በደብረማርቆስ ከተማ አንድ መሀንዲስ ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ከተያዙ በሁዋላ በማግስቱ ተለቀቁ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ ባለሀብት ለኢሳት እንደገለጹት ፣ መሀንዲሱ ገንዘብ ካላመጣችሁ የግንባታ ፈቃድ አልሰጥም በማለቱ ባለሀብቱ ከዞኑ ፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በብሮቹ ላይ ልዩ ምልክት በማድረግ 13 ሺ ብር መስጠታቸውን ቀረውን 7 ሺ ብር እንደሚሰጡትም ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል።

መሀንዲሱ ገንዘቡን ከተቀበሉ በሁዋላ ፖሊሶች በስፍራው ደርሰው በቁጥጥር ስር አውለውታል። ይሁን እንጅ ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ሁኔታ ግለሰቡ ለአንድ ቀን ታስሮ በማግስቱ እንዲለቀቅ መደረጉን ገንዘቡን የሰጡት ባለሀብት ተናግረዋል። “ፍትህና ስርአት አለ ብለን አመልክተን ግለሰቡን እጅ ከፍንጅ ብናስይዘውም፣ እኛ ጠቁመን ከመመለሳችን ተከሳሹ ቀድሞ ተፈትቶ ጠበቀን ሲሉ ተናግረዋል።