ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር አቶ ሶፊያን አህመድ ለፓርላማው ባቀረቡት የ2006 በጀት መግለጫ ላይ በቀጣዩ ዓመት አገሪቱ 154 ቢሊየን 903 ሚሊየን 290 ሺህ 899 ብር ረቂቅ በጀት በሚኒስትሮች ም/ቤት መጽደቁን አመልክተዋል። ይህ በጀት ከአምና ጋር ሲነጻጸር የ12 ነጥብ 3 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ በረቂቅ በጀቱ ድልድል ከተደረገላቸው ተቋማት መካከል መከላከያ 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር፣ ...
Read More »በመተማ የሁለት ቀበሌ ነዋሪዎች በመሬት ዙሪያ ከመንግስት ጋር እየተወዛገቡ ነው
ሰኔ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመተማ ዮሐንስ እና ኮኪት ቀበሌዎች የሚኖሩ አርሶአደሮች መሬታችን አድሎአዊ በሆነ መልኩ ለባለሀብቶች እየተሰጠብን ነው በማለት ተቃውሞአቸውን እያሰሙ ነው። የነዋሪዎቹ ተወካይ እንደተናገሩት አቤቱታቸውን ለም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም ለአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ቢያቀርቡም ፣ ባለስልጣኖቹ ” አልሰማንም ” የሚል መልስ ከመስጠት በስተቀር ፣ ለችግራቸው ፈጣን መልስ አልሰጡም። መንግስት መሬት የአለአግባብ እየተረፈ ...
Read More »በአፋር ፌደራል ፖሊሶች ከህዝቡ ጋር ሲታኮሱ ዋሉ
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት የ20 አመቱ ወጣት የሆነው ሙሀመድ ካይብ የፌደራል ፖሊስ አባላት በቅርበት ባሉበት በኢሳዎች መገደሉን ተከትሎ፣ አፋሮች ገዋኔ ወለጌሊ እየተባለ በሚጠራ ስፍራ ከፌደራል ፖሊስ ጋር ዛሬ ሲታኮሱ ውለዋል። ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ተኩሱ አለመቆሙን ለማወቅ ተችሎአል። ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ተኩስ የከፈቱት ፣ ፖሊሶቹ ሆን ብለው ሁለቱን ብሄረሰቦች ለማጋጨት እየጣሩ ነው በሚል ...
Read More »በማዳበሪያ እዳ ለስደትና ለእንግልት ተዳርገናል ሲሉ አርሶ አደሮች ተናገሩ
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሺንዲ ወንበርማ ወረዳ የማንችለውን ውዝፍ የማዳበሪያ እዳ እንድንከፍል በመገደዳችን ለስደትና እንግልት ተዳርገናል ሲሉ በርበሬ አምራች አርሶ አደሮች ተናግረዋል ፡፡ በመንግስት በታጠቁ ሀይሎች ሀብት ንብረታችን ተዘርፎና የቤታችን ቆርቆሮው ተገፎ ተወስዶብናል ያሉት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አርሶ አደሮች፣ ዛሬ ቤት ንብረታችንን ጥለን ቤተሠባችንን በትነን ለስደት ተዳርገናል ብለዋል። በአየር ንብረት መዛባት ችግር በደረሰብን አደጋ ምርታችን በከፍተኛ ደረጃ ...
Read More »ፓዌ ወደ ልዩ ወረዳነት እንድትመለስ የጠየቁ ነዋሪዎች እንግልት እንደደረሰባቸው አስታወቁ
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን የሚኖሩ ነዋሪዎች ፓዌ በፊት ትጠራበት ወደነበረው ልዩ ወረዳነት እንድትመለስ በመጠየቃቸው ከፍተኛ እንግልት እና ድብደባ እየደረሰባቸው መሆኑን ፡፡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ በወረዳዋ የሚኖሩ ወጣቶች በጋራ እንደገለፁልን ከ1977 ዓ.ም በፊት ከሃገሪቱ የተለያዩ ክልሎች በሠፈራ መጥተው ፓዌ ወረዳ ላይ የቆዩ ሲሆን በ1983 ዓ.ም በአካባቢው ከሚኖሩ ጉምዝ፣ ሺናሻ፣ ርታ፣ ማኦ እና ኮሞ ...
