አልሸባብ በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ጉዳት አደረስኩ አለ

 

ሚያዚያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ ከቀናት በፊት አልሸባብ መዳከሙን በገለጡበት ማግስት ነው ታጣቂው ሀይል ጥቃት መፈጸሙን ያስታወቀው።

ኦል አፍሪካ ዶት ኮም እንደዘገበው ጥቃቱ የተፈጸመው ዋብሆ እና ዳክ በሚባሉ ቦታዎች ሲሆን፣ በጥቃቱም ሶስት የኢትዮጵያ ወታደሮች ተገድለዋል ብሎአል። የኢትዮጵያ መንግስት ግን ጥቃቱ ስለመፈጸሙ የሰጠውም ማረጋጋጫ የለም። አቶ መለስ ወደ ሶማሊያ የላኩትን ጦር ወደ አገሩ የሚመልሱት  የአፍሪካ ሰላም አስከባሪ ሀይል በቦታው ተገኝቶ የተያዙትን ቦታዎች መቆጣጠር ሲችል ነው በማለት መናገራቸው ይታወሳል። ይሁን እንጅ የዩጋንዳም ሆነ የጂቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ጦር ለመተካት ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አይታይም።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide