ህዳር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የካርታ ስራዉ የመሬት ይዞታ ድንበሮችን፤ ባለቤትነትና ምዝገባን የሚያካትት ሲሆን ጨረታዉን የሚያሸንፈዉ ድርጅት 23 ከተሞችን፤ የኦሮሚያ፡ የአማራ፤ የትግራይና የደቡብ ክልሎችን ጨምሮ እንዲሁም የቻርተር ከተማ ሆነዉ የተመዘገቡትን የአዲስ አበባንና የድሬዳዋ ከተሞችን በሚሸነሽን መልክ የአየር ፎቶግራፍ ያነሳል። ከአንድ አመት ጥቂት ቀደም ብሎ የአዲስ አበባ ከተማ ተመሳሳይ ስራ 50 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ገንዘብ በሚሆን ወጪ በአንድ የጀርመን የአየር የቅያስ ...
Read More »የመምህር የኔሰው ገብሬ ሞትን ተከትሎ አንድ ወጣት በአካባቢው ባለስልጣናት ፊት እራሱን በገመድ አንቆ ለመግደል ሞከረ
ህዳር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ህዳር 12 ቀን 2011 ዓም የዳውሮ ዋና ከተማ በሆነው ተርጫ ከተማ የሚኖረው ወጣት እራሱን በገመድ አንቆ ለመግደል የሞከረው፣ የአካባቢው ባለስልጣናት በፈጠሩበት የአስተዳደር በደል ነው። ለአመቻች መምህርነት ስራ ለመቀጠር አመልክቶ ምልመላውን አልፎ የነበረው ወጣት፣ ወደ ስልጠና ለመሄድ ሲዘጋጅ የወረዳው ባለስልጣናት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ወደ ተጠባባቂነት ቦታ ማውረዳቸውን የአካባቢው ሰዎች ተናግረዋል። በድህነት ይኖር የነበረው ወጣት፣ “ለምን ...
Read More »በእነ አቶ አንዱአለም አራጌ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲካኞች እና ጋዜጠኞች በድጋሜ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ህዳር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዛሬ ህዳር 14 ቀን 2004 ዓም ከቀኑ በ9 ሰአት በዋለው ችሎት ላይ ሁሉም እስረኞች እጆቻቸው በካቴና ታስሮ በፍርድ ቤቱ ተገኝተዋል። የፍርድ ቤቱን ሄደት ለመከታተል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ቢገኙም፣ ፖሊሶች ግን 20 ሰዎችን ብቻ እንደሚያስገቡ በመግለጣቸው አብዛኛው ህዝብ ሁኔታውን በውጭ ሆኖ ለመከታተል ተገዶአል። ፍርድ ቤቱ ከአንደኛውና ከአራተኛው ክሶች በስተቀር ሌሎች ክሶች መሰረተ ቢስ ናቸው፣ አንደኛውና ...
Read More »የአፋሩ ሀንፍሬ አሊ ሚራ፤ በበዓለ-ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር በመንግስት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው መንፀባረቁን ተዘገበ
ህዳር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ዓመት ሚያዚያ 26 ቀን በሞት በተለዩት አባታቸው በቢትወደድ ሱልጣን አሊሚራ ምትክ፤ ሰሞኑን እጅግ በደመቀ በዓል የሱልጣንነት ማዕረግ የተጎናፀፉት ሀንፍሬ አሊ ሚራ፤ በበዓለ-ሲመታቸው ላይ ባደረጉት ንግግር በመንግስት ላይ ቅሬታ እንዳላቸው መንፀባረቁን ሪፖርተር ዘገበ። “የአፋር ህዝብ ልብ፤ከመንግስት?ወይስ ከሱልጣን?” በሚል ርዕስ ጋዜጣው እንደዘገበው፤ የሀንፍሬ አሊሚራህን የሱልጣን ሲመት ለማክበር በኤርትራና በጅቡቲ የሚገኙትን ጨምሮ በአራቱም ማዕዘን የሚገኙ አፋሮች ...
Read More »በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የተከሰሱት 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢ ዜጎች የክስ ቻርጅ ዛሬ ጠዋት ቀርቦ ተነበበ
ህዳር 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱት 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢ ዜጎች የክስ ቻርጅ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጠዋት ቀርቦ ተነበበ፡፡ ከጠዋቱ 3፡40 ሰዓት ላይ በካቴና ታስረው ወደ ችሎት የቀረቡት በሀገር ውስጥ የሚገኙት ከተራ ቁጥር 1 እስከ ተራ ቁጥር 8 ያሉት ተከሳሾች ብቻ ...
