Amsterdam

የኤርትራ ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ

የኤርትራ ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ (ኢሳት ዜና ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኤርትራ የመጣውን ልኡካን ቡድን በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውለታል፡፡ የኤርትራው ፕሬዝዳንት አማካሪ እና የፖለቲካ ጉዳዮች ሃላፊ የማነ ገብረዓብ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳሌህና በአፍሪካ ህብረት የአገሪቱ አምባሳደር የሆኑት አርዓያ ደስታ ከልዑካን ቡድኑ አባላት መካከል ይገኙበታል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከኤርትራ ...

Read More »

በአሶሳ ብሄርን ማእከል ባደረገ ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ

በአሶሳ ብሄርን ማእከል ባደረገ ጥቃት 3 ሰዎች ተገደሉ (ኢሳት ዜና ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት ከሳምንት በፊት በስልጣን ላይ የነበሩ የህወሃት አባላት በብሄር ብሄረሰቦች መካከል ግጭት እንዲፈጠር ለማድረግ በርታና ጉምዞች በአማራ እና ኦሮሞ ተወላጆች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አስደርገው 3 ሰዎች መሞታቸውንና ከ20 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። የህወሃት ሰዎች በአካባቢው እንደነበሩ እና ባምባሲና እና አሶሳ ዙሪያ እየዞሩ የበርታ ...

Read More »

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠውን መልስ ተቃወመ

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የተሰጠውን መልስ ተቃወመ (ኢሳት ዜና ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ/ም) ኮሚቴው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰኔ 4 ቀን 2010 ዓም የወልቃይት የአማራ ብሄርተኝነት አስመላሽ ኮሚቴ ያቀረበው የማንነት ይከበርልኝ ጥያቄ ህግን ተከትሎ ያልተካሄደ ነው በማለት ውድቅ ማድረጉን በጽኑ ተቃውሞአል። የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ በመግለጫው የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሒም ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 አመጽ ነክ እንቅስቃሴ ከማድረግ መቆጠቡን አስታወቀ

አርበኞች ግንቦት7 አመጽ ነክ እንቅስቃሴ ከማድረግ መቆጠቡን አስታወቀ (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ከሰኔ 15 ቀን 2010 ዓም ጀምሮ አርበኞች ግንቦት 7 “በማናቸውም መልኩ በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍሎች ምንም አይነት አመጽ ነክ እንቅስቃሴ ከማድረግ ታቅቧል” ብሎአል። “ኢትዮጵያ ዉስጥ በየትኛዉም አካባቢ የሚገኙ የነጻነት ታጋዮቻችን ከማናቸውም የአመጽ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ ድርጅታዊ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል” ያለው ድርጅቱ ውሳኔው “በኢህአደግ ውስጥ ያሉ ...

Read More »

በቄለም ወለጋ ዞን የሚታዬው ውጥረት አለመቀነሱን የአማራ ተወላጆች ተናገሩ

በቄለም ወለጋ ዞን የሚታዬው ውጥረት አለመቀነሱን የአማራ ተወላጆች ተናገሩ (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በ1977 ዓም በነበረው ድርቅ ከወሎ ክፍለ ሃገር ተሰደው በቄለም ወለጋ መቻራ ዙሪያ የሚኖሩ አርሶአደሮች ለኢሳት እንደተናገሩት ትናንት ከጠዋት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ በሚሉ ወጣቶችና በእነሱ መካከል በነበረው ግጭት 11 ሰዎች ቆስለዋል። ግጭቱን ለማብረድ አባገዳዎች ጣልቃ ገብተው ለማስቆም ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ...

Read More »

ህወሃት የሰማዕታት ቀን በሚል የሚከበረውን በአል የተቃውሞ መገለጫ አድርጎት ዋለ

ህወሃት የሰማዕታት ቀን በሚል የሚከበረውን በአል የተቃውሞ መገለጫ አድርጎት ዋለ (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) ዛሬ የትግራይ ሰማዕታት ቀን በሐውዜን ከተማ በተከበረበት እለት የተያዙት መፈክሮች ህወሃት በቅርቡ የኢትዮ- ኤርትራን የሰላም ስምምነት በተመለከተ የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ያሳለፈውን ውሳኔ በመተቸት ያወጣውን መግለጫ የሚያንጸባርቁ ናቸው። የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝቦች ያልተሳተፉበት ሰላም ዘላዊ ሰላም አይሆንም፣ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ህዝቦች ለዘላቂ ሰላም ጣምራ ክንድ ...

Read More »

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የአርባምንጭ ወጣቶች እየታሰሩና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው

በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የአርባምንጭ ወጣቶች እየታሰሩና ስቃይ እየደረሰባቸው ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ የሽብር ወንጀል ሰበብ ተከሰው በእስር ቤት ከቆዩ በሁዋላ በቅርቡ የተለቀቁ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ ወደ አካባቢያቸው ቢመለሱም፣ ፖሊሶች እያሳደዱዋቸው ነው። ባለፈው ሳምንት ከእስር የተፈታው ኢንጅነር ጌታሁን በየነ ትናንት በፖሊሶች ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞበታል። ከጌታሁን በየነ ጋር አብሮ የነበረው ጓደኛው ወጣት ካሳሁን፣ ...

Read More »

ሪክ ማቻር ወደ ገለልተኛ አገር ሊዛወሩ ነው

ሪክ ማቻር ወደ ገለልተኛ አገር ሊዛወሩ ነው (ኢሳት ዜና ሰኔ 15 ቀን 2010 ዓ/ም) በደቡብ ሱዳን ላለፉት 4 አመታት የቆየውን ግጭት ለማስቆም የተቃዋሚ መሪ የሆኑት ሪክ ማቻር አሁን ከሚገኙበት ደቡብ አፍሪካ ወጥተው ወደ ገለልተኛ አገር ሊሄዱ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። እቅዱ በኢጋድ አገራት ተቀባይነት አግኝቷል። ኢትዮጵያ ውስጥ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የሰላም ንግግር ውጤት አልባ ሆኗል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ከቀድሞው ምክትል ...

Read More »

የምህረት አዋጁ በቅርቡ እንደሚጸድቅ ተነገረ

የምህረት አዋጁ በቅርቡ እንደሚጸድቅ ተነገረ (ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም) በሚቀጥለው ሳምንት ፓርላማው ያጸድቀዋል ተብሎ የሚጠበቀው የምህረት አዋጅ በሽብርተኝነት የተፈረጁ ድርጅቶች ምህረት እንደሚደረግላቸው ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ ገልጸዋል። አዋጁ ወደ ተወካዮች ምክር ቤት ቀድም ብሎ የተመራ ቢሆንም፣ ምክር ቤቱ እስካሁን መልስ አልሰጠበትም። ይሁን እንጅ በሚቀጥለው ሳምንት ውስጥ አዋጁ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ አርበኞች ግንቦት7 በዶ/ር ...

Read More »

በነዳጅ እጥረት የሚሰቃዩ የወልድያ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

በነዳጅ እጥረት የሚሰቃዩ የወልድያ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ (ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም)አሸክርካሪዎቹ በየጊዜው በሚጨምረው የነዳጅ ዋጋ መማረራቸውን ሲገልጹ ከቆዩ በሁዋላ ዛሬ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ ቶታል ነዳጅ ማደያ፣ ኦይል ሊቢያ እና ኖክ የነዳጅ ማደያዎች መታሸጋቸው ታውቋል። አጋጣሚውን በመጠቀም በሰልፉ ላይ የተቀላቀሉ ወጣቶች፣ “በዶ/ር አብይ ሙስና የለም” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን አሰምተዋል።

Read More »