ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በተለያዩ የአውርጳ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ ያቋቋሙት “በአውሮጳ የኢትዮጵያዊያን አንድነት ታስክ ፎርስ” የኢህአደግ መንግሥት በዜጎች ላይ የሚፈጽመውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲያቆምና የዜጎችን መብት እንዲያከብር ለመጠየቅ የፊታችን ረቡዕ ጁን 19 ቀን 2013 የአውሮጳ ህብረት መቀመጫ በሆነው ብራስልስ የህብረቱ ካውንስል ጽ/ቤት ፊት ለፊት ታላቅ ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ መዘጋጀታችውን ለኢሳት ከላኩት መረጃ ለማወቅ ተችሎአል። ...
Read More »የሁለት የቤንሻንጉል ጉምዝ ምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት ተነሳ
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረዋል ያላቸውን ሁለት የምክር ቤት አባላት የሕግ ከለላ ማንሳቱን አስታወቀ። የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ የሆኑት አቶ አቡሽ ሙስጠፋ እንደገለጹት ከሆነ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ያቋቋመው አጣሪ ቡድን ባሰባሰበው መረጃ መሠረት በካማሽ ዞን በያሶ ወረዳ የሚኖሩ በሺህ የሚቆጠሩ የአማራ ...
Read More »በደብረ ታቦር ከተማ 2 ወጣቶች በደህንነት ሀይሎች ተይዘዉ ተወሰዱ
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በፋርጣ ወረዳ በመንገድ ትራንስፓርት ውስጥ የሚሰሩ ምስጋናዉ መልካም እና በሪሁን ዉበቴ የተባሉ ወጣቶች ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ እና ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች። ገልጸዋል። በደብረታቦር ባለፈው ሳምንት 6 ወጣቶች በተመሳሳይ ምክንያት መታሰራቸው ይታወቃል። በፈቀደ እግዚ ኮሌጅ መምህር የሆኑት ታደሰ መንግስቴ እና ፍቃዱ ጌትነት እንዲሁም በደብረ ታቦር የ2ኛ ደረጃ መምህር ...
Read More »ኮከብ አርማ የሌለው ሰንደቅ ዓላማ ተጠቅማችኃል በሚል የእግር ኳስ ደጋፊ ወጣቶች ተደበደቡ
ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ኢትዮጵያ ትናንት ደቡብ አፍሪካን ማሸነፉዋን ተከትሎ ምሽት ላይ በነቂስ ወደ አደባባይ ወጥተው ድጋፍ ካደረጉት የባህር ዳር ነዋሪዎች መካከል በዛ ያለ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች “የኮከብ ዓርማ የሌለውን ሰንደቅ ዓላማ በመልበሳቸው፣ እንዲሁም ‹‹ሰማያዊ ፤ሰማያዊ ደገመው ዋልያዊ››፣ “ኢትዮጵያዊው ለሰንደቅ አላማው ፤ለሰማያዊው ” እያሉ ደስታቸውን በመግለጻቸው፣ ከፌደራል ፖሊሶች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተው አምሽተዋል። ፖሊሶች ሰንደቅ ዓላማውን ...
Read More »በአባይ ግድብ ዙሪያ ከፍተኛ ጥበቃ ማድረግ ተጀመረ
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው የደህንነት መረጃ እንዳመለከተው ከፍተኛ ወጪ የወጣባቸው ቻይና እና ሩሲያ ሰራሽ ራዳሮች ሰሞኑን በአካባቢው ተተክለዋል። መንግስት ማንኛውንም አይነት ድንገተኛ የአየር ወይም የሰርጎ ገቦች ጥቃት ለመከላከል ዘመናዊ ራዳሮችን ከመትከል በተጨማሪ የተወሰኑ የአጋዚ ክፍለ ጦር አባላት በአስችኳይ ወደ አካባቢው እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል። በፌደራል ፖሊስ ሲደረግ የነበረው ጥበቃ በመከላከያ ሰራዊት አባላት እንዲጠናከር ያደረገው መንግስት ፣ በሻለቃ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ <<በአባይ ወንዝ ላይ የተጀመረው ግድብ ከሐገራዊ ጠቀሜታው ይልቅ የገዥውን ፓርቲ የስልጣን እድሜ ለማራዘም የታለመና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ የሚደለቅ ከበሮ ነው>> አለ።
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰማያዊ ፓርቲ ፦<<እነሱ ከ አባቶቻቸው አይበልጡም፤ እኛም ከ አባቶቻችን አናንስም>> በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፤ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ወረራና ደባ መፈፀም የጀመረችው ኢትዮጵያ ዛሬ በአባይ ላይ ግድብ ለመስራት ከመነሳቷ እጅግ በርካታ አመታት በፊት ጀምሮ መሆኑን በመጥቀስ ሀገራችን ከግብፅም ሆነ ከሌሎች የተቃጣባትን ተደጋጋሚ ወረራዎች በመመከትና ጠላቶቿንም ድባቅ በመምታት ነፃነቷን ጠብቃ መኖሯ ለጠላቶቿ መራር የሆነ እውነት ነው ...
