70 ድርጅቶች በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ተከሰሱ

ታህሳስ ፲፬( አስራ አራት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :- ፋና እንደዘገበው በአዲስ አበባ በግሉ ዘርፍ ከተሰማሩ 470 ቀጣሪ ድርጅቶች መካከል 70 ዎቹ ሰዎችን በህወጥ መንገድ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎችን ያዘዋውራሉ ተብሎ ክስ ተመስርቶባቸዋል።

የሰራተኛና የማህበራዊ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት ኤፍሬም ግዛው ፣ በድርጅቶች ላይ ክስ ለመመስረት አስፈላጊው መረጃ ሁሉ ተሰብስቧል።

የአዲስ አበባ መስተዳድር በበኩሉ እርምጃው በሌሎች ድርጅቶችም ላይ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ታገዱ የተባሉት ድርጅቶች በስም አልተጠቀሱም። አስተያየቱን የተጠየቀው የአዲስ አበባው ዘጋቢ መንግስት በሳውድ አረቢያ የተከሰተውን ችግር ተከትሎ እርምጃ እየወሰደ ቢመስልም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ በ70 ድርጅቶች ላይ ምርመራ አድርጎና ማስረጃ ሰብስቦ ለመጨረስ የሚችል አይመስለኝም ብሎአል።  የገዢው ፓርቲ ኩባንያዎች የማይፈልጉዋቸውን ድርጅቶች ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ እንዲህ አይነቱን ዘዴ ሊጠቀሙ እንደሚችልም ያለውን ስጋት ገልጿል።