ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝነት በማድረግ ላይ ያለው የልኡካን ቡድኑ መሪ ባርባራ ሎክብሂለር ጋዜጠኞች እና የሲቪክ ማህበረሰብ መሪዎች ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ የማምለክና የመሰብሰብ መብታቸውን በመጠቀማቸው መታሰራቸው ተገቢ ባለመሆኑ ሊፈቱ ይገባል ብለዋል። በኢትዮጵያ በስራ ላይ ያለው የጸረ ሽብርተኝነት ህጉ የፖለቲካ ልዩነትን ለማፈን እየዋለ መሆኑን የገለጸው የልኡካን ቡድኑ፣ የአገሪቱ ህገመንግስት ጥሩ ቢሆንም የፍትህ ስርአቱ አድሎአዊ መሆኑን ለመመልከት ...
Read More »የሥነ-ምግባር መኮንኖች ተወቀሱ
ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጽያ የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ትግሉን እንዲያግዙና የሥነ ምግባር ትምህርቶችን በየተቋሞቻቸው እንዲያሰርጹ በመንግስት መ/ቤቶች የተቋቋሙ የስነምግባር መከታተያ ክፍሎች በባለሙያዎች የተሠጣቸውን ተልዕኮ እየተወጡ አለመሆኑ ተሰምቷል፡፡ የሥነ-ምግባር መኮንን ተብለው በየመንግስት መ/ቤቶች የተቀመጡት እነዚሁ ባለሙያዎች በየተቋማቸው ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመዋጋት እንዳልቻሉ ሰሞኑን ባካሄዱት ስብሰባ ላይ በይፋ አምነው ተቀብለዋል፡፡ የፌዴራል የሥነምግባርና ጸረ ሙስና ኮምሽን በጠራው በዚሁ ስብሰባ ላይ ...
Read More »የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎቹ በተደጋጋሚ ያነሱትን የአስተዳደር መሻሻል ጥያቄ ሳይመልስ እስከ መጪው መስከረም አጋማሽ ድረስ እንዲዘጋ የአመራር ቦርዱ ወሰነ።
ሐምሌ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮሌጁ ተማሪዎች ያነሷቸውን የተለያዩ ጥያቄዎች ይዘው ወደ ፓትሪያሪኩ ልዩ ጽ/ቤት ከትናትና በስቲያ ያመሩ ቢሆንም ፤የስራ አመራር ቦርዱ ያለው ችግር እስኪጣራ ድረስ ኮሌጁ እንዲዘጋ መወሰኑን እና ተማሪዎችም ከሐምሌ 8 ቀን እስከ ሐምሌ 9 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ በደብዳቤ አሳውቋል። ተማሪዎቹ ከትናንት በስቲያ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንግበው ወደ መንበረ ፓትሪያሪክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አቅንተው- ...
Read More »የደብረብርሀን ነዋሪዎች ፍትህ አጣን አሉ
ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ሺዋ ዞን የደብረ ብርሃን ከተማ ኗሪዎች የመንግስት ሹማምንት የሚያደርሱባቸውን በደሎች በመዘርዝር ለመንግስት አቅርበዋል። ክልሉ በቅርቡ በጀመረው የህዝብ ብሶቶችን መስሚያ መድረኮች ላይ ነዋሪዎች ” በአደባባይ እንደበደባለን ፤እንታሰራለን፤ በአገራችን በሰላም ለመኖር አልቻልንም” ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡በተደጋማሚ በሚደርስባቸው በደል አገር ጥለው የሚሰደዱ ዜጎች መበራከታቸውንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ሹመት የሚሰጠው በዘመድ ዝማድ ነው ያሉት አንድ ተናጋሪ ፣ ...
Read More »በኦጋዴን 500 ሰዎች መታሰራቸው ተዘገበ ኦጋዴን ፕሬስ ቱደይ የተሰኘው ድረገጽ እንደዘገበው
ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በያዝነው ወር ብቻ 500 ሲቪሎች፣ ከጅጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ዋርዴር እና ጎዴ በደህንነት ሀይሎች ተወስደው እስር ቤት ገብተዋል። አዲሱ የእስር ዘመቻ የተከፈተው በቅርቡ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናትና ወታደሮች ከድተው እጃውን ለኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ከሰጡ በሁዋላ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። ከታሰሩት መካከል በርካታ ህጻናትና ሴቶች ሲገኙበት፣ አብዛኞቹም ጅጅጋ አካባቢ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ መታሰራቸው ታውቋል። ሙሀመድ ...
