(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 16/2011)በአሜሪካ ሁለት ኢትዮጵያውያንን በመግደል ወደኢትዮጵያ አምልጧል በሚል በተጠርጣሪነት የሚፈለግን ግለሰብ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አሳልፎ እንዲሰጥ መወሰኑ ውዝግብ አስነሳ። ዮሀንስ ነሲቡ የተባለና የአሜሪካ ዜግነት ያለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ የ25 ዓመት ወጣት በአሜሪካን ቨርጂኒያ ግዛት ውስጥ ሁለት ወጣቶችን በመግደሉ አሜሪካ በጥብቅ ስትፈልገው የነበረ መሆኑ ተመልክቷል። ኢትዮጵያና አሜሪካ ወንጀለኛን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ሳይኖራቸው ተጠርጣሪውን ለአሜሪካ ለመስጠት በአቃቤ ህግ የተላለፈው ውሳኔ ህገወጥ ነው ...
Read More »ጎሰኝነት በህግ ይታገድ በሚል የማህበራዊ ድረ ገጽ ዘመቻ ተከፈተ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 16/2011)ጎሰኝነት በህግ ይታገድ በሚል በማህበራዊ ሚዲያዎች ዘመቻ መከፈቱ ታወቀ። በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያውያን ግብረሃይል የዘር ፖለቲካ እንዲታገድ የሚጠይቅ ትዕይንተ ህዝብ ሊያደርግ በዝግጅት ላይ መሆኑም ታውቋል። ከትላንት ጀምሮ በፌስ ቡክ፣ በቲውተርና በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያዎች በተጀመረው ዘመቻ ኢትዮጵያን ለአደጋ ያጋለጠ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዜጎቿን ለመፈናቀልና ለግድያ የዳረገው የጎሳ ፖለቲካ በህግ እንዲታገድ የሚጠይቁ መልዕክቶች በመተላለፍ ላይ ናቸው። በመንግስት የተጀመረው የማሻሻያ ስራ የጎሳ ...
Read More »አዴፓ ማብራሪያ የሚሰጥ መግለጫ አወጣ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 16/2011) የአማራ ክልላዊ መንግስት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር አምባቸው መኮንን አዲስ አበባን በተመለከተ በቅርቡ በሰጡት አስተያየት ዙሪያ ማብራሪያ የሚሰጥ መግለጫ አወጣ። ክልላዊ መንግስቱ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በህግ አግባብ ለመምራት በሚደረገው ጥረት ከኦሮሚያ ክልል ጎን ተሰልፎ የመታገል ጉዳይ ከመርህ ውጭ እየተተረጎመ ነው ሲል በመግለጫው አስፍሯል። በቅርቡ በአምቦ ከተማ ተካሄዶ በነበረው የአማራና የኦሮሞ የሕዝብ ለሕዝብ መድረክ ላይ ርእሰ መስተዳደሩ ዶክተር አምባቸው ...
Read More »ዶክተር ሰገነት ቀለሙ በካንሳስ ዩንቨርስቲ እውቅና ተሰጣቸው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2011)በእርሻ ምርምር ስራ የሚታወቁት ዶክተር ሰገነት ቀለሙ በሙያቸው ካላቸው የላቀ እውቀትና ባደረጉት አስተዋጽኦ በካንሳስ ዩንቨርስቲ እውቅና ተሰጣቸው። ዶክተር ሰገነት ያገኙት ዓለም አቀፍ እውቅና ከ12 ሰዎች መካከል ከተመረጡትና ከ5 ሴቶች መካከል አንዷ ሆነው በመመረጣቸው መሆኑን ዩንቨርስቲው አስታውቋል። የካንሳስ ግዛት ዩኒቨርሲቲ የአልሙኒ መርሃግብር ምክትል ፕሬዝዳንት አንድሪያ ብሪያንት ዶክተር ሰገነት በስራቸውና በተሰማሩበት የሙያ ዘርፍ የላቀ ተግባርና ውጤታማ የምርምር ስራ በማከናወናቸው የተመረጡ ...
Read More »ኢትዮጵያ አዲስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እየቀረጸች ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2011)ኢትዮጵያ አዲስ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እየቀረጸች መሆኑ ተገለጸ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ እንደገለጹት በስራ ላይ ያለው የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና ስትራቴጂ የቆየና አላስፈላጊ ዝርዝሮችን የያዘ በመሆኑ ይቀየራል። የነበረው ፖሊሲ ከውጭ ወደ ውስጥ የሚመለከት መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው አዲሱ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ጥቅም ቅድሚያ በሚሰጥ መልኩ የሚቀረጽ መሆኑን ገልጸዋል። አሁን በስራ ላይ ካለው የውጭ ጉዳይ ...
