መሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ የሚታየው የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ንረት በየአካባቢው የሕዝብ ቅሬታዎችን እየፈጠረ ነው፡፡

መሠረታዊ ፍጆታዎች ላይ የሚታየው የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ንረት በየአካባቢው የሕዝብ ቅሬታዎችን እየፈጠረ ነው፡፡
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 2 ቀን 2010 ዓ/ም) የጤፍ ዋጋ መጨመር፣ የስኳር እና ዘይ አቅርቦት እጥረት መከሰት እና ኮታ ማነስ ዋና ዋና ችግሮች ሆነው ቀጥለዋል፡፡
የአማራ ክልል ንግድ ቢሮ ባወጣው የገበያ ዋጋ ግምገማ በክልሉ በሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር፣ በደሴ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተማ፣ በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር ለገሂዳ፣ አርጐባ፣ ቦረና እና ተሁለደሬ ወረዳዎች፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ሞጣ ከተማ አስተዳደር እና ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳዎች፣ የምዕራብ ጐጃም ዞን አስተዳደር ሜጫና ይልማና ዴንሳ ወረዳዎች እና በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር ሁሉም ወረዳዎች በጤፍ እና በሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ በመከሰቱ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ እያስነሳ ነው፡፡