ሉሲ ወደ ኢትዮጵያ መመለሷ ተገለጸ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-እጅግ አወዛጋቢ በሆነ ሁኔታ ያለፉትን 5 አመታት በአሜሪካ ያሳለፈችው ለኢትዮጵያ “የሰው ዘር መገኛ” የሚል ስም ያሰጠችው ብርቅየዋ የኢትዮጵያ ቅርስ ሉሲ ( ድንቅነሽ) ወደ አገሯ መመለሱዋን መንግስት አስታውቋል። በአሜሪካ በ350 ሺ ሰዎች እንደተጎበኘች የተነገረላት ሉሲ ወደ አገሯ የተመለሰቸው ትክክለኛዋ ሉሲ መሆኑዋን እና አለመሆኑዋን አለማቀፍ እውቅና ያላቸው ኢትዮጵያውያን የመስኩ ባለሙያዎች ማረጋገጫ አልሰጡም። ወደ አገሩዋ ተመለሰች የተባለችው ሉሲ በገልልተኛ ምሁራን ተረጋግጦ መግለጫ እስካልተሰጠ ድረስ ትክክለኛነቱን አምነን ለመቀበል ይቸግረናል በማለት የተለያዩ ሰዎች አስተያየታቸውን በማህበራዊ ሚዲያዎች አቅርበዋል። በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ምእራባዊያን አገራት ቅርሶቻቸውን ለማስጠበቅ የሚያወጡትን ገንዘብ ግምት ውስጥ በማስገባት ለሚሰጡት አስተያየት መንግስት  በገለልተኛ አካላት በማስፈተሽ ትክክለኛዋ ሉሲ መሆኑዋን ማረጋገጥ ይኖርበታል በማለት አስተያየታቸውን የሰጡ በርካቶች ናቸው።

ወደ አገሩዋ የተመለሰቸው እውነተኛዋ ሉሲ መሆኑዋ ቢረጋገጥ እንኳን ሉሲ በገንዘብ ወይም በሌላ መንገድ ለኢትዮጵያ ያስገኘችው ጥቅም ለህዝብ ይፋ መደረግ አለበት በማለት አስተያየታቸውን የሰጡም አሉ።