የፈረንጆቹ አዲስ ዓመት እየተከበረ ነው

ታህሳስ ፳፪( ሃያ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎርጎሪያን ካላንደር የሚቆጥሩ አገሮች አዲስ ዓመታቸውን በልዩ ድምቀት እያከበሩት ይገኛሉ። በጎርጎሪያን ቀመር መሰረት ኢየሱስ  በዳዊት ከተማ በኢሩሳሌም በምትገኘው ቤተ-ልሔም ከተወለደ 2014 ዓመት ሆኖታል ። እንደ ቢቢሲ ዘገባ አዲስ ዓመትን ከሁሉም ቀደም ብላ የተቀበለችው አገር  ኒውዚላንድ ነች። ቤጅንግን ጨምሮ የምስራቅ እስያዎቹ  ጃካርታ እና ሲንጋፓር አዲስ ዓመቱን በደመቀ ሁኔታ ተቀብለዋል ።

Read More »

በተቀነባበረ የመብራት ሀይል ሙስና ኢትዮጵያ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ እንድታጣ ተደረገ

ታህሳስ ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ኤለክትሪክ ሀይል ኮርፖሬሽን ውስጥ በታየው ከፍተኛ የሙስና ወንጀል አገሪቱ ግማሽ ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ አጥታለች። ይህንን የሙስና አሰራር የተቃወሙት ስራ አስኪአጁ አቶ ምህረት ደበበ በመጨረሻ ከስልጣናቸው ተነስተዋል። የህወሃቱ ነባር ታጋይ፣ የደህንነት ምክትል ሃላፊ ፣ በአሁኑ ጊዜ በም/ል ጠቅላይ ሚኒስትር ማእረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመብራት ሃይል የቦርድ ሰብሰባ የሆኑት  ዶ/ር ...

Read More »

የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎችን ከደቡብ ሱዳን ማስወጣት መጀመሩን አስታወቀ

ታህሳስ ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ 1 ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ከቦርና ቢንቲዩ ግዛት መውጣታቸውን እና 650 የሚሆኑት ወደ ኢትዮጵያ ቀሪዎቹ ደግሞ ዋና ከተማዋ ጁባ መግባታቸውን ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ እንዳሉት ሁኔታዎች እየከፉ የሚሄዱ ከሆነ ቀሪዎቹን ዜጎች የማውጣት እቅድ አለ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በግጭቱ ውስጥ ከሞቱት 1 ሺ ሰዎች መካከል ...

Read More »

በገጠር መንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት ውስጥ በብልሹ አሰራር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እየባከነ ነው

ታህሳስ ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የተገኘ መረጃ እንደሚያመለክተው በባለስልጣኑ ውስጥ በብልሹ አሰራር   በትግራይ ክልል 37 ሚልየን 832 ሺ 770 ብር 35 ሳንቲም ለብክነት ተዳርጓል፡፡ በኦሮምያ ክልል ከ17 ሚልየን 892 ሺ ብር በላይ ፤ በደቡብ ክልል ከ23 ሚልየን 19 ሺ ሰባ ሶስት  ብር አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ባክኗል። በመተማ አብረሃጅራ ፕሮጀክት ብቻ ...

Read More »

ለስኳር ፕሮጀክቶች ገንዘብ አልተገኘም ተባለ

ታህሳስ ፳፩ ( ሃያ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሪፖርትር እንደዘገበው በአምስት አመቱ የልማት እቅድ መሰረት 10 አዳዲስ ፋብሪካዎችን ለመገንባትና 3 ነባር ፋብሪካዎችን ለማስፋፋት እንዲሁም የተጓተተውን የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ለማጠናቀቅ እቅድ ቢወጣም ፣ ሶስቱ ነባር ፋብሪካዎች ከህንድ በተገኘ 640 ሚሊዮን ዶላር ብድር ግንባታቸው እየተካሄደ ሲሆን፣ ለአዳዲሶቹ በቂ ገንዘብ አልተገኘም። የስኳር ኮርፖሬሽኑ 75 ቢሊዮን ብር ከመንግስት ግምጃ ቤት በሚገኝ ፋይናንስ ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት እንዲታደጋቸው እየተማጸኑ ነው

ታህሳስ ፲፰ አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዩኒቲ በሚባለው ግዛት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን በጦርነት አጣብቂኝ ውስጥ መገኘታቸውንና ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን ተናግረዋል። በግዛቱ ውስጥ በአንድ የመንገድ ስራ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ 6 ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩት በሁለቱ ተፋላሚ ሀይሎች መካከል የሚደረገውን የተኩስ ልውውጥ ለማምለጥ ያለፉትን ሁለት ቀናት በከባድ ማሽነሪዎች ውስጥ በመደበቅ ለማሳለፍ ተገደዋል። በአካባቢያቸው 2 ኢትዮጵያውያን መገደላቸውንና 3ቱ ደግሞ መቁሰላቸውን ...

