ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎች እንደገለጹት ላለፉት 25 አመታት ከኖሩበት ቤት በጉልበት ተነሱ በመባላቸው ሜዳ ላይ ለመውደቅ ተገደዋል። ነዋሪዎቹ ስሜታቸውን በከፍተኛ ሀዘን እየገለጹ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል። የመንግስትን እርምጃ በመቃወማቸው የተወሰኑ ሰዎች የደረሱበት አለመታወቁንም ነዋሪዎች ገልጸዋል። በአዳማም በተመሳሳይ መንገድ ከ25 ሺ በላይ ህዝብ ቤት አልባ መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል።
Read More »ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ሕዝብ ያዋጣው 5.7 ቢሊየን ብር ነው ተባለ
ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት ዓመታት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ከሕዝብ የተዋጣው ገንዘብ ከ10 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑ በመንግስት የመገናኛ ብዙሀን ሲነገር ቢቆይም አንድ ባለስልጣን ግን ትክክለኛው አሀዝ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ነው ሲሉ ተናግረዋል። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ጽ/ቤት የአቶ በረከት ስምኦን ምክትል የሆኑት አቶ ዛዲግ አብርሃን ጠቅሶ መንግስታዊው አዲስ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እጣ ፋንታ አልታወቀም
ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ረቡዕ ቦር እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የታየውን ከፍተና ግጭት ተከትሎ በአካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ አልታወቀም። በርካታ ደቡብ ሱዳናውያን በመንግስት ደጋፊና ተቃዋሚዎ ታጣቂዎች መገደላቸውን ሲኤን ኤን የዘገበ ሲሆን፣ በአካባቢው የሚኖሩ ከ1 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን እጣ ፋንታ እስካሁን በውል አለመታወቁንም ከአካባቢው ሸሽተው ወደ ኡጋንዳ ድንበር የደረሱ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ኢትዮጵያውያኑ ...
Read More »የፌዴሬሽን ምክርቤት በአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ ካሳ ተክለብርሃን የሚመራው የፌዴሬሽን ምክርቤት ፍ/ቤት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በሙስና ወንጀል በተከሰሱት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሰልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት የፊታችን ሰኞ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ታወቀ፡፡ የፌዴራሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሙስና ወንጀል በመጠርጠር በሶስት የተለያዩ መዝገቦች ስር ከባለስልጣናትና ባለሀብቶች ጋር ክስ የመሰረተባቸው አቶ መላኩ ...
Read More »በደቡብ ሱዳን ተገደው የተደፈሩ 4 ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጁባ ገቡ
ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በደቡብ ሱዳን የተነሳውን የእርስ በርስ ግጭት ተከትሎ የተደፈሩ 4 ሴቶች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሆስፒታል በሚገኝበት ጁባ ደርሰው ምርመራ እየተደረገላቸው ነው። ሴቶቹ መደፈራቸውንና ሆስፒታል መግባታቸውን ኢሳት ለማረጋገጥ የቻለ ሲሆን፣ ሴቶቹ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ያደረገው ጥረት በመስመር ግንኙነት የተነሳ ሊሳካለት አልቻለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ከውጭ ጉዳይ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤቱን እንዲለቅ ትእዛዝና ማስጠንቀቂያ ተሰጠው::
ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰማያዊ ፓርቲ ግንፍሌ አከባቢ የሚገኘውን እና በጽ/ቤትነት የሚጠቀምበትን ቢሮ በአስቸኳይ እንዲለቅ ትዕዛዝ ደረሰው። በዛሬው እለት ከሰኣት በኋላ አቶ ሄኖክ የተባሉ አከራዩ ከአራት ግለሰቦች ጋር በመምጣት ፦”ቤቱን ለነዚህ ግለሰቦች ስለሸጥኩላቸው እንድትለቁላቸው” ሲሉ ከውል ውጪ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ቤቱን ገዛሁት የሚለው ግለሰብ በበኩሉ፦”ቤቱን የኔ ስለሆነ በአስቸኳይ እንድትለቁልኝ፣ ካልሆነ የራሴን እርምጃ እወስዳለሁ” ሲል አመራሮቹ ...
