በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ የንብረት ውርስ ላይ ትእዛዝ ተሰጠ

ህዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከፍተኛው ፍርድ ቤት በ1ኛ ተከሳሽ በአቶ አንዷለም አራጌ ባለቤት ስም የተመዘገበው የቤት መኪና ፤ በ7ኛ ተከሳሽ አቶ እስክንድር ነጋ ስም የተመዘገበ 1 ቤትና ከእናታቸው በውርስ ያገኙት ተዳምሮ 2 መኖሪያ ቤቶች እና በባለቤታቸው ስም የተመዘገበ 1 የቤት መኪና ፤ እንዲሁም በሌሉበት በተከሰሱት በ16ኛ ተከሳሽ በአቶ አበበ በለው ባለቤት ስም ፥ የተመዘገበ መኖሪያ ቤት ላይ የቀረበውን የውርስ አቤቱታ ያደመጠ ሲሆን አቶ አንዱአለም ባለቤት በጠበቃቸው አማካኝነት መኪናዋ ልጆችን ትምህርት ቤት የምታመላልስ መሆኗን ጠቅሰዋል።  የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል ችሎት ቀርበው እንዳማይከራከሩ በችሎቱ ላይ ተገልጿል።

የ አቶ አበበ በለው  ባለቤትም ችሎት ስላልቀረቡ ለታህሳስ 18 መጥሪያ ደርሷቸው ችሎት እንዲገኙ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት ለታህሳስ 18 ቀን 2005 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል