በአፋር አንድ ሰው በፌደራል ፖሊሶች ተገደለ

ሐምሌ ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በቡሪሞዲያቶ ወረዳ አባ በርሀቤ ቀበሌ አቶ ሀሰን በረከት የተባሉ ነዋሪ የተገደሉት አንድ ሾፌር የቤት እንስሶቻቸውን መግደሉን ተከትሎ በተፈጠረ ውዝግብ መሀል ነው። አቶ ሀሰን ካሳ እንዲሰጣቸው ሹፌሩን በሚጠይቁበት ወቅት ጉዳዩን በትክክል ያልተረዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት በግለሰቡ ላይ ተኩስ ከፍተው ገድለውታል። በቅርቡ በአፋር እና በፌደራል ፖሊሶች መካከል የተጀመረው ግጭት ለግለሰቡ መገደል ምክንያት ሳይሆን አይቀርም ተብሎአል።

በትናንትናው እለትም በፌደራል ፖሊስ አባላት እና በአፋሮች መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመልክቷል።