በአዲስ አበባ የአንድነት ፓርቲ አባሎች እየታሰሩ ነው

ሐምሌ ፰( ስምንት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በደሴና እና በጎንደር የተሳኩ የተቃውሞ ሰልፎችን ባካሄደ ማግስት ከ30 በላይ አባሎቹ በዋና ከተማዋ የተቃውሞ ፊርማ ሲያሰባስቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ባለፉት ሳምንታትትም በተመሳሳይ መንገድ የታሰሩ እና የፍርድ ቤት ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ ያሉ አባላት አሉ።

አንድነት ፓርቲ ለ3 ወራት በሚቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ  በዋና ዋና ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎችን ከማካሄድ ባሻገር ቤት ውስጥ ስብሰባዎችንና እና 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ፊርማ ያሰባስባል።

ፓርቲው በደሴና በጎንደር ያደረገው ተቃውሞ ለፓርቲው አባላት ከፍተኛ መነቃቃት እንደፈጠረ አንዳንድ አባላቱ ተናግረዋል።