የኢትዮጵያመንግሥትየጋዜጣናመጽሔትአከፋፋዮችንያለንግድፈቃድበመሥራትእናታክስባለመክፈልወንጀልለመክሰስ  እየተዘጋጀመሆኑተሰማ፡፡

ግንቦት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :የጋዜጣናመጽሔትአከፋፋዮችበተለይመንግሥትንየሚደግፉጋዜጣናመጽሔቶችንሆንብለውከገበያያስወጣሉበሚልከቅርብጊዜወዲህየተጠናከረትችትከመንግሥትባለሰልጣናትበመቅረብላይሲሆንበአቶሬድዋንሁሴንየሚመራውየመንግስትኮምኒኬሽንጽ/ቤትእያካሄደያለውንጥናትማጠናቀቁ ታውቋል። ምንጮችእንደገለጹትየጋዜጣናመጽሔትአከፋፋዮችንበሕገወጥነጋዴነትከመክሰስጎንለጎንእነሱሲሰሩ የነበሩትንሥራበአነስተኛናጥቃቅንነጋዴዎችበማስተላለፍመንግስትበአከፋፋዮችአማካይነትይደርሳልያለውንአፈናለማስቀረትእንደሚቻልጥናቱይጠቁማል፡፡ይህየመንግሥትሃሳብገናከውጥኑተቃውሞእየቀረበበትየሚገኝ ሲሆን፣  በተለይየሕትመትስርጭቱንበተዘዋዋሪመንገድመንግስትለመቆጣጠር  ማሰቡመንግስትየፈለገውንሲያሰራጭ፣ያልፈለገውንእንዲያፍንዕድልይሰጠዋል። በአሁኑወቅት በገዢው ፓርቲ ልሳን በሆነው ራዲዮፋናከአከፋፋዮችጋርበተያያዘከጋዜጠኞችጋርውይይትእየተካሄደሲሆንበተለይየብሮድካስትባለስልጣንየቦርድአባልየሆኑትአቶዛዲግአብርሃብዙዎቹአከፋፋዮችሕገወጦችመሆናቸውንበመጥቀስመንግስትእርምጃለመውሰድእያጠናመሆኑንበግልጽተናግረዋል፡፡ በዚሁፕሮግራምላይአከፋፋዮቹከውጪገንዘብእየተቀበሉየተወሰኑየፕሬስውጤቶችንያፍናሉየሚሉውንጀላዎችምተደምጠዋል፡፡ ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ገዢው ፓርቲ አይደግፉኝም የሚላቸውን ጋዜጦች በተለያዩ ወንጀሎች እየከሰሰ ከገበያ ሊያወጣቸው እየሞከረ መሆኑን መዘገባችን ይታወቃል።

Read More »

በሃረር በአንድ ለአምስት ያልተደራጁ የእርዳታ አጎበር እንደማያገኙ ተነገራቸው

ግንቦት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሃረር ወኪላችን እንደዘገበው ለወባ መከላከያ በሚል ከውጭ በእርዳታ ስም የተገኘውን አጎበር የመንግስት ባለስልጣናት በአንድ ለአምስት እና በአንድ ለሰላሳ ላልተደራጁት አንሰጥም በመላታቸው ፣ መደራጀት ያልቻሉ ነዋሪዎች አጎበር  ሳያገኙ ቀርተዋል። በነጻ የሚታደለው ይህ አጎበር ከክረምቱ መግቢያ ጋር ተያይዞ የአካባቢው ህዝብ ራሱን ከወባ እንዲከላከል ተብሎ የሚሰጥ ነው። ከአለማቀፉ የወባና ኤድስ ፈንድ በነጻ እንደተገኘ በሚገለጸው እርዳታ ፣ ...

Read More »

በእነ መላኩ ፋንታ ላይ ሊሰጥ የነበረው ብይን ተራዘመ  

ግንቦት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከፍተኛው ፍርድ ቤት የተከሳሽ ጠበቆችና አቃቢ ህግ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ተንተርሶ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም፣ 15ኛወንጀልችሎትበነመላኩፈንታየክስመዝገቦችክስመቃወሚያላይለዛሬብይን ለመስጠት ይዞትየነበረውን የመጨረሻ ቀጠሮዳግምያራዘመው የአቃቂ ቃሊቲ ምድብ ችሎት መንገድ ዳር በመሆኑ በስፍራው ያለው ድምጽ ችሎቱን ለመሰየም አያስችልም በሚል ምክንያት ነው። ችሎቱ በፊት ሲደረግ እንደነበረው በልደታ ፍርድ ቤት ግንቦት22፣ 2006 ዓም እንዲካሄድ ሲወስን ጠበቆች ግን ፍርድ ...

