በአርማጭሆ የካርቱም አስተዳዳሪ ጥቃት ተፈጸመባቸው

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአማራ ክልል ተቆርሶ ለሱዳን የተሰጠውን መሬት ለማስመለስ ወደ አርማጭሆ የተጓዙት የካርቱም አስተዳዳሪ ጥቃት ተፈጸመባቸው አተያር የተባለው የሱዳን ጋዜጣ እንደዘገበው የካርቱም አስተዳዳሪ የሆኑት  ከረመላ አባ ሼክ ከትናንት በስቲያ የመለስ መንግስት የለገሳቸውን መሬት በጉልበት ከአርማጭሆ ህዝብ አስመልሳለሁ በማለት ወደ አማራ ክልል እየተጓዙ ነበር። አስተዳዳሪው ወደ ቦታው ደርሰው ገበሬዎቹን ሰብስበው በማነጋገር ላይ እያሉ፣ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች ...

Read More »

ወደ ዋልድባ ገዳም የተጓዙ ምእመናን በፌደራል ፖሊስ ታገዱ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዋልድባን ከሚደርስበት ጥፋት እንከላከል በማለት ወደ ገዳሙ የተንቀሳቀሱ ምእመናን በፌደራል ፖሊስ ታገዱ በርካታ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎችን የጫኑ ከ5 በላይ መኪኖች መጋቢት 27  ቀን 2004ዓም ወደ ዋልድባ ገዳም ሲንቀሳቀሱ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት አስቀድመው መንገድ ላይ በመጠባበቅ ምእመናኑ እንዳይንቀሳቀሴ ማገዳቸው ታውቋል። በህዝቡና በምእመኑ መካከል ውዝግብ በመፈጠሩም መነኮሳት ህዝቡን ለማግባባትና ወደ ሁዋላ እንዲመለስ ለማድረግ መቻላቸው ታውቋል። ...

Read More »

ኢትዮጵያ የተመድ ሰራተኛን በሽብርተኝነት ወንጅላ አሰረች

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ አምነስቲ ኢንተርናሽናልን ጠቅሶ እንደዘገበው ግለሰቡ የታሰሩት ከኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ ነው። የተመድ የደህንነት ሰራተኛ የሆኑት አብዱረህማን ሼክ ሀሰን ለእስር የተዳረጉት በኦጋዴን ክልል የተጠለፉትን ሁለት የሶማሊ ተወላጆችን ለማስለቀቅ ድርድር እንዲጀመር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው። የመንግስት ቃል አቀባይ የሆነው ሽመልስ ከማል የተመድ ሰራተኛ ስለመታሰሩ እንደማያውቅ ተናግሯል። የአምነስቲ ኢንትርናሽናል የአፍሪካ ተመራማሪ የሆኑት ...

Read More »

አቶ ሽፈራው ሺጉጤ ከቤንች ማጂ ዞን የተፈናቀሉ 800 አማሮች ብቻ ናቸው አሉ

ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ስፈራው ሽጉጤ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከ30 አመት በላይ የኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች አሁንም ሰላማዊ ኑሮአቸውን እየመሩ ነው።                                   በ2000 ዓ.ም በጉራፌርዳ ወረዳ 22 ሺ 46፣ በሜኒሻሻ 1ሺ 484 ፣ በሜኒት ጎልደያ ደግሞ 1ሺ 520 የአማራ ክልል ተወላጆች መኖራቸውን የገለጡት ፕሬዚዳንቱ ፣ የክልሉ መንግሥት በ2001 ዓ.ም አንድ ሰፋሪ ሁለት ሄክታር ...

Read More »

ባለፉት ሶስት ቀናት ከጉርፋዳ ወረዳ የተባረሩ የአማራ ተወላጆች ደብረብርሀን እና ባህርዳር ደረሱ

መጋቢት ፳፱ (ሃይ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት ዘጋቢዎች እንደገለጡት ከጉርዳፋ ወረዳ ከተባረሩት በአስር ሺዎች ከሚቆጠሩት የአማራ ተወላጆች መካከል በ8 መኪኖች የተጫኑ ደብረብርሀን ላይ እንዲራገፉ ሲደርግ የተቀሩት ደግሞ ወደ ባህርዳር አምርተዋል። ከሾፌሮቹ ለመረዳት እንደተቻለው ሰዎቹ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ጥብቅ መመሪያ ተሰጥቷል። ዘጋቢያችን አንዳንዶችን አነጋግሮ እንደዘገበው የሚፈናቀለው የአማራ ተወላጅ ቁጥር የመገናኛ ብዙሀን ከሚዘግቡት በእጅጉ የላቀ ነው።ተፈናቃዮቹ በአንድነት ሆነው ወደ ...

