ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የሚመሩት 33ኛው የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ታወቀ። ( ኢሳት ዜና መስከረም 02 ቀን 2011 ዓ/ም ) ኤርትራ ዳግም ወደ ኢጋድ አባልነት የምትመለስበት ጉዳይ ከስብሰባው አጀንዳዎች አንዱ መሆኑ ታወቀ። የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የሚመሩት የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት /ኢጋድ/ 33ኛው የመሪዎች ስብሰባ በመዲናችን አዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን በሶስት አበይት ጉዳዮች ላይ ...
Read More »የኢትዮጵያና የጣሊያን አውሮፕላኖች ለጥቂት ከግጭት ተረፉ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 1/2011)የኢትዮጵያና የጣሊያን አውሮፕላኖች በኬንያ የአየር ግዛት ውስጥ ለጥቂት ከግጭት መትረፋቸው ተዘገበ። የኬንያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች በኢትዮጵያ የነበረው የአየር ትራፊኮች አድማ ያስከተለው ነው በማለት ተቃውሞ ቢያቀርቡም ክስተቱ ሊያጋጥም የነበረው በኬንያ የአየር ክልል ውስጥ በመሆኑ ውዝግብ ቀስቅሷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪ ከፍታውን በመጨመር ከጣሊያኑ አውሮፕላን ጋር ባይተላለፍ ኖሮ በአቪየሽን ታሪክ ዘግናኙ አደጋ ይከሰት እንደነበር ዘገባው አመልክቷል። ዘግይቶ የወጣው ይህ መረጃ ...
Read More »የሜቴክ ሃላፊዎች በፈጸሙት ዝርፊያ ላይ ምርመራው እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 1/2011) የመሰረታዊ ብረታብረት ኮርፖሬሽን ሜቴክ ሃላፊዎች በሃገሪቱ ሃብት ላይ በተለይም በሕዳሴው ግድብ ያካሄዱትን የተደራጀ ዘረፋ በተመለከተ ምርመራ መቀጠሉ ታወቀ። በዘረፋው ሒደት ተዋናይ የሆኑ የሌሎች ተጨማሪ ደላሎችና ግብረ አበሮች ዝርዝር መውጣት ጀመሯል። የሜቴክ ሃላፊዎች በዘር ተደራጅተው በሃገሪቱ ሃብት ላይ በሚያደርጉት የተደራጀ ዘረፋ በደላላነት የተሳተፉና በዝርፊያው ተባባሪ የነበሩ ግለሰቦች ዝርዝር በመውጣት ላይ ይገኛል። በድሬደዋ ከተማ የባለ ኮከብ ሆቴል ባለቤትና የመከላከያ ...
Read More »የወረኢሉ ወረዳ ህዝብ ያለመንግስት አስተዳደር መቀመጡን ገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 1/2011) በደቡብ ወሎ ዞን ወረኢሉ ወረዳ ህዝብ ያለመንግስት አስተዳደር ከአንድ ወር በላይ እንዳለፈው ተገለጸ። ህዝቡ አስተዳዳሪዎቹን ከስልጣን ወርደው ለህግ ይቅረቡ የሚል ጥያቄ ማንሳቱን ተከትሎ በተፈጠረ ውዝግብ የወረኢሉ ወረዳ አመራሮች ሸሽተው ደሴ መግባታቸውንም የደረሰን መረጃ ያመለክታል። አመራሮቹ ህዝብን የበደሉ፣ የለውጡ እንቅፋት የሆኑ ናቸው በሚል የተነሳው ተቃውሞ መቀጠሉም ታውቋል። አስተዳዳሪ የሌላት የወረኢሉ ወረዳ በህዝብ በተወጣጣ አመራር እየተመራች መሆኑን የኢሳት ምንጮች ...
Read More »የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች አዲሱን አመት ከሁለቱ ሃገራት ወታደሮች ጋ አከበሩ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 1/2011) የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ አዲሱን አመት በቡሬና ዛላ አንበሳ ግንባር ከሁለቱ ሃገራት ወታደሮች ጋ አከበሩ። የሁለቱም ሃገራት ወታደሮች በአንድነት በመቆም ላለፉት 20 አመታት የዘለቀውን ፍጥጫ አስወግደዋል። የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ዛሬ መስከረም 1 ቀን 2011 አመተምህረት በቅድሚያ ወደ ቡሬ ግንባር፣ከዚያም ወደ ዛላ አንበሳ በማቅናት አዲሱን አመት ...
