መድረክ የፊታችን ቅዳሜ በሚያደርገው የተቃውሞ ሰልፍ ህዝቡ በብዛት እንዲገኝ ጥሪ አቀረበ

ግንቦት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመድረክ የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ጥላሁን እንዳሻው ለኢሳት እንደተናገሩት በመጪው ቅዳሜ በሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ህዝቡ በብዛት ወጥቶ ችግሮቹን እንዲያሰማ ጠይቀዋል።

የሰልፉ ዋና አላማ በአገራችን ለሚነሱ የመብት ጥያቄዎች የሃይል ምላሽ መስጠት ይቁም የሚል መሆኑን የገለጹት አቶ ጥላሁን፣ በኦሮምያ በተማሪዎች ላይ የተወሰደውን የሃይል እርምጃ እንደሚያወግዝም ጠቁመዋል።

መድረክ ሁለት ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥያቄ አቅርቦ ቢከለከልም በመጨረሻ ግን ፈቃድ ማግኘቱን የገለጹት አቶ ጥላሁን፣ ግንቦት 16 የሚካሄደው ሰልፍ  ከጧቱ 3 ሰአት ጀምሮ እስከ 6 ሰአት ድረስ ከግንፍሌ ወንዝ ድልድይ ተነስቶ የካ ከፍለ ከተማ ወረዳ 8 ባለው ቦታ ላይ ይካሄዳል።

የአዲስ አበባ አዲሱን ማስተር ፕላን በተመለከተ መድረክ ያለህዝብ ተሳትፎ መካሄድ እንደሌለበት እንደሚያምን የገለጹት አቶ ጥላሁን፣ መንግስት በሚስጢር ይዞ የሚሰራው ስራ አሁን የታየውን ችግር መፍጠሩንና እስካሁንም ለታየው ችግር መንግስት ተጠያቂ መሆኑን ገልጸዋል

“የተቃውሞ ሰልፎችን በጋራ ለማካሄድ ለምን አልቻላችሁም፣ መድረክ የህዝብ ግንኙነት ስራ በመስራት በኩል ድክመት እንዳለበት በገሃድ ይታያል  ለዚህስ ምን ምላሽ አላችሁ ተብለው የተጠየቁት አቶ ጥላሁን፣ ከፓርቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት ጥረት ማድረጋቸውን፣ የህዝብ ግንኑነት ስራን በተመለከተም ድክመት ቢኖርባቸውም ሌሎች ሚዲያዎችም ለመድረክ በቂ ሽፋን የማይሰጡ መሆናቸውን በማንሳት ወቀሳ አቅርበዋል። ሙሉ ቃለ መልልሱ ከመጨረሻው ዜና በሁዋላ እንደሚቀርብ ለመግለጽ እንወዳለን።

በሌላ ዜና ደግሞ ከአዲስአበባማስተርፕላን ጋር ተያይዞ  የተነሳውን  ተቃውሞለማርገብበአዲስአበባየሚገኙ የጸጥታሃይሎችበፖለቲካናበደህነትክትትልአቅማቸውንለማጎልበት በሚል ስልጠናእየተሰጣቸውነው፡፡ከፖሊስጣቢያኃላፊጀምሮእስከከፍተኛየፖሊስማዕረግያላቸውየፖሊስአባላትበኮልፌፖሊስማሰልጠኛናበሰንዳፋፖሊስማሰልጠኛከግንቦት 11 ቀን 2006 ዓ.ምጀምሮለአንድወርየሚቆይስልጠናእየተሰጣቸው እንደሚገኝ ለመረዳት ተችሎአል።

ስልጠና በገቡትኃላፊዎችምትክሌሎችየፖሊስአባላትንበመወከልየጸጥታስራውንከመረጃናደህንነትአባላትጋርበማቀናጀት  እየተከታተሉትእንደሚገኙ ታውቋል፡፡

በከተማዋበየቀኑጧት 4፡00 ሰዓት ላይ በክፍለከተማስራአስፈፃሚደረጃየከተማውጸጥታሁኔታእየተገመገመሲሆን፣ከሰዓት በሁዋላ 8፡00 ሰዓትላይደግሞየግምገማሪፖርቱለመረጃናደህንነትግብረኃይልሪፖርትእየተደረገ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሎአል፡፡