በአገሪቱ ያሉ “ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም፣ የማንነት ጥያቄዎች እና መብቶችን” የፌድሬሽን ምክር ቤት የማይመልስበት ደረጃ እየደደረሰ ነው ሲል የምክር ቤቱ መሪዎች አስታወቁ፡፡

በአገሪቱ ያሉ “ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም፣ የማንነት ጥያቄዎች እና መብቶችን” የፌድሬሽን ምክር ቤት የማይመልስበት ደረጃ እየደደረሰ ነው ሲል የምክር ቤቱ መሪዎች አስታወቁ፡፡
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) አሁንም ድረስ ለፌድሬሽን ምክር ቤት ቀርበው የታፈኑ የማንነት ጥያቄዎች በአስቸኳይ ካልተፈቱ እሳት ሊረጩ ይችላሉ ሲል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡
የፌድሬሽን ምክር ቤት ባለፉት ዓመታት በነበረው አመራር ከካሳ ተክለብርሃን እስከ ያለው አባተ ባለፉበት መንገድ በህገ መንግስቱ የተነሱ የማንነት ጥያቄዎች እና መብቶች በቂ ምላሽ አላገኙም ሲል የ2ኛ እድገት ትራንስፎርሜሽን ሁለት አመታት ተኩል ግምገማ ከመንግስት ጉዳዩች ሚንስትር ጋር ባደረገው የምክክር መድረክ ላይ ገልጿል፡፡
በዚህም በርካታ የሰው ልጅ ህይዎት በማንነት ጥይያቄዎች ምክንያት ሲቀጠፍ ዝም ብሎ ተመልክቷል ተብሏል፡፡ ከደቡብ ክልላዊ መንግሥት ከሀድያ ዞን ከደንጣ ማኅበረሰብ የቀረበው የማንነት ፣ በአማራ ክልል በቅማንት ማኅበረሰብ የቀረበው የማንነት ጥያቄ ፣ 349 የንፁሐን ዜጎች ህይዎት በተለያየ ጊዜ ቀጥፏል። 1342 ዜጎች አሁንም ድረስ እስር ቤት እንዲገቡ ምክንያት ሁኗል፡፡ በቢልዮን የሚቆጠር መሰረተ ልማት አውድሟል፡፡ ለአካባቢው ኗሪዎች ስጋት እና እንግልት መሆኑ ቀጥሏል፡፡
ይሄ ሁሉ ችግር የተፈጠረው የፌድሬሽን ምክር ቤት ባግባቡ ስራውን ባለማከናወኑ ነው ያለው ሪፖርቱ፣ በተመሳሳይ ከማንነት እና ከሕገ – መንግሥታዊ መብቶች አኳያ በደቡብ ክልል ከዶርዜ፣ ከቁጫ፣ ከሀላባ፣ ከወለኔ፣ ከሲዳማ-ሀድቾ፣ ከማረቆ እና ከኮንሶ ማኅበረሰቦች፤ በኦሮሚያ ክልል የዛይና ጋሮ ማኅበረሰቦች፤ ከኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል የኢሳ ጎሳ አባላት የቀረቡ አቤቱታዎች ላይ ተገቢውን ምላሽ አላገኙም፡፡
አንዱ በቂ ምላሽ እንዳያገኙ እንዲገፉ ካደረጋቸው ጉዳዩች ውስጥም የፌድሬሽን ምክር ቤት በቂ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ፣ በአዋጅ ቁጥር 251/93 አንቀጽ 20 መሠረት በየክልሎቹ እንዲታዩ ጉዳዩን በመግፋት እልባት አሳጥቶታል ሲል ቀደም ሲል የምክር ቤቱ አመራር የነበሩት እና አሁን በአምባሳደርነት የተሾሙትን አቶ ካሳ ተክለብርሃን እና ያለው አባተ ላይ የውሳኔ ሰጭ ችግር ነበረባቸው ሲሉ የወቅቱ አፈ ጉባኤ ተናግረዋል።
በአፋር ክልል የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ባቀረቡት የመብት አቤቱታ መነሻነት ከቋሚ ኮሚቴው እና ከባለሙያዎች የተውጣጣ ቡድን በአካባቢው በመገኘት ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በችግሩ አፈታት ዙሪያ ውይይት አካሂዶ ቢመለስም ለክልሉ መንግስት የተሰጠው የአሰራር እና አመራር አካሄድ በእጅጉ ከህግ እና ከስርዓት ያፈነገጠ ነው ብለዋል። በእነዚህ እና መሰል አሰራሮች የፌድሬሽን ምክር ቤት የታፈኑ ፣ ጫና የሚታይባቸው አሰራሮች ከማንነት ጥያቁዎች አመላለስ አንፃር እሳት ሊረጩ ይችላሉ ሲሉ አቶ ወርቁ አዳሙ የምክር ቤቱ የማንነት ጉዳዩች ሰብሳቢ ተናግረዋል፡፡