የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ ስልጣናቸውን ለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 29/2010)በሃዋሳ ከተማ ከተነሳው ግጭት ጋር በተያያዘ የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀቁ።

የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አክሉሉ አዱላና የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴድሮስ ገቢባ በከተማዋ ተከስቶ ከነበረው የጸጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ ከትላንት ሰኔ 28/2010 ጀምሮ በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀዋል።

ሁለቱ ባለስልጣናት በከተማዋ በተከሰተው ግጭት ለደረሰው ጉዳት ሃላፊነት መውሰዳቸውም ተመልክቷል።