Read More »የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሪዎች በሁለቱ አገራት ድንበሮች ላይ ተገኝተው አዲሱን አመት በማክበር ድንበሮችን ከፈቱ
የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መሪዎች በሁለቱ አገራት ድንበሮች ላይ ተገኝተው አዲሱን አመት በማክበር ድንበሮችን ከፈቱ ( ኢሳት ዜና መስከረም 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) ለላፉት 20 ዓመታት የአዲስ ዓመት በአልን በምሽግ ሲያሳልፉ የነበሩት የሁለቱ አገራት ወታደሮች ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድና ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ በተገኙበት በቡሬ እና በዛላንበሳ ግንባር በአሉን አክብረዋል። ቡሬ ግንባር ያለውን ድንበር ከከፈቱ በሁዋላ መሪዎቹ ወደ ዛላንበሳ ግንባር በማምራት በዓሉን ...
Read More »የኢትዮጵያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከአየር ላይ ግጭት ተረፈ
የኢትዮጵያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከአየር ላይ ግጭት ተረፈ ( ኢሳት ዜና መስከረም 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) ዘ ኢስት አፍሪካን እንደዘገበው ባለፈው ረቡዕ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ኢት 858፣ ቦይንግ 737-800 ከጣሊያኑ የሌዢር ኤርላይን ኒዮስ ቦይንግ 767-306 R የበረራ ቁጥር NOS 252 ጋር በኬንያ ሰማይ ላይ ለመጋጨት ሲቃረብ በአንድ ደቂቃ ልዩነት ተርፏል። አደጋ ተፈጥሮ ቢሆን ኖሮ በአለም አሰቃቂው የአውሮፕላን አደጋ ...
Read More »ሩስያ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ ታላቅ የተባለ የጦር ልምምድ ማድረግ ጀመረች
ሩስያ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ ታላቅ የተባለ የጦር ልምምድ ማድረግ ጀመረች ( ኢሳት ዜና መስከረም 01 ቀን 2011 ዓ/ም ) 300 ሺ የሚጠጉ የሩስያ ወታደሮች በምስራቅ ሳይቤሪያ በጀመሩት ወታደራዊ ልምምድ፣ 3200 ወታደሮችን የላከቸው ቻይናና ሞንጎልያም ተካፍለዋል። ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በሁዋላ በአይነቱ ልዩ ነው የተባለው ፣ ቮስቶክ 2018 የተባለ ስያሜ የተሰጠው ወታደራዊ ልምምድ አላማው የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን አገሮች ወይም ኔቶ ...
Read More »የደቡብ ሱዳን አውሮፕላን ተከስክሶ 19 ሰዎች ሞቱ
(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 5/2010) አንድ አነስተኛ የደቡብ ሱዳን አውሮፕላን ተከስክሶ የ19 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ አንዲት ሕጻንን ጨምሮ ሶስት ሰዎች ከአደጋው መትረፋቸው ታወቀ። ወንዝ ላይ ተከሰከሰ የተባለው አውሮፕላን ከደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ይሮል ወደተባለ ሌላ የደቡብ ሱዳን ከተማ በመጓዝ ላይ እንደነበሩ ዘገባው አመልክቷል። የደቡብ ሱዳን የማስታወቂያ ሚኒስትር ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ አንድ ሕጻንና ረዳት አብራሪውን ጨምሮ ሶስት ሰዎች በሕይወት ተርፈዋል። በአደጋው ...
Read More »በባንግላዴሽ 140 ኪሎ ግራም የሚመዝን የኢትዮጵያ ጫት ተያዘ
(ኢሳት ዲሲ–ጳጉሜ 5/2010) በባንግላዴሽ ዳካ አውሮፕላን ማረፊያ 140 ኪሎ ግራም የሚመዝን የኢትዮጵያ ጫት በቁጥጥር ስር ዋለ። ዴይሊ ስታር ከዳካ እንደዘገበው የባንግላዴሽ የጉምሩክና የጸጥታ ሰራተኞች በትብብር ትላንት በቁጥጥር ስር ያዋሉት 140 ኪሎግራም የኢትዮጵያ ጫት ከህንድ ወደ ባንግላዴሽ መጓዙም ተመልክቷል። ዴይሊ ስታር የኢትዮጵያ ማሪዋና በሚል የገለጸው ጫት ለምርመራ መላኩም ተመልክቷል። ጫቱ ከኢትዮጵያ ወደ ህንድ እንዴት እንደሔደ የተገለጸ ነገር የለም። ከጥቂት ሳምንታት ቀደም ...
Read More »