Read More »የሰርሃ ዛላምበሳ ድንበር በቅርቡ ሊከፈት ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2011) የሰርሃ ዛላምበሳ ድንበር በቅርቡ ሊከፈት እንደሚችል ተገለጸ። የኤርትራ መንግስት ባለስልጣናትን ጠቅሶ የኤርትራ ፕሬስ እንደዘገበው ሰሞኑን ከተዘጉትና ኢትዮጵያንና ኤርትራን ከሚያገናኙ ድንበሮች መካከል በዛላምበሳ በኩል ያለው በቅርቡ ይከፈታል። ኤርትራ የኢትዮጵያን የወደብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ወደ ምጽዋ የሚወስዱ መንገዶችን በመስራትና በመጠገን ላይ መሆኗንም አስታውቃለች። የድንበሮቹ መዘጋት ከባድ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናገዱ አቅም ያላቸው መንገዶችን ለመስራት ሊሆን እንደሚችልም ተጠቁሟል። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኟትን ሁለት ...
Read More »የኢትዮጵያ አድቬንቲስት ኮሌጅ የእርሻ መሬት እንዳይታረስ ተከለከለ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 15/2011) የኢትዮጵያ አድቬንቲስት ኮሌጅ የሚጠቀምበት የእርሻ መሬት እንዳይታረስ መከለከሉ ተገለጸ። በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ወረዳ ኩየራ አቅራቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ አድቬንቲስት ኮሌጅ በአከባቢው ወጣቶች መሬቱ ይገባናል የሚል ጥያቄ በመነሳቱ የዘንድሮው የእርሻ ዘመን መቅርቱን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ የቆየው ኮሌጁ ለዘመናት የሚጠቀምበት የእርሻ መሬት በህገወጥ መንገድ መታገዱን አስመልክቶ የአካባቢው የመንግስት ባለስልጣናት መፍትሄ እንዲሰጡ ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ያገኘነው መረጃ ...
Read More »ኤርትራ በአፋር በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ዘጋች
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 14/2011)ኤርትራ በአፋር በኩል ከኢትዮጵያ የሚያዋስናትን ድንበር መዝጋቷ ታወቀ። ወደ ኤርትራ የሚያስገባው የቡሬ መስመር ከትላንት ጀምሮ መዘጋቱን የአፋር ክልላዊ መንግስት አስታውቋል። ኤርትራ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር ስትዘጋ የቡሬው ሁለተኛው መሆኑ ነው። ባለፈው ሳምንትም በሁመራ መስመር ያለውን ድንበሯን መዝጋቷ የሚታወስ ነው። የቡሬ መስመር የተዘጋበት ምክንያት ግን አልተገለጸም። የትላንቱ የቡሬው መስመር መዘጋቱን ተከትሎ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስኗትን ...
Read More »የወላይታ ዲቻና የደቡብ ፖሊስ ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲካሄድ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 14/2011) የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ከደቡብ ፖሊስ ጋር የሚደረገው ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲካሄድ ጠየቀ። የእግር ኳስ ክለቡ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በጻፈው ደብዳቤ ቅዳሜ ዕለት በሃዋሳ ከተማ ሊደረግ የነበረው ጨዋታ በደጋፊዎቹና በንብረቱ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ጠቅሶ ከሀዋሳ ውጪ በገለልተኛ ቦታ እንዲደረግ ጥያቄ አቅርቧል። የሃዋሳ ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በደጋፊዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ...
Read More »የባስኬቶ ልዩ ወረዳና የመለኮዛ ወረዳ አመራሮች ከስልጣን ተነሱ
(ኢሳት ዲሲሚያዚያ 14/2011)በባስኬቶ ልዩ ወረዳና በመለኮዛ ወረዳ ለዜጎች መፈናቀል ምክንያት ናቸው የተባሉ አመራሮች ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ምንጮቹ እንደሚሉት አመራሮቹን ከስልጣን ማውረድ ብቻ ሳይሆን በቁጥጥር ስር እንዲውሉም ተደርጓል። አመራሮቹን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉ ነው የተገለጸው። ይህ በእንዲህ እንዳለም የወረዳው አመራሮች ባነሱት የቀበሌ ይገባኛል ጥያቄ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እየተሞከረ ነው መሆኑ ታውቋል። ነገር ...
Read More »