በዚገም ወረዳ የነበረውን ችግር በውይይት ለመፍታት ውሳኔ ላይ ተደረሰ

በዚገም ወረዳ የነበረውን ችግር በውይይት ለመፍታት ውሳኔ ላይ ተደረሰ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 10 ቀን 2010 ዓ/ም ) ላለፉት 3 ቀናት በአዊ ዞን በዚገም ወረዳ የተነሳውን ተቃውሞ ለማብረድ የአማራ ክልል አመራሮች ወደ አካባቢው በመሄድ ከህዝቡ ጋር ውይይት አካሂደዋል።
በዛሬው ውይይት በቡሬ አድርጎ ዚገምን ከአዲስ አበባ ጋር የሚያገናኝ መንገድ ከመስከረም ጀምሮ ስራ እንደሚጀምር ፣ ቴክኒክና ሞያ ት/ት ቤት እንደ ሚከፈት፣ ሆስፒታል ሚከፈት፣ የፍትህ አካላት በወንጀለኛ ፖሊሶች ላይ ምርመራ እንዲያደርጉና ቶሎ ወሳኔ እንዲሰጥ እስከዚያ የታሰሩት 31 ፖሊሶችን ህብረተሰቡ እንዲለቃቸው እና ንፁሃን ፖሊሶች ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ፣ የወረዳው ፖሊስ አዛጅ ወደ ሌላ አካባቢ እንዲዛወር፣ የወሪዳዋ አመራሮች አስቸኳይ ግምገማ ተደርጎ ከስልጣናቸው እንዲነሱ፣ መብራት ከ20 ቀን በሁዋላ ለ24 ሰዓት አገልግሎት እንደሚጀምር፣ የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ “ ለማድረግ ውሳኔ ላይ ተደርሷል። ባለስልጣናት ቃለ የገቡትን የማይፈጽሙ ከሆነ ህዝቡ በተደራጀ ሁኔታ እንደሚታገል ግልጽ አድርጓል።