ከፍተኛው ፍርድ ቤት ባለ አምስት ኮከብ የሆነውን ኢንተርኮንቴነንታል ሆቴል እና ሌሎች ህንጻዎችን ከሙስና ከተጠረጠሩ ባለሀብቶች ተወስደው በገለልተኛ ወገን እንዲተዳደሩ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

ነሀሴ ፩ ቀን ፩፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍርድ ቤቱ በትላንትናው እለት የፌደራሉ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቢ ህግና የተጠርጣሪ ጠበቆች በጋራ ተስማምተው ንብረቱን የሚያስተዳድር አካል እስከ መስከረም 22 ቀን 2006 ዓ.ም. እንዲያቋቁሙ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ ንብረታቸው በገለልተኛ አካል እንዲተዳደር ፍርድ ቤት የወሰነባቸው ንብረትነቱ የአቶ ሰማቸው ከበደ የሆነው ባለ 5 ኮከብ ኢንተርኮንተነንታል ሆቴል እና ዲ ኤች ሲሜክስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንዲሁም ...

Read More »

መንግስት ሰሞኑን የሚከበረውን የኢድ አልፈጥር በዓል በመግቢያ ካርድ እንዲሆን ያስተላለፈውን መመሪያ በልዩ ትዕዛዝ እንዲቆም ማድረጉን ለኢሳት ከአዲስ አበባ የደረሱ መረጃዎች አመለከቱ

ነሀሴ ፩ ቀን ፩፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት በትላንትናው ዕለት የህዝበ ሙስሊሙን የተቃውሞ ስልፍ በመፍራት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚከበረውን በአል በልዩ የመግቢያ ካርድ እንዲሆን በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የመግቢያ ካርዶችን እንዳዘጋጀ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይሁንና ዛሬ የፌደራል መረጃና ደህንነት መስሪያ ቤት ልዩ ትዕዛዝ በመስጠት ሁኔታው እንዲቆም ማድረጉ ታውቋል፡፡ የፌደራል መረጃና ደህንነት ተወካዮች በአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተማ የሚገኙ የመጅሊስ አባላትን፣ ካድሬዎችና የደህንነት ሰዎችን ...

Read More »

ጉግል የአበበ ቢቂላን ፎቶ በፊት ገጹ ላይ በማስቀመጥ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አስበውት እንዲውሉ አደረገ

ነሀሴ ፩ ቀን ፩፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የታዋቂው የአበበ ቢቂላ 81ኛ ዓመት የልደት በዓል በማስመልከት ታዋቂው የድህረ ገጽ ቋት የሆነው ጉግል የአበበ ቢቂላን ፎቶ በፊት ገጹ ላይ በማስቀመጥ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አስበውት እንዲውሉ አደረገ፡፡ የጉግል አካል የሆነውና ጉግል በአርማነት የሚጠቀመው ጉግል ዶድል ድረ ገጽ ላይ የመጀመሪያው የሰብ ሰሀራ ኦሎምፒክ አሸናፊ የሆነው አበበ ቢቂላ እንደዚህ አይነት ክብርን ሲያገኝ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አትሌት ...

Read More »

120 ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራውያንን የያዘች መርከብ በማልታና ጣሊያን መንግሥታት ወደ ግዛቴ አላስገባም በሚል ውዝግብ በእንግልት ላይ ናቸው

ነሀሴ ፩ ቀን ፩፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሁኔታው ያሳሰበው የአውሮፓ ህብረት የማልታ መንግስት ያለምንም መዘግየት በእንግልት ላይ የሚገኙትን ሰዎች ወደ ድንበሩ ገብተው ሰብአዊ መብት እንዲያገኙ ጠይቋል፡፡ ማረፊያ ያጣችው መርከብ በውስጧ አራት እርጉዝ ሴቶችን፣ አንድ የተጎዳች ሴትና የ5 ወር ህጻን መያዟን የአውሮፓ ህብረት አስታወቋል፡፡ በላይቤሪያ መንግስት ንብረትነት የተመዘገበችው ጀልባ በግሪካዊ ኩባንያ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረች ሲሆን 120 ኢትዮጵያውያኑንና ኤርትራዊያኑን በሊቢያ ቀይ ባህር ...

Read More »

በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ የተገጣጠሙ የህዝብ አውቶብሶች አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተበላሹ

በቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ የተገጣጠሙ የህዝብ አውቶብሶች አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ60 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተበላሹ ሐምሌ ፴(ሠላሳ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ያመረታቸው እና የገጣጠማቸው የከተማ እና  አገር አቋራጭ  አውቶብሶች አመት ሳይሞላቸው ለጉዳት ተደርገዋል። አውቶብሶቹ ከግማሽ በላይ አካላቸው በሀገር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የተመረተ ቢሆንም በውጭ ሃገር ግዥ የተፈፀመው የሞተር አካላቸው ግን ምንም ...

