Amsterdam

ኢትዮጵያ ባጋጠማት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ በረዥም ጊዜ ክፍያ ነዳጅ ለማስገባት ሳኡዲ አረቢያን ጠየቀች።

ኢትዮጵያ ባጋጠማት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሳቢያ በረዥም ጊዜ ክፍያ ነዳጅ ለማስገባት ሳኡዲ አረቢያን ጠየቀች። ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ትናንት ረቡዕ ሀገራቸው ካጋጠማት የምንዛሬ እጥረት አንጻር በ12 ወራት ተከፍሎ በሚያልቅ እዳ የነዳጅ ዘይት እንድትሸጥላቸው ለሳኡዲ አረቢያ ጥያቄ እንዳቀረቡ መናገራቸውን፤ ሬውተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ብሄት ኃላፊ አቶ ፍጹም አረጋ በበኩላቸው ...

Read More »

ኢህአዴግ ህዳጣን ወይም አናሳ እያለ በሚጠራቸው ክልሎች የተፈፀሙ በደሎች አስከፊ መሆናቸውን የፌድራል ጉዳዩች እና የአርብቶ አደር ሚንስቴር ገለፀ፡፡

ኢህአዴግ ህዳጣን ወይም አናሳ እያለ በሚጠራቸው ክልሎች የተፈፀሙ በደሎች አስከፊ መሆናቸውን የፌድራል ጉዳዩች እና የአርብቶ አደር ሚንስቴር ገለፀ፡፡ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኢትዮ-ሶማሌ ክልል የፍትሕ አሰጣጥ ሂደት ላይ የታዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፣ ቅሬታዎች ላይ ምርመራ በማድረግ እና ችግሮቹን በመለየት በኢፌዴሪ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 21 የተቀመጡ መሠረታዊ የታራሚ መብቶችን የጣሱ ድርጊቶች መፈጸማቸውን አሳውቋል። ...

Read More »

በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ (ቢጂአይ) ውስጥ ምዝበራው ተባብሶ መቀጠሉ ተነገረ፡፡

በቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ (ቢጂአይ) ውስጥ ምዝበራው ተባብሶ መቀጠሉ ተነገረ፡፡ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) የቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካ በህወሃት ሰዎች እጅ ለዘመናት በቁጥጥር ስር መዋሉን ለመከላከል የሚሞክር አመራር በመጥፋቱ፤ ምዝበራው አሁንም ተባብሶ መቀጠሉን ሰራተኞች ናቸው የተናገሩት። መስከረም 3 ቀን 2009 ዓ.ም የኢሳት ቴሌቪዥን ፋብሪካው በህወሃት አባላት ቁጥጥር ስር መሆኑን የውስጥ አዋቂ ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ ባቀረበው ...

Read More »

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን አባቶች ለቤተክርስቲያኗ መከፋፈል መንግስትን ተጠያቂ አደረጉ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን አባቶች ለቤተክርስቲያኗ መከፋፈል መንግስትን ተጠያቂ አደረጉ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) ዘጋቢያችን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራት ኅብረት በቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል ስለሚካሄደው እርቀ ሰላምና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ ሲኖዶሱ የሰጠውን መግለጫ ተከትሎ በሀገር ውስጥ ሲኖዶስ ቅርብ ክትትል የሚያደርጉ የስራ ኃላፊዎችን አናግሮ ባጠናቀረው ዘገባ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከእርቅ ሰላሙ ጋር ...

Read More »

በአገሪቱ ያሉ “ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም፣ የማንነት ጥያቄዎች እና መብቶችን” የፌድሬሽን ምክር ቤት የማይመልስበት ደረጃ እየደደረሰ ነው ሲል የምክር ቤቱ መሪዎች አስታወቁ፡፡

በአገሪቱ ያሉ “ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም፣ የማንነት ጥያቄዎች እና መብቶችን” የፌድሬሽን ምክር ቤት የማይመልስበት ደረጃ እየደደረሰ ነው ሲል የምክር ቤቱ መሪዎች አስታወቁ፡፡ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) አሁንም ድረስ ለፌድሬሽን ምክር ቤት ቀርበው የታፈኑ የማንነት ጥያቄዎች በአስቸኳይ ካልተፈቱ እሳት ሊረጩ ይችላሉ ሲል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡ የፌድሬሽን ምክር ቤት ባለፉት ዓመታት በነበረው አመራር ከካሳ ተክለብርሃን እስከ ያለው አባተ ባለፉበት ...