Read More »

መድረክ የፊታችን ቅዳሜ በሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ ህዝቡ በብዛት እንዲገኝ ጥሪ አቀረበ

ግንቦት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመድረክ የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ጥላሁን እንዳሻው ለኢሳት እንደተናገሩት በመጪው ቅዳሜ በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ህዝቡ በብዛት ወጥቶ ችግሮቹን እንዲያሰማ ጠይቀዋል። የሰልፉ ዋና አላማ በአገራችን ለሚነሱ የመብት ጥያቄዎች የሃይል ምላሽ መስጠት ይቁም የሚል መሆኑን የገለጹት አቶ ጥላሁን፣ በኦሮምያ በተማሪዎች ላይ የተወሰደውን የሃይል እርምጃ እንደሚያወግዝም ጠቁመዋል። መድረክ ሁለት ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ አቅርቦ ቢከለከልም ...

Read More »

በጣሊያን ራሳቸውን እንዳጠፉ የተነገረላቸው ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት አሟሟት መንስኤ በውል አልታወቀም

ግንቦት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትናንት በስቲያ ከመደበኛ የስራ ሰአት ውጭ ከጧቱ 1 ሰአት ተኩል ላይ ወደ ቢሮአቸው በመግባት ራሳቸውን ከ2ኛ ፎቅ ወርውረው የገደሉት የ62 አመቱ ዲፕሎማት አቶ ፍሰሃ ተስፉ ስለ አሟሟታቸው መንስኤ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መግለጫ አልሰጠም። ክሮናካ ዲ ሮማ የተባለው የጣሊያን ጋዜጣ ዛሬ ይዞት በወጣው ሰፊ ዘገባ ዲፕሎማቱ ከመሞታቸው ከሁለት ቀናት በፊት ከስራ ተነስተው ወደ አገራቸው ...

Read More »

በአዲስ አበባ በህገወጥ መንገድ ተስርተዋል የተባሉ ቤቶችን የማፍረስ ሂደቱ እንደቀጠለ ነው

ግንቦት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች እንደገለጹት መንግስት በህወገወጥ መንገድ ተስረተዋል ያላቸውን ቤቶች ያለምንም ተተኪ ቦታና ቤት በማፍረሱ በርካታ ቤተሰቦች ሜዳ ላይ እየተበተኑ ነው። ኮልፌ አካባቢ አንፎ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው ሰፈር ከ2 ሺ እስከ 3 ሺ ቤቶች መፍረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚኖሩ ከ570 በላይ ቤቶች ይፈርሳሉ በመባሉ ነዋሪዎች አቤቱታዎችን ...

Read More »

ደብረ ብርሃን በአንበጣ መንጋ መወረሩዋ ታወቀ

ግንቦት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በአዲስ አበባ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በደብረብርሃን ከተማ መታየቱን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአንበጣ መንጋው በአካባቢው ባለ እጽዋት ላይ ያደረሰው ጉዳት ይኑር አይኑር በውል አልታወቀም።

Read More »

በደቡብ ሱዳን ለተከሰተው ረሃብ የገንዘብ ድጋፍ እየተሰባሰበ ነው

ግንቦት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና በተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር መካከል የተጀመረው ጦርነት ከ4 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ለረሃብ ማጋለጡን ተከትሎ በኖርዌይ በተካሄደው የእርዳታ ማሰባሰብ ስራ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ ተገኝቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ችግሩን ለመቅረፍ ከ1 ቢሊዮን 800 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ እየገለጸ ነው። በርካታ ገበሬዎች በጦርነት የተነሳ ማረስ እንዳልቻሉ እና የረሃቡም መንስኤ ጦርነቱ መሆኑን ...

Read More »

የሶማሊ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ወሬዎች እየተናፈሱ ነው

ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦህዴድ -ህወሃት እንደተቀነባበረ በሚነገርለት አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙ የሶማሊ ክልል ተወላጅ ተማሪዎችን ከኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ጋር ለማጋጨት ያለመ መሆኑን ለኢሳት ደረሰው መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ካድሬዎች ” የሶማሊ ተማሪዎች ከመንግስት ጎን ቆመው በኦሮሞ ተማሪዎች ዙሪያ መረጃ እየሰጡን ነው” የሚል አሉባልታ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች መነዛቱ፣ የሶማሊ ተማሪዎችን ስጋት ላይ የጣላቸው ሲሆን፣ ተማሪዎቹ ከመንግስት ጎን ...

Read More »

በጣሊያን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለስልጣን መሞታቸው ታወቀ  

ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአባታቸው ስም ለጊዜው ያልታወቀውና በተጠባባቂ አምባሳደር ማእረግ ደረጃ ሲሰሩ የቆዩት አቶ ፍስሃ ጧት ስራ ከገቡ በሁዋላ መሞታቸው ታውቋል። ኢሳት ስለ አሟሟታቸው ዝርዝር መረጃ ባያገኝም አንዳንድ ጣሊያን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግለሰቡ የሞቱት ከ3ኛ ፎቅ ላይ ራሳቸውን ወርውረው ነው ይላሉ። ፖሊስ ወደ አካባቢው ደርሶ ምርመራ ካደረገ በሁዋላ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንና መሞታቸውን ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል። ...

Read More »