በኦጋዴን 500 ሰዎች መታሰራቸው ተዘገበ ኦጋዴን ፕሬስ ቱደይ የተሰኘው ድረገጽ እንደዘገበው

ሐምሌ ፱( ዘጠኝ )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-በያዝነው ወር ብቻ 500 ሲቪሎች፣ ከጅጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ዋርዴር እና ጎዴ በደህንነት ሀይሎች ተወስደው እስር ቤት ገብተዋል።

አዲሱ የእስር ዘመቻ የተከፈተው በቅርቡ በርካታ የመንግስት ባለስልጣናትና ወታደሮች ከድተው እጃውን ለኦጋዴን ነጻ አውጭ ድርጅት ከሰጡ በሁዋላ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።

ከታሰሩት መካከል በርካታ ህጻናትና ሴቶች ሲገኙበት፣ አብዛኞቹም ጅጅጋ አካባቢ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ መታሰራቸው ታውቋል።
ሙሀመድ ሂሮ የተባለ የአካባቢው የኤች አይቪ ኤድስ መቆጣጠሪያ ሀላፊ እና ስዊድን የተወለደ ኢትዮጵያዊ  ይገኙበታል።

የአለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ና የመገናኛ ብዙሀን በኦጋዴን አካባቢ የሚካሄደውን የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለመታዘብ እንዳይችሉ መታገዳቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ መንግስት መጪውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በጅጅጋ ለማክበር ማሰቡን ተከትሎ በቅርቡ በርካታ አርቲስቶችና ጋዜጠኞች ጅጅጋንና አካባቢውን እንዲጎበኙ መደረጋቸው ይታወሳል።