በጅጅጋ በዘራችን ብቻ የንግድ ድርጅቶቻችንን ተቀማን በማለት ነዋሪዎች ገለጹ

ታህሳስ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በሶማሊ ክልል በጅጅጋ ከተማ ተወልደው ያደጉ  በንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት በአማራ ክልል በመገኘት የብሄር ብሄረሰቦችን በአል አክብረው በተመለሱ ማግስት የንግድ ድርጅቶቻችሁን አስረክቡ እንደተባሉ ገልጸዋል። ቀደም ብሎ ታይዋን እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የልብስ እና የተለያዩ ሸቀጣሸቀጥ ሱቆችን ከፍተው ሲሰሩ የነበሩ ነጋዴዎች እንደገለጹት፣ መንግስት ሱቆቻቸውን እንዲያስረክቡ ያደረጋቸው ፣ የሌሎች አካባቢ ተወላጆች የንግድ ድርጅቶችን ...

Read More »

በማረቃ ወረዳ አንድ ግለሰብ በፖሊስ ተገደለ

ታህሳስ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ታህሳስ 4 ቀን 2005 ዓም ማንነቱ ያልታወቀው ግለሰብ የተገደለው በወንጀል ተጠርጥሮ ከተያዘ በሁዋላ ነው። ግለሰቡን ተኩሶ የገደለው ፖሊስ በስም አልታወቀም። ይሁን እንጅ የወረዳው ፖሊስ ግለሰቡ ሊያመልጥ ሲል ተገደለ የሚል ምክንያት መስጠቱን ለማወቅ ተችልኦል። የተርጫ ዞን የፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮሚሽነር አለማየሁ ጦፉ ግድያ መፈጸሙን ባይሸሽጉም ፣ ዝርዝሩን ከስብሰባ እንደወጡ እንደሚሰጡ ቢገልጹም ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ...

Read More »

ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ማሰማታቸውን ቀጥለዋል

ታህሳስ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ላለፈው አንድ አመት የጁመዓን ጸሎት ተከትሎ  ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት ተቃውሞ  ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። ኢትዮጵያውያኑ መንግስት ድምጻችን ይስማን፣ የታሰሩ መሪዎች ይለቀቁ፣ መንግስት የለም ወይ በማለት ድምጻቸውን አስምተዋል። ከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ በተካሄደበት በዚህ ተቃውሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በአንዋር መስጊድና በውጭ በመሆን ድምጻቸውን አሰምተዋል። በሴቶች መስገጂያ በኩል የጸጥታ ሀይሎች 11 የሚሆኑ ሴቶችን ይዘው ማሰራቸው ...

Read More »

ፌዴራል ፖሊስ አገሪቱን በስለላ ካሜራዎች ለማጥለቅለቅ አቅዷል

ታህሳስ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የፌዴራል ፖሊስ ከሁለት ዓመት በፊት በአዲስአበባ ተክሎ ሥራ ላይ ያዋላቸው የስለላ ካሜራዎች (cctv ካሜራዎች) ውጤታማ በመሆናቸው ወደክልሎች ለማስፋፋት ማቀዱን አስታወቀ፡፡ ከፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው በኢትዮጵያ የፖሊስ ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስአበባ ዋናዋና መንገዶች ላይ ካሜራዎችን በመግጠም የመቆጣጠሪያ ክፍል በማቋቋም በመንገዶቹ ላይ የሚሰሩ ሕገወጥ ድርጊቶችንና የትራፊክ አደጋዎችን በአነስተኛ የፖሊስ ኃይል ያለብዙ ወጪና ድካም ...

Read More »

በመቀሌ ከተማ ጋዜጣ”መፅሄትና መፃሕፍት በማዞርና መንገድ ዳር በመዘርጋት ሽጠው የሚተዳደሩ ወገኖች ስራቸውን እንዲያቆሙ ታዘዙ

ታህሳስ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በመቀሌ ከተማ ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች”ህፃናትና ኣዛውንቶች ከታሕሳስ 5/2005ዓ/ም ጀምረው ስራቸውን እንዲያቆሙ የከተማው ኣስተዳደር ከፖሊስና ሚሊሻ ሓይሎች ጋር በመቀናጀት ኣስቁመዋቸዋል$ እነዚህ ወገኖች ጋዜጣ”መፅሄትና መፃሕፍት በማዞር”መንገድ ዳር ተቀምጦው በመሸጥ የዕለት ገቢያቸው ንየሚያገኙ ሲሆኑ የከተማው ኣስተዳደር ጋዜጣና መፅሄት እንዳያዞሩና ኣንድ ቦታ ላይ ተቀምጠውም እንዳይሸጡ  ያዘዘ ሲሆን፣  ያላቸው መጽሄት እና ጋዜጣ ሽጠው እንዲጨርሱ የኣምስት ቀን ዕድል ሰጧቸዋል ...