Read More »በሙስና የታሰሩት የጉምሩክ አቃቤ ሕግ፣ ቀብረውት የነበረ ከ1ሚልዪን በላይ ብር መገኘቱ ተነገረ
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሙስና ተጠርጥረው በማረሚያ ቤት የሚገኙት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓቃቤ ህግ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ማርክነህ አለማየሁ ቀብረውታል የተባለ ከአንድ ሚልዮን ብር በላይ መገኘቱ ታውቋል። ጉዳዪን የሚከታተለው የምርመራ ቡድን እንዳስታወቀው ከሆነ፣- አቶ ማርክነህ አለማየሁ በወንድማቸው አማካኝነት ለመሰወር አቅደው የቀበሩት አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ዘጠና ሺ ብር የተገኘው ወላይታ ሶዶ፣ ወራንዛላሸ በተሰኘች ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ...
Read More »የህዳሴውን ግድብ ግንባታ በኢትዮጵያ ሕዝብ መዋጮ ብቻ መሸፈን ወይም ዳር ማድረስ አይቻልም ተባለ
ሰኔ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሥራ ዓለምም በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጊዜያዊ ጽሕፈት ቤት በተለያዩ ኃላፊነቶች የሠሩትና የፈረንሳይ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር ሀይሉ ወልደጊዮርጊስ ይህን የገለጹት እሁድ ለህትመት ከበቃው ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር በ ዓባይ ግድብ ዙሪያ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። “ የ ዓባይ ውሀ በህግ ላይ የሚያቀርበው ፈተና” በሚል ርዕስ በፈረንሳይኛ መጽሐፍ ያሳተሙት አምባሳደር ሀይሉ ...
Read More »የምርጫ 97 የሰኔ 1 ሰማዕታት ታስበው ዋሉ
ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በምርጫ 97 ወቅት “የተጭበረበረው የወላጆቻችች ድምጽ ይመለስ” በማለት ወደ አደባባይ ወጥተው በግፍ የተጨፈጨፉት የምርጫ 97 ሰምአታት 8ኛ አመት በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቦ ውሎአል። በሟቹ ጠቅላይ ሚ/ር መለስ ዜናዊ ትእዛዝ ከ100 በላይ ኢትዮጵያውያን ሰኔ አንድ ቀን 1997 ዓም በአጋዚ ወታደሮች መጨፍጨፋቸው ይታወሳል። በተፈጥሮ ሞት ከተለዩት ከአቶ መለስ ዜናዊ በስተቀር ጭፍጨፋውን በመምራት የተባበሩት ሌሎች ባለስልጣኖች ዛሬም ...
Read More »የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ በከፍተኛ የአስተዳደር ችግር ውስጥ መግባቱዋን የሀይማኖት አባቶች ገለጹ
ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንዳንድ ካህናት የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች በመሆናቸው ቤተክርስቲያኑዋን እየጎዱዋት ነው ሲሉ የሀይማኖት አባቶች ገልጸዋል ኢሳት ያነጋገራቸው የተለያዩ ሀይማኖት አባቶች እንደገለጹት በስልጣን ላይ ያሉ አንዳንድ ካህናት መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ትተው የገዢው ፓርቲ ካድሬ በመሆናቸው ፣ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ለሚታየው የአስተዳደር መበላሸት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸው። ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የሀይማኖት አባት “በከተማው፣ በገጠሩ በርካታ ...
Read More »አዋሳ እና ባህርዳር ከ 2006 ዓ.ም ጅምሮ በፌደራል መንግስት ሥር ሊሆኑ ነው
ሰኔ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የደቡብ ክልል ርእሰ መዲና ሓዋሳ እና የአማራ ክልል ርእሰ መዲና ባህርዳር የክልል ርእሰ መዲናነታቸውን በማስረከብ በቀጥታ በፌደራል መንግስቱ አንደሚተዳደሩ ታውቋል፡፡ የሚኒስትሮች ም/ቤት ለውይይት ባዘጋጀው ሰነድ ላይ እንደገለጸው ከተሞቹ ከርእሰ መዲናነት ወደ ፌዳራል ከተማነት በመሸጋገር ለማእከላዊ መንግስት ግብር ይከፍላሉ፣ በማእከላዊ መንግስት ይተዳደራሉ። በአቶ አዲሱ ለገሰ መሪነት የብአዴን ባለስልጣናት ውይይት አድርገዋል። ባህርዳር የክልል ርእሰ መዲናነቱዋን ...
Read More »