Read More »

በሃረር ፖሊሶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

በሃረር ፖሊሶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) በሃረር ፖሊሶች በ5 መኪኖች ሆነው በሃረር ዋና ዋና መንገዶች መፈክሮችን እያሰሙ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ፖሊሶቹ የአንድ ብሄር የበላይነት ይቁም፣ የህዝብ መብት ይከበር፣ ሙሰኞች ለፍርድ ይቅረቡ፣ እኛ ፖሊሶች ከህዝባና ከቄሮዎች ጎን እንቆማለን፣ የተጀመረውን ለውጥ እንደግፋለን የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። በክልሉ የፖሊሶች ግምገማ በመካሄድ ላይ ነው።

Read More »

በራያ አላማጣ እና ዋጃ አካባቢዎች የሚደርሱ ጥቃቶች መጨመራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

በራያ አላማጣ እና ዋጃ አካባቢዎች የሚደርሱ ጥቃቶች መጨመራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 10 ቀን 2010 ዓ/ም ) የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል አባላት የጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ መስል ያለበትን ቲ ሸርት የለበሱ ሰዎችን እየያዙ በማሰር ላይ መሆናቸውን በአላማጣ ከተማ ከ300 በላይ ቲሸርቶችን ገዝቶ በማከፈፋሉ የተሳረው አቶ ሞገስ በላይ ለኢሳት ተናግሯል። በክልሉ ያሉ የፌደራል ፖሊሶች በያዙት ጊዜ የዶ/ር አብይን ቲሸርት ...

Read More »

በሃረሪ ፖሊስ ኮሚሽን መሳሪያ ግምጃ ቤት ውስጥ የበርካታ ሰዎች አጽም ተገኘ

በሃረሪ ፖሊስ ኮሚሽን መሳሪያ ግምጃ ቤት ውስጥ የበርካታ ሰዎች አጽም ተገኘ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 10 ቀን 2010 ዓ/ም ) ዛሬ ሃምሌ 10 ቀን 2010 ዓም በፖሊስ ኮሚሽን ግቢ ውስጥ በጓሮ በኩል የወዳዳቁ የሰው አጽሞች የተገኙ ሲሆን፣ እንዲሁም አሰሳ ያደረጉት ቄሮዎች እዛው አካባቢ ሌላ በጆንያ የተጠቀለለ ሌላ አጽም አግኝቷል። አዲሱ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኦድሪን በድሪና ምክትሉ አቶ ነቢል መሃዲ እንዲሁም ...

Read More »

በዚገም ወረዳ የነበረውን ችግር በውይይት ለመፍታት ውሳኔ ላይ ተደረሰ

በዚገም ወረዳ የነበረውን ችግር በውይይት ለመፍታት ውሳኔ ላይ ተደረሰ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 10 ቀን 2010 ዓ/ም ) ላለፉት 3 ቀናት በአዊ ዞን በዚገም ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ የአማራ ክልል አመራሮች ወደ አካባቢው በመሄድ ከህዝቡ ጋር ውይይት አካሂደዋል። በዛሬው ውይይት በቡሬ አድርጎ ዚገምን ከአዲስ አበባ ጋር የሚያገናኝ መንገድ ከመስከረም ጀምሮ ስራ እንደሚጀምር ፣ ቴክኒክና ሞያ ት/ት ቤት እንደ ሚከፈት፣ ሆስፒታል ...

Read More »

ዐቃቤ ሕግ በአርበኞች ግንቦት 7 የተከሰሱት ክስ እንዳይቋረጥ ጠየቀ

ዐቃቤ ሕግ በአርበኞች ግንቦት 7 የተከሰሱት ክስ እንዳይቋረጥ ጠየቀ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 10 ቀን 2010 ዓ/ም ) የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የአርበኞች ግንቦት 7 ስም ከአሸባሪነት ዝርዝር ቢነሳም ፣ በስሙ የተከሰሰሱትና በእስር ላይ የሚገኙት አባሎች ክሳቸው መነሳት የለበትም ሲል መከራከሩን ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው ዘግቧል። ሐምሌ 10/2010 ዓም በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በአርበኞች ግንቦት 7 ...

Read More »