በባህርዳር በመቶዎች የሚቆጠሩ በልመና የሚተዳደሩ ሰዎች ተይዘው አንድ ካምፕ ውስጥ ታጎሩ

ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ለኢሳት ከባህርዳር የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በከተማዋ ውስጥ በመዘዋወር ይለምኑ የነበሩ ሰዎች ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ ተሰብስበው ጅንአድ እየተባለ በሚጠራው ስፍራ እንዲጠራቀሙ ተደርጓል። ጎስቋሎቹ የተያዙት በባህርዳር የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች በአል  ውበት ይቀንሳሉ፣  ለከተማዋም መጠፎ ምስል ይፈጥራሉ  በሚል ምክንያት ነው። እንደ ፈለጉ የመዘዋወር ህገመንግስታዊ መብታቸው ተጥሶ እንዲታጎሩ የተደረጉት ጎስቋሎች፣ በአሁኑ ጊዜ በቂ ምግብና ውሀ ያግኙ አያግኙ የታወቀ ነገር የለም። ከታጎሩት መካከል አሮጊቶችና ህጻናት እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሎአል።

በተመሳሳይ ዜናም በከተማ ውስጥ በድለላ ስራና በወያላነት የሚሰሩ ወጣቶች እየተያዙ በመታሰር ላይ ናቸው። ወጣቶቹ በአሉን ለማክበር ወደ አካባቢው የሚሄዱትን እንግዶች ሊያውኩ ይችላሉ በሚል ምክንያት ነው የሚታሰሩት። ባለፉት ሶስት ቀናት እስርን በመሸሽ በርካታ ወጣቶች መደበቃቸውን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል።

በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየቱን የጠየቅነው ወጣት እንዳለው “ ጎስቋሎችን በመደበቅ ፣ ለማኝ ጠፍቷል እያሉ ራስን ማታለል አይቻልም፣ የልመና ምንጩን ካላደረቅነው፣ ለማኞቹ ነገ ሲለቀቁ ተመልሰው ከተማዋን ማጣበባቸው አይቀርም።” ሲል አስተያትን ሰጥቷል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as

other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide