በነዳጅ እጥረት የሚሰቃዩ የወልድያ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

በነዳጅ እጥረት የሚሰቃዩ የወልድያ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም)አሸክርካሪዎቹ በየጊዜው በሚጨምረው የነዳጅ ዋጋ መማረራቸውን ሲገልጹ ከቆዩ በሁዋላ ዛሬ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል።
ተቃውሞውን ተከትሎ ቶታል ነዳጅ ማደያ፣ ኦይል ሊቢያ እና ኖክ የነዳጅ ማደያዎች መታሸጋቸው ታውቋል።
አጋጣሚውን በመጠቀም በሰልፉ ላይ የተቀላቀሉ ወጣቶች፣ “በዶ/ር አብይ ሙስና የለም” የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን አሰምተዋል።