Read More »

በሳውድ አረቢያ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ውስጥ ዘረኝነትና ሙስና ተስፋፍቷል ተባለ

ታህሳስ ፲፰( አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከቆንስላው ባገኘው የውስጥ መረጃ በሃላፊነት ላይ የተመደቡት አምስቱ ዲፕሎማቶች በዘረኝነትና በሙስና ከመዘፈቃቸው ም በተጨማሪ ሊሴ ፓሴ ለማውጣት ወደ ቆንስላው የሚደውሉትን ስደተኞች በስብሰባ ሰበብ የሉም በማስባል ጉዳያቸውን እያስፈጸሙ እንደልሆነ ተመልክቷል። ከአንድ ወር በፊት ከ160 ሺ በላይ ህዝብ የተፈናቀለበትን ችግር ለማወቅ በቆንስላው የተገኙትና ከዲፕሎማቶች ውጭ ያሉ ሰራተኞችን ብቻ በመሰብሰብ ” የችግሩ ምንጭ ...

Read More »

በቅርቡ ከእስር በተለቀቁት አንዳንድ የሙስሊም የመፍትሄ ኮሚቴ አባላት መካከል በ6ቱ ላይ ይግባኝ ሊጠየቅ ነው

ታህሳስ ፲፰( አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 4ኛው ምድብ ችሎት ካሰናበታቸው ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን መካከል በስድስቱ ላይ አቃቤ ህግ ይግባኝ መጠየቁ ታውቋል። አቃቢ ህግ ውሳኔው እንደተላለፈ ይግባኝ እንደሚል ባስታወቀው መሰረት ይግባኝ ማለቱ ታውቋል።  አቃቢ ህግ ይግባኝ የጠየቀባቸው ሰዎች ስም ዝርዝር አልታወቀም። አንዳንድ አስተያያት ሰጪዎች አቃቢ ህግ ይግባኝ መጠየቁ ፍርድ ቤቱ ነጻ መሆኑን ለማሳየት ተብሎ የተቀነባበረ ...

Read More »

በሞቃዲሹ ምግብ ቤት ውስጥ በተጠመደ ፈንጅ 11 ሰዎች ተገደሉ

ታህሳስ ፲፰ ( አስራ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ እንዳጠመደው በሚገመተው ፈንጅ ከሞቱት መካከል 6ቱ ወታደሮች ናቸው ተብሎአል። አንድ የሞቃዲሹ ፖሊስ ባለስልጣን ግን የሞቱት ወታደሮች ቁጥር 3 ናቸው ይላሉ። ወታደሮች ወርሀዊ ደሞዛቸውን ተቀብለው በምግብ ቤቱ ውስጥ እንደተገኙ ፍንዳታው መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል። የምግብ ቤቱን ባለቤት ጨምሮ 5 ሲቪሎች የተገደሉ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስ ፍንዳታውን አደረስኩ የሚል ወገን መግለጫ አልሰጠም። አልሸባብ ...

Read More »

በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በነጭ ሳር ግቢ የሚማሩ ከ25 ያላነሱ ተማሪዎች መታሰራቸው ታወቀ

ታህሳስ ፲፮( አስራ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም  ኢሳት ዜና :-ተማሪዎቹ የታሰሩት ካለፈው አርብ ጀምሮ ሲሆን፣ እስካሁንም በእነርሱ ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት አለመቆሙ ታውቋል። በግቢው ውስጥ ተማሪዎች የሚጠቀሙበት መጸዳጃ የተበላሸ መሆን፣ የምግብ ጥራት መጓደል፣ የውሀ እጥረት፣ የመብራት ለረጅም ጊዜ መቋረጥ፣ የትምህርት ስርአቱ በተገቢው መልኩ አለመከናወን፣ የመጽሀፍት እጥረት፣ የኮምፒዩተር አለመኖር እና በተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው የጤና መቃወስ ተማሪዎች ተቃውሞ እንዲያነሱ ግድ ብሎአቸዋል። ...

Read More »