ታህሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰንደቅ በህዳር 25፣ 2005 ዓም እትሙ እንዳስነበበው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በሚኒስትሩና በሚኒስትር ዴኤታው መካከል ከፍተኛ ውዝግብ ተቀስቅሷል። በሁለቱ ሚኒስትሮች የተፈጠረው አለመግባባት በሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ላይ ግራ መጋባትን መፍጠሩን የጠቀሰው ሰንደቅ፣ ወደ 1 ሺህ 800 የሚጠጉ የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞችም ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን አልቻሉም ብሎአል። የጸቡ ምክንያት የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንትና ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ...
Read More »የአዲስ አበባ ወጣቶች የአንድነት የቃሊቲ ጉብኝት እንዲካሄድ ጠየቁ
ታህሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ወጣቶቹ ለኢሳት በላኩት መልእክት እንደገለጡት በመጪው እሁድ ታህሳስ 7፣ 2005 ዓም አለአግባብ የታሰሩ የሙስሊም ማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን፣ ጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ መሪዎችን በቃሊቲ ተገኝተው ለመጠየቅና ለመዘከር አስበዋል። ማንኛውም የህገመንግስቱን የእምነት እና ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መከበር እንዳለበት የሚደግፍ ኢትዮጵያዊ በሙሉ ወደ ቃሊቲ በመሄድ ድጋፉን እንዲያደርግ እንጠይቃለን ያለው መግለጫ፣ እነዚህ ታሳሪዎች ህገመንግስቱ የሰጣቸውን መብት በመጠቀም ...
Read More »መስተዳድሩ የሚድሮክን ሁዳ ሪል ስቴት መሬት ነጠቀ
ታህሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሥር ለሚገኘው ሁዳ ሪል ስቴት ሜክሲኮ አደባባይ ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል አጠገብ ሰጥቶት የነበረውን የግንባታ መሬት የነጠቀው መሬቱን ከተረከበ ካለፉት 8 አመታት ጀምሮ ግንባታ ባለማካሄዱ ነው፡፡ 6ሺ 400 ሄክታር ስፋት ያለው መሬት የተሰጠው ከፍታቸው ከ20 ፎቅ በላይ የሆኑ መንትያ ሕንፃዎች እንደገነቡበት ነበር። ሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ ...
Read More »ፕሬዚዳንት ሞርሲ መከላከያ ሰራዊቱ ህግ እንዲያስከብር ጠየቁ
ታህሳስ ፩(አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በግብጽ የተጀመረው ተቃውሞ የፕሬዚዳንቱን ስልጣን አደጋ ውስጥ እየከተተው መምጣቱን ተከትሎ ፕሬዚዳንቱ የጤር ሀይሉ ህግ እንዲያስከብር፣ የመንግስት ተቋማትን እንዲጠብቅና አጥፊዎችን እንዲያስር ስልጣን ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሞርሲ በቅርቡ ከፍተኛ ስልጣን የሚሰጣቸውን ህግ በመሰረዝ የህዝቡን ቁጣ ለማብረድ የሞከሩ ቢሆንም ፣ የህዝቡ ቁጣ ግን አሁንም ሊበርድ አልቻለም። ተቃዋሚዎች ለአዲሱ ህገመንግስት ድምጽ ለመስጠት የፊታችን ቅዳሜ የተያዘውን ቀጠሮ እንዲሰረዝ ቢጠይቁም፣ ...
Read More »ጠቅላይ ሚ/ር ሀይለማርያም ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር ለምታደርገው የእግር ኳስ ጨዋታ ቦታ እንዲለወጥ መጠየቁን አላውቅም አሉ
ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ይህን የተናገሩት ከአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ነው። ረዩተር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቃል አቀባይ የሆኑትን አቶ መላኩ አየለን በመጠቀስ ” ለተጫዋቾች ደህንነት ሲባል እግር ኳስ ፌደሬሽኑ የጨዋታው ቦታ እንዲቀየር መጠየቁን ” ዘግቦ ነበር። ቢቢሲና አልጀዚራን የመሳሰሉ ታላላቅ አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀንም ለጉዳዩ የዜና ሽፋን መስጠታቸው ይታወቃል። በኢትዮጵያ በኩል የቀረበውን ...
