በሃረር ፖሊሶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

በሃረር ፖሊሶች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም ) በሃረር ፖሊሶች በ5 መኪኖች ሆነው በሃረር ዋና ዋና መንገዶች መፈክሮችን እያሰሙ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል። ፖሊሶቹ የአንድ ብሄር የበላይነት ይቁም፣ የህዝብ መብት ይከበር፣ ሙሰኞች ለፍርድ ይቅረቡ፣ እኛ ፖሊሶች ከህዝባና ከቄሮዎች ጎን እንቆማለን፣ የተጀመረውን ለውጥ እንደግፋለን የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።
በክልሉ የፖሊሶች ግምገማ በመካሄድ ላይ ነው።