በኤርትራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሁለቱም አገራት መሪዎች በተገኙበት በይፋ ተከፈተ ( ኢሳት ዜና ጳግሜን 01 ቀን 2010 ዓ/ም ) በኤርትራ ላለፉት ሃያ ዓመታት ተዘግቶ የነበረው የኢትዮጵያ ኤንባሲ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እና በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተመርቆ ተከፈተ። ከወራት በፊት ኤርትራም በተመሳሳይ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ተዘግቶ የቆየውን ኤንባሲዋን በአዲስ አበባ መክፈቷ ይታወሳል። ይህም የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነትን ወደ ላቀ ...
Read More »Amsterdam
በራያ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረው ጥቃት እንዲቆም የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተደረገ።
በራያ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረው ጥቃት እንዲቆም የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተደረገ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) የትግራይ ክልል በልዩ ጦሩና በሚሊሺያው አማካኝነት የሚፈጽመውን የመብት ጥሰት እንዲያቆም ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል። መነሻቸውን ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ያደረጉት ሰልፈኞቹ ፍትህ ለራያ ሕዝብ፣ ማንነታችን ይከበር፣ የትግራይ ልዩ ኃይል የሚፈጽመውን ጭፍጨፋ ያቁም፤ የሚሉና የተለያዩ መፈክሮችን አሰምተዋል። በሕዝብ ቀረጥ የሚተዳደረው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኢቲቪ ...
Read More »በረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከፍተኛ ሙስና መፈጸሙን የውስጥ ምንጮች ገለጹ
በረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከፍተኛ ሙስና መፈጸሙን የውስጥ ምንጮች ገለጹ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከ120 ሚሊዮን ዶላር ወይም አሁን ባለው ምንዛሬ ከ3 ቢሊዮን ብር ያላነሰ በጀት ተመድቦለት የተሰራው የአዲስ አበባ ረጲ የደረቅ ቆሻሻ ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከውል ስምምነት ጀምሮ ሙስና የተፈጸመበት እንደሆነና ለዚህም ዋናው ተጠያቂ በወቅቱ የኢትዮጵያ መብራት ሃይል ቦርድ ዳይሬክተር ዶ/ር ደብረጺዮን ...
Read More »አርቲስት ታማኝ በየነ በጎንደር ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
አርቲስት ታማኝ በየነ በጎንደር ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከሃያ ሁለት ዓመታት በኋላ ወደ ትውልድ አገሩ ኢትዮጵያ የተመለሰው የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና አርቲስት ታማኝ በየነ በዛሬው እለት በጎንደር ከተማ በመገኘት ከሚወዱት አድናቂዎቹ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቷል። ታማኝን በየነና ባለቤቱን አርቲስት ፋንቲሽ በቀለን ለመቀበል የከተማ ነዋሪዎች፣ የክልሉ ባለስልጣናትን ጨምሮ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከጎንደር አጼ ...
Read More »ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ሰመራ ገቡ
ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ሰመራ ገቡ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) ሱልጣኔ በአፋር ዋና ከተማ ሰመራ ሲደርሱ ህዝቡ ወጥቶ ደማቅ አቀባባል አድርጎላቸዋል። በሽግግር መንግስቱ ወቅት የአፋር ክልል መሪ የነበሩት ሱልጣን ሃንፍሬ፣ ከህወሃት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ከስልጣናቸው እንዲወርዱ በመደረጉ ለስደት ተዳርገዋል። በኢትዮጵያ የሚታየውን የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ ወደ አገራቸው የተመለሱት ሱልጣኑ፣ በክልሉ በሚካሄደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ዋና ተዋናይ ይሆናሉ ተብሎ ...
Read More »ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የአሰብ እና ምጽዋ ወደቦችን ጎበኙ።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የአሰብ እና ምጽዋ ወደቦችን ጎበኙ። ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 30 ቀን 2010 ዓ/ም ) ከሃያ ዓመታት በላይ ግንኙነታቸውን አቋርጠው የነበሩት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ እርቀ ሰላም በማድረግ ከመሪዎች እና ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነነት በተጨማሪ የወደብና የንግድ ሥራዎች በይፋ ጀምረዋል። ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በአሰብ ወደብ አየር ማረፊያ በማቅናት ወደቡንና ሁለቱን አገራት የሚያገናኘውን የጥርጊያ መንገድ ጎብኝተዋል። በአሁኑ ወቅት ያለው ...
Read More »የትግራይ ክልል አስተዳደር ያፈናቀላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቆቦ ሰፍረዋል
የትግራይ ክልል አስተዳደር ያፈናቀላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቆቦ ሰፍረዋል ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) የራያ ተወላጆች ህወሃት በሚያዛቸው ወታደሮች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገረዋል። በርካታ ወጣቶች የራያን የማንነት ጥያቄ በማንሳታቸው በርካታ ወታደሮችን ያስገቡት የህወሃት መሪዎች፣ በወጣቶች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ነው። ከ400 በላይ ተፈናቃይ ወጣቶች ከአላማጣ ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል በመሄድ ቆቦ ከተማ ላይ የሰፈሩ ...
Read More »የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መንግስት በወሰደው እርምጃ ግራ መጋባታቸውን ገለጹ
የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መንግስት በወሰደው እርምጃ ግራ መጋባታቸውን ገለጹ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ከመልካም አስተዳደር፣ ከደሞዝ፣ ከማበረታቻና ከፈቃድ ጋር በተያያዘ ላቀረቡት ጥያቄ የደህንነት ሰራተኞች እና ፖሊስ ድጋፋቸውን ሰጥተው የነበረ ቢሆንም፣ በሌሎች ባለስልጣናት ታዘው የአድማ መሪዎች የተባሉ ሰዎች እንዲታሰሩ መደረጉ አስገርሟቸዋል። 120 የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የአለማቀፍ ሲቪል አቬሽን እና አለማቀፍ የሰራተኞች ...
Read More »በሃረሪ ክልል የህግ የበላይነት እንዲከበር ተጠየቀ
በሃረሪ ክልል የህግ የበላይነት እንዲከበር ተጠየቀ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) የክልሉ ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ ጋዲሳ ተስፋዬ፣ የደቡብ ምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ፣ ጄ/ል ዱባለ አብዲ፣ የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ በመሩት ስብሰባ የክልሉ የጸጥታ ችግር እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል። ምክንያቱ ደግሞ ከአጎራባች ክልሎች ተደራጅተው የሚመጡ እና በተለያዩ ሰዎች በግልጽም በስወርም ድጋፍ የሚደረግላቸው ሃይሎች ናቸው ብለዋል። የእነዚህ ሰዎች ...
Read More »በደቡብ ሱዳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በእስር ቤት ስቃይ እንደደረሰባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ
በደቡብ ሱዳን በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በእስር ቤት ስቃይ እንደደረሰባቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ ( ኢሳት ዜና ነሐሴ 29 ቀን 2010 ዓ/ም ) በእስር ቤት ውስጥ ስቃይ የደረሰባቸው ሰዎች አብዛኛዎቹ የፖለቲካ እስረኞች ናቸው። በርካታ ሴቶችም በእስር ቤት ውስጥ ተደፍረዋል። የደቡብ ሱዳን መንግስት የሚቀርብበትን ትችት እንደማይቀበል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልጿል። የፕሬዚዳንት ሳለቫኪር ቃል አቀባይ አቴንግ ዋግ አቴንግ የአምነስቲን ሪፖርት አስተባብለው በቅርቡ 20 የፖለቲካ እስረኞች ...
Read More »