Read More »

በደቡብ ኦሞ ስውር እስር ቤቶች ተበራክተዋል ሰዎችም በህገወጥ መንገድ እየተገደሉ ነው ተባለ

መጋቢት ፳፱ (ሃይ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ኦሞ ዞን የመድረክ አባል ድርጅቶች የሆኑት አንድነት ለፍትህ ና ለዲሞክራሲ፣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት መጋቢት 7፣ 2004 ዓም ለደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በጻፉት ድብዳቤ በዞኑ የሚገኙ በህግ ያልታወቁ እስር ቤቶች እንዲዘጉ ጠይቀዋል።   ድርጅቶቹ በሰሜን አሪ ወረዳ 67 በመቶ፣ በማሌ ወረዳ 70 በመቶ እንዲሁም በቤና ...

Read More »

አንድ አርሶአደር በፍትህ እጦት ምክንያት ራሳቸውን አጠፉ

  መጋቢት ፳፱ (ሃይ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል በሲዳማ ዞን በጩኮ ወረዳ ማንጉዶ ቀበሌ በግብርና ስራ ይተዳዳሩ የነበሩት አቶ ካሚሶ ካያሞ የቀበሌው ሊቀመንበር የይዞታ መሬታቸውን ስለቀማቸው ለተለያዩ የመንግስት አካላት አቤቱታ ቢያቀርቡም የሚሰማቸው ባለማግኘታቸው ነው ራሳቸውን አጠፉት።   አርሶ አደሩ ራሳቸውን ከማጥፋታቸው በፊት መጋቢት 20 ቀን 2004ዓም ” ልጆቼና ቤተሰቤ በችጋር ሲያልቁ አላይም፣ ፍትህ የለም በግፍ መሬቴን ስለተነጠኩ ...

Read More »

የአፋር ሽማግሌዎች ከመሬታችን የሚለየን ሞት ብቻ ነው ይላሉ

መጋቢት ፳፰ (ሃይ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን ኢሳት በአፋር አካባቢ የሚገኙ ሰፋፊ ቦታዎችን መንግስት ለሸንኮራ አገዳ እርሻ ልማት እንደሚፈልገው ማስታወቁን ተከትሎ የአካባቢው ህዝብ ተቃውሞ ማሰማቱን መዘገቡ ይታወሳል። የህዝቡ ተቃውሞ ያሰጋው መንግስት በአካባቢው የእርሻ ስራ እየሰሩ ያሉት ዶዘሮች በልዩ ሀይል እንዲጠበቁ በማድረግ የእርሻውን ስራ በጉልበት ለማካሄድ ወስኗል። የመንግስትን እርምጃ የተቃወሙ አፋሮች ተደብድበዋል ብዙዎችም ታስረዋል። ቤታችን አናፈርስም ብለው በመቃወማቸው ከታሰሩት ...

Read More »

በዱባይ በአሰሪዋ ተገድላ ግቢ ውስጥ ተቀብራለች የተባለችው ወጣት እጣ ፋንታ መጨረሻው አልታወቀም

መጋቢት ፳፰ (ሃይ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዱባይ በአሰሪዋ ተገድላ ግቢ ውስጥ ተቀብራለች የተባለችው ወጣት እጣ ፋንታ አልታወቀም ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት የኢትዮጵያው ዲፕሎማት መረጃ አልሰጥም ብለዋል። በዱባይ በአሰሪዋ ተገድላ ጓሮ ውስጥ ስለተቀበረችው ወጣት ኢትዮጵያ ኢምባሲ በቂ ክትትል እንዳላደረገ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉት በዱባይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገልጠዋል። በተለይም አረጋሽ እየተባለች የምትጠራዋ ኢትዮጵያዊት ድርጊቱን ይፋ ካደረገች በሁዋላ አሁንም ድረስ በኢትዮጵያ ኢምባሲ ውሰጥ ...

Read More »

በ2011ዓ/ም የመን የገቡት ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ቁጥር 65ሺህ መሆኑ ታወቀ

መጋቢት ፳፰ (ሃይ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በየመን ኢትዮጵያዉያን ስደተኞች ከፍተኛ ችግር፤ እስራትና እንግልት እየደረሰባቸዉ መሆናቸዉን የዘገበዉ የመን ታይምስ ጋዜጣ የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኛ ከፍተኛ ኮሚሽነርን በመጥቀስ እንደገለፀዉ እኤአ በ20110 የመን የገቡት ስደተኞች ቁጥር 34ሺህ 422 ሲሆን በ2011 ይኸዉ ቁጥር ወደ 65ሺህ ከፍ ማለቱን አመልክቷል። በ2010 ከገቡት መካከል 616 ሰዎች እስካሁን የት እንደደረሱ የማይታወቅ ተገልጿል።   የየመን መንግስት ወታደሮች ህገወጥ ናቸዉ ...

Read More »