በጣሊያን የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለስልጣን መሞታቸው ታወቀ  

ግንቦት ፲፫ (አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአባታቸው ስም ለጊዜው ያልታወቀውና በተጠባባቂ አምባሳደር ማእረግ ደረጃ ሲሰሩ የቆዩት አቶ ፍስሃ ጧት ስራ ከገቡ በሁዋላ መሞታቸው ታውቋል።

ኢሳት ስለ አሟሟታቸው ዝርዝር መረጃ ባያገኝም አንዳንድ ጣሊያን ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ግለሰቡ የሞቱት ከ3ኛ ፎቅ ላይ ራሳቸውን ወርውረው ነው ይላሉ።

ፖሊስ ወደ አካባቢው ደርሶ ምርመራ ካደረገ በሁዋላ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውንና መሞታቸውን ነዋሪዎች አክለው ተናግረዋል።

ስለ አሟሟታቸው መንስኤ እስካሁን ይህ ነው የተባለ መረጃ አልተገኘም።

ባለቤታቸው ወደ ሮም መምጣታቸውን፣ ሮም የሚገኘው ኢትዮጵያ ኢምባሲ ዝግ ሆኖ መዋሉን ኢሳት አረጋግጧል። ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን ለህዝብ እናቀርባለን።