Read More »

በማረሚያቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰት መኖሩን መንግስታዊው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አመነ

ታህሳስ ፭(አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- መንግስታዊው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መኖራቸውን በይፋ አመነ፡፡ ኮሚሽኑ በባህርዳር ከተማ የተከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ተከትሎ ሰሞኑን ባካሄደው ስብሰባ ላይ የቀረበ አንድ ጥናት እንዳመለከተው በሕገመንግስቱ የተደነገጉና አገሪቱ ተቀብላ ያጸደቀቻቸውን ዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶች በሚቃረን መልኩ በአንዳንድ ማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በታራሚዎች ላይ እየተፈጸሙ መሆኑን ይፋ ...

Read More »

የጋምቤላ ጭፍጨፋ 9ኛ አመት ታስቦ ዋለ

  426 የአኝዋክ ብሄረሰብ ተወላጆች የተገደሉበት 9ኛው አመት የጋምቤላ ጭፍጨፋ ዛሬ በመላው ዓለም ታስቦ ውሏል። በተለይም የአኝዋክ ብሄረሰብ ተወላጆች በብዛት በሚገኙበት የሜኒሶታ ግዛት መታሰቢያው በሀዘን ድባብ እየተደረገ መሆኑን ዶ/ር ማኝ ኛንግ ለኢሳት ገልጸዋል። ከ9 አመት በፊት፤ በታህሳስ 1996 ዓ.ም. በአኝዋክ ብሄረሰብ አባላት እንደተገደሉ የሚጠረጠሩ ስምንት የመሀል አገር ሰዎችን ወይም ደገኞችን ሞት ለመበቀል በሚል ሰበብ፤ የመንግስት ወታደሮች የተማሩ አኝዋክ ብሄረሰብ ተወላጆችን ...

Read More »

ሜጀር ጄነራል አብርሀ በኦጋዴን ጦርነት አትራፊ ናቸው ተባለ

ሜጀር ጄነራል አብርሀ በኦጋዴን ጦርነት አትራፊ ናቸው ተባለ በኦጋዴን ደገሀቡር ውስጥ በመንግስት ወታደሮችና በኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ተዋጊዎች መካከል በተደረገ ውጊያ፤ ከሁለቱም ወገን 32 ሰዎች መገደላቸው ሲገለጽ፤ ጦርነቱን የሚያቀጣጥሉት ከአካባቢው ከሚካሄደው የኮንትሮባንድ ንግድ ትርፍ የሚያጋብሱ የምስራቅ እዝ የጦር አዛዥ ጄኔራል አብርሀ ወልደማሪያም እና የክልሉ ፕሬዚዳንት ናቸው ሲሉ የኦብነግ አመራር አባል አቶ ሀሰን አብዱላሂ ለኢሳት ገለጹ። በጅጅጋ የሚገኙ ዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ...

Read More »

በኢትዮጵያ በ2003 ዓም ብቻ 100 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ተዘርፎ ወደ ውጭ ባንኮች መግባቱ ታወቀ

ታህሳስ ፬(አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጥናቱን ይፋ ያደረገው አለማቀፍ እውቅና ያለው ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ የተባለው ተቋም ሲሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2010 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2003 ዓም ብቻ ከኢትዮጵያ በተለያዩ መንገዶች ተዘርፎ ወደ ውጭ አገር ባንኮች የተላከው ገንዘብ 5 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን 400 ሺ ዶላር ወይም በጊዜው በነበረው ምንዛሬ ወደ  100 ቢሊዮን  ብር ነው። ገንዘቡ የተዘረፈው በአብዛኛው በሙስ እና  በታክስ ማጭበርበር ...

Read More »

አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቦርድ ሰብሳቢነት ተነሱ

ታህሳስ ፬(አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለቤታቸው ወ/ሮ ሀቢባ ሙሀመድ ከሳውዲ አረብያ መንግስት 50 ሺ ብር እና ቅዱስ ቁራን መጽሀፎችን ተቀብለዋል ተብለው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በሁዋላ፣ በአቶ ጁነዲን ሳዶ ላይ የሚወሰደው እርምጃ በርትቶ አሁን ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የቦርድ ሰብሳቢነት እንዲነሱ ተደርጓል። አቶ ጁነዲን ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰትርነታቸው ከተነሱ  እንዲሁም በኦህዴድ ውስጥ ተራ አባል ሆነው እንዲቀጥሉ ከተወሰነ በሁዋላ ነው፣ የአዲስ አበባ ...

Read More »