Read More »በባህርዳር ለሚከበረው 7ኛው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ዝግጅት 200 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ ታወቀ
ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት የመረጃ ምንጮች እንደገለጡት በአሉን ለማክበር የወጣው ገንዘብ እስካሁን ባለው ግርድፍ መረጃ 200 ሚሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ሂሳቡ ሲወራረድ ወጪው ከዚህም ከፍ ሊል ይችላል ተብሎአል። በትናንትናው ዕለትም በ20 ሚሊየን ብር የተሰራችው ህዳሴ የተሰኘች መርከብ የከተማዋ ነዋሪዎች፣እንግዶች፣ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቃለች፡፡ህገመንግስቱ የጸደቀበት ህዳር 29 የብሔርብሔረሰቦች በዓል ሆኖ እንዲከበር የፌዴሬሽን ም/ቤት በወሰነው መሰረት በዓሉ በፈንጠዝያና በግብዣ ...
Read More »በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የንብረት ውርስ ላይ ትእዛዝ ተሰጠ
ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከፍተኛው ፍርድ ቤት በ1ኛ ተከሳሽ በአቶ አንዷለም አራጌ ባለቤት ስም የተመዘገበው የቤት መኪና ፤ በ7ኛ ተከሳሽ አቶ እስክንድር ነጋ ስም የተመዘገበ 1 ቤትና ከእናታቸው በውርስ ያገኙት ተዳምሮ 2 መኖሪያ ቤቶች እና በባለቤታቸው ስም የተመዘገበ 1 የቤት መኪና ፤ እንዲሁም በሌሉበት በተከሰሱት በ16ኛ ተከሳሽ በአቶ አበበ በለው ባለቤት ስም ፥ የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ...
Read More »በግብጽ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲሱ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ትንሹ ሙባራክ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ህግ አውጥተዋል በሚል ለሳምንታት የተደረገው ተቃውሞ በመቀጠሉ መከላከያ ሰራዊቱ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል። ሰራዊቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አቋሙን ግልጽ ያደረገ ሲሆን ተቃዋሚዎችና መንግስት እንዲደራደሩ ጠይቋል። የአገሪቱን ተቋማት ለማስከበር አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድም ሰራዊቱ አስጠንቅቋል። ተቃዋሚዎች ፕሬዚዳንቱ አቀረቡትን የንግግር ጥያቄ አልተቀበሉትም
Read More »የሁለቱ ሲኖዶሶች የሰላምና አንድነት ጉባኤ እንደቀጠለ ነው
ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ረቡእ ሕዳር 26፡ 2005 የተጀመረው ስብሰባ በዛሬው እለት ለሶስተኛ ቀን ቀጥሎ እንደዋለ ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ። ስብሰባው እስከእሁድ ፕሮግራም የተያዘለት ቢሆንም፤ ምናልባት ከእሁድ በፊት በዛሬው እለት ውጤቱ ሊታወቅ ይችላል ሲሉ አንዳንድ ምንጮች ገልጸዋል። የኢትዮጵያው ልኡካን ዳላስ በደረሱበት እለት ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ለፓትሪያርክ መርቆሬዎስ የጻፉትን ደብዳቤ ተከትሎ ...
Read More »ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለሕዝብና ለመንግስት ጥሪ አደረጉ
ህዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፕሬዚዳንት፤ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ መንግስት ሕገ መንግስቱን እንዲያከብር፤ የኢትዮጵያ ህዝብም ሕገ-መንግስታዊ መብቱ እንዲከበር እንዲታገል ጥሪ አደረጉ። ዶ/ር ነጋሶ ዛሬ አርብ ህዳር 28 ቀን ከኢሳት ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ባደረጉት ቃለምልልስ፤ ኢህአዴግ ከጥቂት አመታት ወዲህ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን እያለ የሚጠራው ህዳር 29 ቀን፤ በዋንኛነት ሕገመንግስቱ የጸደቀበት ቀን እንደሆነ ...
Read More »