መንግስት በድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች ላይ በድጋሜ ዘመቻ ሊከፍት ነው

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባገኘው አስተማማኝ መረጃ  ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድምጻችን ይሰማ በማለት በየሳምንቱ የሚያቀርቡት ተቃውሞ የስርአቱን ህልውና እየተፈታተነው በመምጣቱ መንግስት ችግሩን በድርድር ከመፍታት ይልቅ በከፍተኛ እና መካከለኛ እንዲሁም በቀበሌዎች አካባቢ ያሉ የተቃውሞ አስተባባሪዎችን በመለየት ሰብስቦ ለማሰር እና ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ክስ ለመመስረት ማቀዱ ታውቋል። በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ታማኝ ...

Read More »

የፌዴራል ዋና ኦዲተር በመንግስት መ/ቤቶች ከፍተኛ ምዝበራ መኖሩን አጋለጠ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ዋና ኦዲተር በኢትዮጽያዊያን 2004 በጀት ዓመት በ116 የፌዴራል መንግስት ተቋማት ላይ ባካሄደው ኦዲት በድምሩ በ84 መ/ቤቶች ከ5 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብና የውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ በወቅቱ ያለመወራረድ ችግሮች ማግኘቱን ይፋ አደረገ፡፡ የፌዴራል ዋና ኦዲተር የ2004 በጀት ዓመት ሒሳብ የኦዲት ግኝት ሪፖርቱን ዛሬ ለፓርላማ ያቀረቡት ዋና ኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ ...

Read More »

ሉሲ ወደ ኢትዮጵያ መመለሷ ተገለጸ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እጅግ አወዛጋቢ በሆነ ሁኔታ ያለፉትን 5 አመታት በአሜሪካ ያሳለፈችው ለኢትዮጵያ “የሰው ዘር መገኛ” የሚል ስም ያሰጠችው ብርቅየዋ የኢትዮጵያ ቅርስ ሉሲ ( ድንቅነሽ) ወደ አገሯ መመለሱዋን መንግስት አስታውቋል። በአሜሪካ በ350 ሺ ሰዎች እንደተጎበኘች የተነገረላት ሉሲ ወደ አገሯ የተመለሰቸው ትክክለኛዋ ሉሲ መሆኑዋን እና አለመሆኑዋን አለማቀፍ እውቅና ያላቸው ኢትዮጵያውያን የመስኩ ባለሙያዎች ማረጋገጫ አልሰጡም። ወደ አገሩዋ ...

Read More »

በደብረማርቆስ ከተማ አንድ መሀንዲስ ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ከተያዙ በሁዋላ በማግስቱ ተለቀቁ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ ባለሀብት ለኢሳት እንደገለጹት ፣ መሀንዲሱ ገንዘብ ካላመጣችሁ የግንባታ ፈቃድ አልሰጥም በማለቱ ባለሀብቱ ከዞኑ ፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በብሮቹ ላይ ልዩ ምልክት በማድረግ 13 ሺ ብር መስጠታቸውን ቀረውን 7 ሺ ብር እንደሚሰጡትም ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል። መሀንዲሱ ገንዘቡን ከተቀበሉ በሁዋላ ፖሊሶች በስፍራው ደርሰው በቁጥጥር ስር አውለውታል። ይሁን እንጅ ምክንያቱ በውል ...

Read More »

የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኅብረት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የትግል ጥሪ አስተላለፈ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ያለተፎካካሪ ሥልጣኑን በኃይል የተቆጣጠረውን ኢህአዴግ በማስወገድ የሕዝብ ሥልጣን ባለቤትነትን ለማምጣት ብቸኛው መፍትሔ በፅናትና በቆራጥነት መታገል ብቻ መሆኑ ተገለፀ። የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጊዜያዊ ኮሚቴ ትላንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ሀገራችን ከገባችበት ፈተናና ሕዝቡ ከሚቀበለው ሥቃይ ልናላቅቀው የምንችለው ከያዘን የፍርሃት ቆፈን ተላቀን ባንድነት በመቆም ቀኑ የደረሰውን አምባገነን ሥርዓት ወደተመኘው መቃብር ለመሸኘት በጽናት መታገል ብቻ ...