Read More »

መንግስት በምእራብ አርሲ ዞን የተገደሉትን ሙስሊሞች ቁጥር መቀነሱን የአካባቢው ሰዎች ገለጹ

ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምእራብ አርሲ ዞን በኮፈሌና አካባቢዋ የፌደራል ፖሊሶች በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ በወሰዱት እርምጃ 3 ሰዎች መገደላቸውና 7 ሰዎች መቁሰላቸውን የኦሮምያን ፖሊስ በመጥቀስ የመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ቢዘግቡም የኢሳት ምንጮች በበኩላቸው የሟቾች ቁጥር ከ18 እስከ 25 ይደርሳል ይላሉ። በአካባቢው የሚገኝ አንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የሟቾችን ቁጥር 18 መሆኑን ሲገልጽ፣ ወደ ኮፈሌ እና ዋቢ ከተሞች ለመግባት ሙከራ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በባህር ዳር እና አርባ ምንጭ ያካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ

ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባህርዳር ስለነበረው ሰልፍ በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ሲገልጽ ” ለ ስምንት አመታት የተዘጉ ልሳኖች ተከፈቱ ፤ መከራና ስቃይ ፣ የኑሮ ውድነት ያንገበገባቸው ፤ስራ አጥነት ያማረራቸው ፤ የፍትህ እጦት ያስነባቸው ወገኖች በአደባባይ ተገኝው ድምፃቸውን አሰሙ ብሎአል። • የታሰሩ የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ይፈቱ • መንግስት ህገ-መንግስቱን ያክብር • መንግስት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ያቁም! • ...

Read More »

በሲጃራ ሙስና የተጠረጠሩት የትንባሆ ሞኖፖል ኃላፊ ነፃ መባላቸውን የጸረ-ሙስና ኮሚሽን ተቃወመ።

ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፀረ-ሙስና ኮሚሽን- የብሔራዊ ትምባሆ ሞኖፖል ድርጅት የሥራ ኃላፊ በተጠረጠሩበት የእምነት ማጉደል ወንጀል በፍርድ ቤት በነፃ መሰናበታቸውን በመቃወም- ይግባኝ እንደሚጠይቅ አስታወቀ። ሪፖርተር እንደዘገበው ፤የብሔራዊ ትምባሆ ሞኖፖል ድርጅት ያለቀላቸው ምርቶች ግምጃ ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ በሻና 787,531.50 ሳንቲም በሚያወጣ 210 ካርቶን ኒያላ ሲጋራ በመሰወር ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር፡፡ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ...

Read More »

በአዲስ አበባና በአንዳንድ የክልል ከተሞች አለመረጋጋት እየታየ ነው

ሐምሌ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የፌደራል ፖሊስ አባላት በአዲስ አበባና በአንዳንድ የክልል ከተሞች በብዛት መታየታቸውን ተከትሎ በከተሞች የሚታየው አለመረጋጋት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሄዱን ዘጋቢዎቻችን ገልጸዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ዘወትር አርብ የሚደረገውን የጁመአ ስግደት አስታኮ የተቃውሞ ድምጹን የሚያሰማ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስድ መዛቱ ይታወቃል። የፖሊስን መግለጫ ተከትሎ የድምጻችን ይሰማ አመራሮች ሌሊቱን የተቃውሞ መርሀግብሩን መሰረዛቸውን ...

Read More »

በአፋር አንድ ሰው በፌደራል ፖሊሶች ተገደለ

ሐምሌ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቡሪሞዲያቶ ወረዳ አባ በርሀቤ ቀበሌ አቶ ሀሰን በረከት የተባሉ ነዋሪ የተገደሉት አንድ ሾፌር የቤት እንስሶቻቸውን መግደሉን ተከትሎ በተፈጠረ ውዝግብ መሀል ነው። አቶ ሀሰን ካሳ እንዲሰጣቸው ሹፌሩን በሚጠይቁበት ወቅት ጉዳዩን በትክክል ያልተረዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት በግለሰቡ ላይ ተኩስ ከፍተው ገድለውታል። በቅርቡ በአፋር እና በፌደራል ፖሊሶች መካከል የተጀመረው ግጭት ለግለሰቡ መገደል ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ተብሎአል። ...

Read More »