በግብጽ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አዲሱ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ ሙርሲ ትንሹ ሙባራክ እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ህግ አውጥተዋል በሚል ለሳምንታት የተደረገው ተቃውሞ በመቀጠሉ መከላከያ ሰራዊቱ መፍትሄ እንዲፈለግ ጥሪ አቅርቧል።

ሰራዊቱ ለመጀመሪያ ጊዜ አቋሙን ግልጽ ያደረገ ሲሆን ተቃዋሚዎችና መንግስት እንዲደራደሩ ጠይቋል።

የአገሪቱን ተቋማት ለማስከበር አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድም ሰራዊቱ አስጠንቅቋል።

ተቃዋሚዎች ፕሬዚዳንቱ አቀረቡትን የንግግር ጥያቄ አልተቀበሉትም