ሚያዚያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰሞኑን ይፋ ባወጣው መረጃ መሰረት በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለአባይ ግድብ ግንባታ ያሳዩት ተነሳሽነት ዝቀተኛ መሆን፣ መንግስትን በእጅጉ ያበሳጨ ጉዳይ ሆኗል በማለት ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ መልእክቱን አስተላልፎአል። መንግስት ለግንባታው የሚውለውን አብዛኛውን የውጭ ምንዛሬ ከዲያስፖራው ለመሰብሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ዲያስፖራው እስከ ዛሬ ያዋጣው ገንዘብ ከ7 ሚሊዮን ዶላር በታች መሆን መንግስት ...
Read More »አልሸባብ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ጉዳት አደረስኩ አለ
ሚያዚያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ ከቀናት በፊት አልሸባብ መዳከሙን በገለጡበት ማግስት ነው ታጣቂው ሀይል ጥቃት መፈጸሙን ያስታወቀው። ኦል አፍሪካ ዶት ኮም እንደዘገበው ጥቃቱ የተፈጸመው ዋብሆ እና ዳክ በሚባሉ ቦታዎች ሲሆን፣ በጥቃቱም ሶስት የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገድለዋል ብሎአል። የኢትዮጵያ መንግስት ግን ጥቃቱ ስለመፈጸሙ የሰጠውም ማረጋጋጫ የለም። አቶ መለስ ወደ ሶማሊያ የላኩትን ጦር ወደ አገሩ የሚመልሱት ...
Read More »የፍትህና የነጋድራስ ጋዜጣ አዘጋጆች ፍርድ ቤት ቀረቡ
ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትህና የነጋድራስ ጋዜጣ አዘጋጆች ፍርድ ቤት ቀረቡ፣ በፍትህ ጋዜጣ ላይ ተጨማሪ አቤቱታ ቀርቧል:: በእነአንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የፍርድ ቤት ዘገባን አዛብተው አቅርበዋል በማለት የፌዴራል ዐቃቤ ህግ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቤቱታ ባቀረበባቸው መሠረት መልስ እንዲሰጡ ፍርድ ቤት የተጠሩት የፍትህና የነጋድራስ ጋዜጦች ዋና አዘጋጆች በጽሑፍ ምላሽ ሰጡ፡፡ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያደርገውን በረራ አቋራጠ
ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያደርገውን በረራ አቋራጠ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቃውሞውን ቀጥሎአል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ኦፊሴላዊ የጉዞ ማመላለሻ መሆኑ በተነገረ በወራት ውስጥ፣ ወደ አገሪቱ ዋና ከተማ ጁባ እና ወደ ማላካ የሚደረገው በረራ እንዲቋረጥ ተደርጓል። ጁባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመደወል ለማረጋጋጥ እንደተቻለው ሰራተኞቹ ወደ ጁባና ሌላዋ የደቡብ ...
Read More »አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት አሀዝ ከግማሽ በላይ አወረደው
ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአለም የገንዘብ ተቋም በመህጻረ ቃሉ አይኤም ኤፍ ኢትዮጵያ በያዝነው አመት 5 በመቶ እድገት እንደምታስመዘገብ ሲገልጽ፣ በርካታ የአፍሪካ አገሮች ከኢትዮጵያ የተሻለ እድገት እንደሚያስመዘግቡ ገልጧል። ምንም እንኳ አቶ መለስ በፓርላማ ንግግር ታሪካቸው ተገኝተው ለመጀመሪያ ጊዜ የዚህን አመት የኢትዮጵያ እድገት ሳይናገሩ ቢወጡም፣ የመንግስቱ መገናኛ ብዙሀን ግን አሁንም ኢትዮጵያ 11 በመቶ እድገት በማስመዝገብ፣ በአፍሪካ ፈጣን እድገት ...
Read More »የአሶሳ ሚሊኒየም ፓርክ በእሳት ቃጠሎ ወደመ
ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው የአሶሳ ሚሊኒየም ፓርክ ሰሞኑን በደረሰበት የ እሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ወደመ። መንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የአሶሳን ፖሊስ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የአሶሳን ሚሊኒየም ፓርክ ሙሉ ለሙሉ ላወደመው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ አንድ አርሶ አደር በቁጥጥር ሥር ውሏል። መንግስት ፤የእሳት ቃጠሎው የተነሳው በፓርኩ አቅራቢያ የሚገኘው ይኸው አርሶአደር የእርሻ ማሳውን ለማፅዳት የለኮሰው እሳት ...
Read More »ፕሮፌሰር ዚግፍሪድ ፓውዘባንግ አረፉ
ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ወዳጅ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ጀርመናዊው የማህበራዊ ሳይንስ ምሁር ፕሮፌሰር ዚግፍሪድ ፓውዘንቫንግ ከዚህ ዓለም መለየታቸውን የዘገበው ዶቼ ቨሌ ነው። ፕሮፌሰር ዚግፍሪድ ፓውዘንቫንግ ከ40 አመታት በላይ በኢትዮጵያ በተለይም በሰብዓዊ መብት እና ዲሞክራሲ በማስፈኑ ሂደት ላይ በማስተማር እና ስልጠና በመስጠት እንደሚታወቁ ገልጧል። ዚግፍሪድ ፓውዘንቫንግ ሶስት ጊዜ የኢትዮጵያ የምርጫ ታዛቢ የነበሩ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት ...
Read More »አቶ መለስ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚያቀርበውን የመብት ጥያቄ ውድቅ አደረጉት
ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአወልያ የተጀመረው ተቃውሞ በመላ አገሪቱ በሚገኙ መስኪዶች እየተስፋፋ መምጣቱን፣ ይህንን ተከትሎም በአዲስ አበባ እና በክልል አካባቢዎች በርካታ ሙስሊሞች እየታሰሩ በሚገኙበት በአሁኑ ጊዜ ፣ ከሙስሊም ማህበረሰቡ አመራሮች ጋር ለመነጋጋር ቀጠሮ የያዙት አቶ መለስ ፣ ከቀጠሮአቸው በፊት ሙስሊሙን ማህበረሰብ በሽብርተኝነት የሚፈርጅ ንግግር ትናንት ለፓርላማው አቅርበዋል። አቶ መለስ በንግግራቸው በአረቡ አለም ውስጥ የሚገኙ የሰለፊያ እስልምና እምነት ...
Read More »የኢትዮጵያ ወጣቶች ተስፋ ድርጅት በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ተነሱ የሚሉ የጥሪ ወረቀቶችን መበተኑን አስታወቀ
ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ በፎቶግራፍ አስደግፎ ለኢሳት የላከው መረጃ እንደሚያሳየው የተበተኑት ወረቀቶች ይዘት ከሞላ ጎደል ህዝቡ ለለውጥ እንዲነሳ የሚጠይቁ ናቸው። አንደኛው ወረቀት ላይ ” የትግላችን አላማ ሀገራችንንና ራሳችንን ነጻነት ለማቀዳጀት ነው።” የሚል መልእክት የሰፈረ ሲሆን፣ በሌላ ወረቀት ላይ ደግሞ ” ትግላችን በገዛ ሀገሩ ህይወት እየጨለመበትና ተስፋ እየቆረጠ ሀገሩን ጥሎ ሲሰደድ በረሀና ባህር እየበላው ወላጅ እናቱ የት ...
Read More »“አሁን ያለው የ ኢኮኖሚ ዕድገት፤ የቤተ-መንግስት እድገት ነው”ሲሉ ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ገለጹ
ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመመስረት ላይ ያለውን የሰማያዊ ፓርቲ በ አባልነት የተቀላቀሉት ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ ይህን ያሉት፤ ከሳምንታዊው ሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ላይ ነው። እርስዎ እንደ አንድ ምሁር በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ምን አስተዋፅኦ አደርጋለሁ ብለው ነው ወደ ፖለቲካ የሚገቡት? ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ፡- ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ለመስራት ስወስን ትልቁ ተልዕኮዬ ፓርቲውን በሰው ኃይል፣ በአመለካከትና በአሰራር ወደተሻለ ደረጃ ...
Read More »