ጉግል የአበበ ቢቂላን ፎቶ በፊት ገጹ ላይ በማስቀመጥ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አስበውት እንዲውሉ አደረገ

ነሀሴ ፩ ቀን ፩፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የታዋቂው የአበበ ቢቂላ 81ኛ ዓመት የልደት በዓል በማስመልከት ታዋቂው የድህረ ገጽ ቋት የሆነው ጉግል የአበበ ቢቂላን ፎቶ በፊት ገጹ ላይ በማስቀመጥ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች አስበውት እንዲውሉ አደረገ፡፡

የጉግል አካል የሆነውና ጉግል በአርማነት የሚጠቀመው ጉግል ዶድል ድረ ገጽ ላይ የመጀመሪያው የሰብ ሰሀራ ኦሎምፒክ አሸናፊ የሆነው አበበ ቢቂላ እንደዚህ አይነት ክብርን ሲያገኝ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አትሌት ነው፡፡

በ1960 በሞስኮ በባዶ እግሩ በመሮጥ 42 ኪሎ ሜትርን ያሸነፈው አትሌት አበበ ቢቂላ ከሞተም በኋላ ቢሆን የአለም ህዝብ ትልቅ ክብርን እየሰጠው ይገኛል፡፡

ጉግል የአንድ ደቂቃ ከ16 ሰኮንድ የሆነ ቪድዮም የልደት በአሉን በማስመልከት የሰራለት ሲሆን ብዙ ተመልካቾች በመጎብኘት ላይ ሲሆኑ አድናቆታቸውን በድረ ገጹ ላይ በማስፈር ላይ ይገኛል፡፡

ጉግል ባሰራጨው ቪድዮ ላይ የአትሌት አበበ ቢቂላ ስራዎችና የህይወት ታሪኩ ጭምር የተካተቱ ሲሆን አዲሱ ትውልድም አበበ ቢቂላን ዳግም እንዲያስበው አድርጓል፡፡