይንተ ሕዝቦች ...

Read More »

የድጋፍ ሰልፎቹ እንደቀጠሉ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 2/2010)በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች የድጋፍ ሰልፎች ተካሄዱ። አርባምንጭ ከ1ሺህ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ለእይታ የበቃበት ደማቅ ሰልፍ መካሄዱ ታውቋል። በእንጅባራ፣ ዳንግላ፣ ዳባት፣ አብርሃጅራና ሶረቃ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር የተመዘገበባቸው የድጋፍ ሰልፎች መደረጋቸውን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በራያ ወሎና በሰሜን ሸዋ አጣዬ  በተደረጉት ሰልፎች ታጣቂዎች ህዝቡ ላይ መተኮሳቸው ታውቋ። የሰው ህይወት መጥፋቱንም ለማወቅ ተችሏል። በየከተሞቹ በተደረጉት ሰልፎች ህወሃትን የሚያወግዙ ...

Read More »