Read More »በአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የአፍሪካ ተጠሪ የሆኑት ጆኒ ካርሰን፣ ኢትዮጵያ ሶማሊያን ዳግም መውረሯ ትክክል አይደለም አሉ
ህዳር 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለስልጣኑ ይህን ቃል የሰጡት ማክላቺ ለተባለው ጋዜጣ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ከአራት አመት በፊት ሶማሊያን በመውረር ለሁለት አመታት ያክል በአገሪቱ ውስጥ ብትቆይም፣ በመጨረሻ አልሸባብን መፍጠር በስተቀር ያመጣቸው ውጤት እንደሌለ ካርሰን ተናግረዋል። ካርሰን በሶማሊያ ሰላም ለማምጣት ማንኛውም እንቅስቃሴ በአፍሪካ ሰላም አስከባሪ በኩል መካሄድ እንዳለበት በመግለጥ የኢትዮጵያን እንቅስቃሴ በእጅጉ ነቅፈዋል። የመለስ መንግስት በድጋሜ ሶማሊያን ለመውረር ለምን እንደፈለገ ግልጽ ...
Read More »ይደርስባት የነበረውን ግፍ መቋቋም ተስኗት አሰሪዋን የገደለችው ኢትዮጵያዊትን ተከትሎ በኩዌት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ስቃይ ውስጥ መውደቃቸው ተሰማ
ህዳር 13 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለስልጣኑ በዋና ከተማዋ ኩዌት ሲቲ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለኢሳት እንደተናገሩት፤ እየደረሰባት ያለውን ግፍ መቋቋም ሢሳናት ሰሞኑን አሰሪዋን ስለገደለችው ኢትዮጵያዊት ሴት ጉዳይ በመገናኛ ብዙሀን ከተሰማ ጀምሮ፤ ኢትዮጵያውያን በየ ቦታው እየተገደሉ ነው። በዚህ ወር ብቻ እነሱ እንዳሉት ወደ ሰባት የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ኩዌት ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ተገድለዋል። ሁሉም በአሳዛኝና በሚያስደነግጥ ሁኔታ በየቦታው ሞተው መገኘታቸውን የጠቀሱት ኢትየጵያውያኑ፤ ይሁንና በ ...
Read More »የንግድ ሚኒስቴር 16 ታዋቂ የቡና ላኪ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ምርት ገባያ ውስጥ እንዳይሳተፉ አዘዘ
ህዳር 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እገዳው ከተጣለባቸው ኩባንያዎችና ግለሰቦች መካከል ካፍ ኢንተርናሽናል፣ አብዱልቃድር ሙሀመድ አሊና አብዱል አሊ የተባሉት ይገኙበታል። ንግድ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ምርት ገበያ በላከው ደብዳቤ ነጋዴዎቹ የታገዱት በመጋዘን ያስቀመጡትን ክምችት ባለማሳወቃቸው ነው ብሎአል። ይህ የቅርብ እገዳ በአጠቃላይ በአለፈው አንድ ወር ውስጥ ብቻ የታገዱትን የቡና ላኪዎች ቁጥር 57 አድርሶታል። አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ነጋዴ ለአዲስ አበባው የኢሳት ወኪል እንደተናገሩት ...
Read More »የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያ መግባት ጀመረ
ህዳር 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጉሬል በተባለችዉ ከኢትዮጵያ ድንበር በ80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ባለች ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለፁት ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችና ታንኮች የያዙ የኢትዮጵያ ወታደሮች እሁድ እለት ድንበር አቋርጠዉ ሶማሊያ መግባታቸዉን ተናግረዋል። የሶማሊያ መንግሰት ቃል አቀባይ አብዱራህማን ኡመር ኦስማን የኢትዮጵያ ወታደሮች በአለም አቀፍ ዉክልና ወይንም ከመንግስታቸዉ ጋር በሚደረግ ስምምነት ካልሆነ በስተቀር መግባት እንደማይችሉና በዚህ ረገድ በቅርብ የተፈፀመ ስምምነት ያለመኖሩን ...
Read More »ታዋቂዋ ኢኮኖሚስት ዳምቢሳ ሞዮ ኢትዮጵያ፣ ህልቆ መሳፍርት የውጭ እርዳታ ብታገኝም፣ አገሪቱ ግን አሁንም ከድህነት አልወጣችም” አሉ
ህዳር 12 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂዋ ኢኮኖሚስት ዳምቢሳ ሞዮ “የምእራባዊያን እርዳታ ማእከል የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ህልቆ መሳፍርት የውጭ እርዳታ ብታገኝም፣ አገሪቱ ግን አሁንም ከድህነት አልወጣችም” አሉ የ”ዴድ ኤንድ”ና የ “ሀው ዘ ዌስት ወዝ ሎስት” የሚሉ መጽሀፎችን የጻፉት ታዋቂዋ ኢኮኖሚስት ደምቢሳ ሞዮ ፣ “የኢትዮጵያ መንግስት የእርዳታ ለጋሾች ወዳጅ በመሆን በቡድን ስምንት አገሮች ስብሰባ ሳይቀር ቢገኝም፣ በኢትዮጵያ ግን አሁንም ድህነት ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ” ...
Read More »