Read More »

ኢትዮጵያ በሚመጣው ዓመት የኤሌክትሪክ እጥረት ያጋጥማታል

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት የ200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት እንደሚያጋጥማት ጥናቶች አመለከቱ። ሀገሪቱ ይህንን ችግር ለመወጣት ባለፉት ዓመታት በወር 100 ሚሊዮን ብር ለጄኔሬተሮች ወጪ ስታደርግ ቆይታለች አሁንም በማውጣት ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ያካሄደውን ጥናት ጠቅሶ ካፒታል ጋዜጣ እንደዘገበው፣ ሀገሪቱ በሚቀጥለው ዓመት የሚያጋጥማት የ200 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ኢኮኖሚውን ...

Read More »

የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ለ3 ቀናት ያቃጠለው እሳት ጠፋ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሳውና ለሦስት ቀናት የዘለቀው የሰደድ እሳት ባካባቢው ሕዝብ ርብርብ መቆሙተገለጠ። ሰደድ እሳቱ ከፓርኩ ይዞታ 15 ኪ.ሜ. ያህል ዘልቆ ጥፋት አድርሷል።ኢሳት ዛሬ ያነጋገራቸው የደባርቅ ከተማ ነዋሪ መንግሥት በወቅቱ የወሰደው የማጥፋት ሙከራ ባለመኖሩ ኅብረተሰቡ እሳቱን ለመቆጣጠር ሦስት ቀን ሊወስድበት ችሏል ብለዋል። በሌላ በኩል ግን ዛሬ በተለይ ከኢሳት ጋር ቃለ ምልልስ ...

Read More »

በኤፕሪል 15 የቦስተን ማራቶን ቦምብ ፍንዳታ የተጠረጠሩ ተጨማሪ ሶስት ሰዎችን ይዞ ማሰሩን የቦስተን ፖሊስ አስታወቀ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- እንደቢቢሲ ዘገባ ፖሊስ ስለተያዙት ሰዎች ማንነትና በፍንዳታው ዙሪያ የነበራቸውን የተሳታፊነት ድርሻ በተመለከተ ተጨማሪ ነገር ከመናገር ተቆጥበዋል። ለሦስት ሰዎች መሞትና ከ260 ሰዎች በላይ መቁሰል ምክንያት በሆነው የቦስተኑ ማራቶን የቦምብ ፍንዳታ የ19 ዓመት ወጣት የሆነው ጆሃር ሰርናዬቭ በተጠያቂነት መከሰሱ የሚታወቅ ነው። የ26 ዓመቱ የሰርናዬቨ ወንድም ከፍንዳታው 3 ቀናት በኋላ ከፖሊሶች በተተኮሰ ጥይት መገደሉ ...

Read More »

የኔዘርላንዷ ንግስት ስልጣናቸውን ለልጃቸው አስረከቡ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 33 አመታት በስልጣን ላይ የቆዩት የኔዘርላንድስ ንግስት ቢያትሪክስ በአምስተርዳም  እጅግ በደመቀ ስነስርአት ስልጣናቸውን ለ46 አመቱ ልጃቸው ዊሊያም አሌክሳንደር በየአመቱ ሚያዚያ 30 በሚከበረው የንግስቷ የልደት ቀን በአል ላይ አስረክበዋል። የንጉሱ ባለቤት የሆኑት አርጀንቲናዊዋ የባንክ ሰራተኛም በስነስነስርአቱ ላይ ንግስት ተብለው ተሹመዋል። በኔዘርላንድስ የነገስታቱ ባህል መሰረት በስልጣን ላይ ያለው ንጉስ ወይም ንግስት እድሜያቸው ሲገፋ ...

Read More »

በጉራፈርዳ ወረዳ ተጨማሪ የአማራ ተወላጆች ተፈናቀሉ

ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አዲሱ ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ባለስልጣኖቻቸው ከእንግዲህ አንድም ሰው እንዳያፈናቅሉ ባስጠነቀቁ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በደቡብ ክልል በቤንች ማጂ ዞን በጉራፈርዳ ወረዳ የሚኖሩ 90 የአማራ ተወላጅ አባዎራዎች ከክልሉ መባረራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። እንደገለጹት የአማራ ተወላጆች በተቀነባበረ ዘመቻ ክልሉን ለቀው እንዲወጡ እየተደረገ ነው። እስካሁን የተባረሩት ሰዎች አድራሻቸው ካለመታወቁም ሌላ ፣ ባለፉት ሁለት ቀናት የተባረሩ ...

Read More »