Read More »በአማራ ክልል በ12 ወረዳዎች ባለፉት 10 አመታት 13 ሺ 64 ሰዎች ከነፍስ ግድያ ወንጀል ጋር በተያያዘ ተገድለዋል
ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- 11 ሺ 93 ስዎች ከነፍስ ግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ተርፈዋል፡፡ የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ባካሄደው የዳሰሳ ጥናት በ10 አመታት ውስጥ ከነፍስ ግድያ ጋር በተያያዘ 13 ሺ 64 ሰዎች ሲገደሉ ፣ 11 ሺ 93 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል። በጥናቱ ውስጥ እንደተመለከተው ድብደባ መፈጸም ቀዳሚነቱን ሲይዝ አካል ማጉደል እና ነፍስ ማጥፋት ወንጀሎች ተከታታዮችን ደረጃዎች ...
Read More »የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ከናይጀሪያ ለቀቁ
ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአፍሪካ ህብረት በጤና ጉዳይ ላይ ለመመካከር በናይጀሪያ ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የተገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ሰብሰባቸውን ሳይጨርሱ ወደ አገራቸው የተመለሱት ፣ አለማቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የናይጀሪያ መንግስት ይዞ እንዲያስራቸው አቤቱታውን ለፍርድ ቤት ካቀረበ በሁዋላ ነው። ፕሬዚዳንቱ ሰኞ እለት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ሲጠበቅ፣ በድንገት አገሪቱን ለቀው መውጣታቸው ታውቋል። ፕሬዚዳንት በሽር ናይጀሪያ ሲገቡ ...
Read More »በቂልንጦ እስርቤት የእሰረኞች ደም በድብደባ እንደጎርፍ መፍሰሱን የአይን እማኞች ተናገሩ
ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርብ ፣ ሀምሌ 6 2005 ዓም በእነ አቶ ተሻለ ኮርኔ መዝገብ የተከሰሱ 69 የኦሮሞ ተወላጆች ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባቸው፣ ፍርድ ቤት የሚወስዳቸው ፖሊስ ያጣሉ። በቅጽል ስሙ ሻእቢያ እየተባለ የሚጠራውን የእስር ቤቱን ሀላፊ ሲጠይቁት ቀጠሮአቸው ለ4 ወር መራዘሙን ይነግራቸዋል። እስረኞቹም ” ከ2 አመታት በላይ የላፍትህ ታስረን በመጨረሻ ብይን በሚሰጥበት ወቅት ለ4 ወራት ...
Read More »በአዲስ አበባ የአንድነት ፓርቲ አባሎች እየታሰሩ ነው
ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በደሴና እና በጎንደር የተሳኩ የተቃውሞ ሰልፎችን ባካሄደ ማግስት ከ30 በላይ አባሎቹ በዋና ከተማዋ የተቃውሞ ፊርማ ሲያሰባስቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል። ባለፉት ሳምንታትትም በተመሳሳይ መንገድ የታሰሩ እና የፍርድ ቤት ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ አባላት አሉ። አንድነት ፓርቲ ለ3 ወራት በሚቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በዋና ዋና ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን ከማካሄድ ባሻገር ቤት ውስጥ ስብሰባዎችንና ...
Read More »የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች አመጽ እንደቀጠለ ነው።
ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ሕዝበ ክርስቲያኑ ከጎናቸው እንዲቆም በመጠየቅ ትናንት በአመታዊ የሥላሴ ክብረ በዓል ላይ መፈክሮችን ሲያሰሙ ውለዋል። ተማሪዎቹ ሲያሰሙዋቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል፦የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅን መዝጋት ታሪክን ማጥፋት/ማበላሸት ነው!፣የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ችግራችንን ይመልከት!፣ሙስናንና ኑፋቄን የሚያደቅ ክንድ አለን!የምንማረው በምእመናን ብር ነው፡፡ ሌቦች ሆይ፣ እጃችኹ ይሰብሰብ! “የሚሉት ይገኝበታል። እንዲሁም፦”ልጆቹን የማይጠይቅ አባት ...
Read More »