Read More »ኦብነግ ከመንግስት ሀይሎች ጋር መዋጋቱ ተዘገበ
ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኦጋዴን ፕሬስ እንደዘገበው የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር ከመከላከያ ሰራዊት እና ከልዩ ሚሊሺያዎች ጋር ባደረገው የተኩስ ልውውጥ 70 የኢትዮጵያ ወታደሮች እንደተገደሉ በእርሱ ወገንም የተወሰኑ ታጣቂዎች እንደሞቱ ገልጿል። እንደ ጋዜጣው ዘገባ 3 የመንግስት ወታደራዊ አዛዦችም ተገድለዋል። መንግስት አስተያየተቱን ባይሰጥም ልዩ ሚሊሺያ የሚባለው ሀይል የኦብነግን ወታደራዊ አዛዥ መግደሉን ለጋዜጣው እንደገለጹለት ተዘግቧል። በደጋሀቡር፣ ኮራሄና ፊክ ...
Read More »70 ድርጅቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተከሰሱ
ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፋና እንደዘገበው በአዲስ አበባ በግሉ ዘርፍ ከተሰማሩ 470 ቀጣሪ ድርጅቶች መካከል 70 ዎቹ ሰዎችን በህወጥ መንገድ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን ያዘዋውራሉ ተብሎ ክስ ተመስርቶባቸዋል። የሰራተኛና የማህበራዊ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት ኤፍሬም ግዛው ፣ በድርጅቶች ላይ ክስ ለመመስረት አስፈላጊው መረጃ ሁሉ ተሰብስቧል። የአዲስ አበባ መስተዳድር በበኩሉ እርምጃው በሌሎች ድርጅቶችም ላይ እንደሚቀጥል ...
Read More »የትምባሆ ፍላጎት መቀነስና የአቅርቦት ቁጥጥር ሥርዓት አገራት እንዲዘረጉ የሚያስገድደውን ዓለምአቀፉ የትምባሆ ቁጥጥር ኮንቬንሽን ረቂቅ አዋጅ በፓርላማ ሊጸድቅ ነው፡፡
ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ፓርላማው እ.ኤ.አ በ2003 በጄኔቭ የወጣው ኣለምአቀፍ የጤና ድርጅት የትምባሆ ቁጥጥር ኢትዮጽያ ፈራሚ አገር የነበረች ሲሆን ይህንን ለማጽደቅ ረቂቅ ሕግ በዛሬው ዕለት ለፓርላማው ቀርቦለት በጉዳዩ ላይ ከተወያየ በሃላ ለሚመለከተው ኮሚቴ መርቶታል፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ በኢትዮጽያ በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል 8በመቶ ያህሉ የትምባሆ ምርቶችን እንደሚጠቀሙ ጥናቶችን ጠቅሶ አስቀምጧል፡፡ በተጨማሪም ...
Read More »በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ አባላት በእስር ቤት ስቃይ እንደተፈጸመባቸው ገለጹ
ታህሳስ ፲፫( አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የስነልቦናዊ እና አካላዊ ስቃይ አድርሰውብናል የሚሉት በእስር ላይ የሚገኙት የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ የደረሱባቸውን በደሎች ዘርዝርው አቅርበዋል። ” ከአስራ አራት ሰአት በላይ ያለ እረፍት ቀጥ ብለን እንድንቆም በማድረግ፣ ጀርባችን ሰንበር እስኪያወጣ እና እስኪገሸለጥ ራቁታችንን በሽቦ በመግረፍ፣ በሰንሰለት በማሰር እና አይናችንን በጨርቅ በመሸፈን የውስጥ እግራችን ...
Read More »