Read More »ኢሳትን ሲመለከቱ የነበሩ 60 ሰዎች መታሰራቸው ተሰማ
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በባሌ ሮቤ እና በጎባ ከተማ በቅርቡ ኢሳትን ሲመለከቱ የተገኙ ሰዎች ገናሌ እየተባለ በሚጠራው እስር ቤት ውስጥ መታሰራቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ግለሰቦቹ የተያዙት በተለያዩ ሰበቦች ቢሆንም ፍርድ ቤት ሲቀርቡ የሚቀርብባቸው ክስ ግን የተቃዋሚ ጣቢያ የሆነውን ኢሳትን ሲመለከቱ ተገኝተዋል የሚል ነው። ከታሰሩት መካከል ወጣቶች እና አረጋውያን እንደሚገኙበት የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የፕሬስ ነጻነት ተከብሮአል በሚባልባት ኢትዮጵያ ...
Read More »የአሜሪካ ኮንግረስ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ግንባታ ዙሪያ አስተያየቶችን ሊሰማ ነው
ሰኔ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ከታዋቂ የውጭ አገር ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ አስተያየቶችን እኤአ ሰኔ 20 ይሰማል። ከኢትዮጵያ የግንቦት7 ሊቀመንበር እና በበክኔል ዩኒቨርስቲ የኢኮኖሚክስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር ብርሀኑ ነጋ እና የሶሊዳሪቲ ሙቭመንት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ አስተያየታቸውን የሚሰጡ ሲሆን፣ ከውጭ አገር ሰዎች መካከል ደግሞ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ...
Read More »አንድነት ፓርቲ ግብጽና ኢትዮጵያ ከጸብ አጫሪነት ድርጊት እንዲቆጠቡ ጠየቀ
ሰኔ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ” ሁሉንም ነገር ለፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል የቆረጠ ፓርቲ የሀገርን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ መጣሉ የማይቀር ነው” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ” የግብጽና የኢትዮጵያ መንግሥት ከፀብ አጫሪ ድርጊት እንዲቆጠቡ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ከሚያበላሹ ፕሮፓጋንዳዎችን ከመንዛት እንዲታቀቡና ለዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጠረጴዛ ዙሪያ ንግግሮች ላይ እንዲያተኩሩ አሳስቦአል።” አባይን መጠቀም የኢትዮጵያ ተፈጥሮዊ መብት መሆኑ እንዲታወቅ፣ሁለቱ ሀገሮች የአባይን ጉዳይ ...
Read More »ከ 30 በላይ አረጋውያን ያለምንም ጥያቄ ታስረው ይገኛሉ ሲሉ ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ
ሰኔ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦሮምያ ክልል በጎሬ ወረዳ በንግድ ስራ ይተዳደሩ የነበሩ ከ30 በላይ አረጋውያን ካለፉት 8 ወራት ጀምሮ በእስር ላይ እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት ገልጸው፣ የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር እውነቱ በቀለ አረጋውያኑ መታሰራቸውን አምነዋል። አብዛኞቹ እስረኞች እድሜያቸው በ65 እስከ 80 መካከል ሲሆን፣ ብዙዎች እስሩን መቋቋም አቅቷቸው ለተለያዩ በሽታዎችና የመንፈስ ጭንቀት ተዳርገዋል። አረጋውያኑ በ2001 ዓም የከተማውን መንገድ ለመስራት ...
Read More »