አይ ኤም ኤፍ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት አሀዝ ከግማሽ በላይ አወረደው

ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአለም የገንዘብ ተቋም በመህጻረ ቃሉ አይኤም ኤፍ ኢትዮጵያ በያዝነው አመት 5 በመቶ እድገት እንደምታስመዘገብ ሲገልጽ፣ በርካታ የአፍሪካ አገሮች ከኢትዮጵያ የተሻለ እድገት እንደሚያስመዘግቡ ገልጧል። ምንም እንኳ አቶ መለስ በፓርላማ ንግግር ታሪካቸው ተገኝተው ለመጀመሪያ ጊዜ የዚህን አመት የኢትዮጵያ እድገት ሳይናገሩ ቢወጡም፣ የመንግስቱ መገናኛ ብዙሀን ግን አሁንም ኢትዮጵያ 11 በመቶ እድገት በማስመዝገብ፣ በአፍሪካ ፈጣን እድገት ያስመዘገበች ብቸኛ አገር እንደሆነች አድርገው ፕሮፓጋንዳ መስራታቸውን ቀጥለዋል። አይ ኤም ኤፍ በዚህ ሳምንት ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ የዚህ አመት እድገት 5 በመቶ ይሆናል ብሎአል። አይ ኤም ኤፍ ያወጣው ሪፖርት የመለስ መንግስት የዘንድሮውን ጨምሮ በሚቀጥሉት 5 አመታት አስመዘግበዋለሁ ከሚለው ከ11 እስከ 14 በመቶ ጋር ሲነጻጸር ከግማሽም በታች ነው። የአቶ መለስ መንግስት የትራንስፎርሜሽን እቅድ አገሪቱ በሚቀጥሉት አምስት አመታት 14 በመቶ እድገት እንደምታስመዘግብ ይተነብያል።
እንደ አይ ኤም ኤፍ ሪፖርት ከ5 በመቶ በላይ የኢኮኖሚ እድገት ያሚያመዘግቡት አገሮች ናይጀሪያ፣ አንጎላ፣ ጋቦን፣ ጃድ፣ ጋና ፣ ኮትዲቫር እና ቻድ፣ ታንዛኒያ፣ ኮንጎና ሞዛምቢክ ናቸው።
_____________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide