ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ2014 “የጎልደን ፔን ኦፍ ፍሪደም” ሽልማት አሸናፊ የሆነው እስክንድርነጋ ዛሬ ሽልማቱን ተቀበለ። በጣሊያን ቶሪኖ በተካሄደው የሽልማት ስነ-ስር ዓት ላይ እስክንድርን ወክሎ ሽልማቱን የተቀበለው በቃሊቲእስርላይየነበረው ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ ነው። “ምኞቴ ይህን ሽልማት እኔ እንድቀበለው አልነበረም” በማለት ንግግሩን የጀመረው ማርቲን፣ “ዛሬ ጠዋት ስነሳ ምናለ፦“ ተፈታሁኮ፤ ሽልማቱን እኔ ራሴ ልቀበል እመጣለሁ” የሚል ስልክ ከአዲስ አበባ በስልክ ብሰማ ...
Read More »አንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በደብረማርቆስ እና በአዳማ ከተሞች ደማቅ ሰልፎችን አድረገ።
ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት!” በሚል መሪ ሀሳብ ትናንት እሁድ በሁለቱ ከተሞች ባደረጋቸው ሰልፎች በሺህዎች የሚቆጠሩ የየከተሞቹ ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት የ ኢህ አዴግ መንግስት እየፈጸማቸው ናቸው ባሉዋቸው ሀገራዊና አስተዳደራዊ በደሎችዙሪያ የተቃወሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ከብ መንግስታዊ ቢሮከራሲዎች እና እልህ አስጨራሽ ወጣ ውረዶች በሁዋላ በተደረጉት ሰልፎች በተለይም መሬት የመንግስት የፖለቲካ መሳሪያ መሆኑ እንዲያከትም እና ገበሬው የመሬት ...
Read More »በፓኪስታን- ካራች አውሮፕላን ማረፊያ ከባድ ጥቃት ተፈጸመ።
ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንደ ቢቢሲ ሪፖርት፤በሀገሪቱ ታላቅ አውሮፐላን እሀድ እለት በተከፍተው ጥቃት አስር የጥበቃ ሰራተኞችን ጨምሮ በትኝሹ 28 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፤ የታሊባን አማጺዎች ለጥቃቱ ሀላፊነቱን ወስደዋል። ጥቃቱ የተጀመረው እሁድ ማምሻው ላይ ለካርጎ ጭነት እና “ለቪ. አይ፣ፒ” በረራ በሚያገለግሉት የካራቺ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያው ክፍሎች ላይ ነው። ሰኞ ማለዳ በአውሮፐላን ማረፊያው አዲስ የተኩስ ልውውጥ መሰማቱን ተከትሎ የሀገሪቱ ባለስልጣናት በሰጡት ...
Read More »በአዲስ አበባ የህዝብ መፈናቀል እንደሚቀጥል መረጃዎች አመለከቱ
ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ማደስና ፕላን ዝግጅት በሚባለው ፕሮግራሙ በመሃል አዲስ አበባ የሚገኙ ኪስ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎችን በስፋት እንደሚያፈናቅል የሚነገርለትን እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የአስተዳደሩ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ አካባቢን መልሶ የማልማት ገጽታ አለው በሚባለው ሥራ ውስጥ ዘንድሮ ከተካተቱ አካባቢዎች መካከል በካዛንቺስ 26 ሄክታር፣በደጃችውቤ 11.6 ሄክታር፤በሸበሌሆቴልዙሪያ 10.4 ሄክታር፣አሜሪካንግቢ 16 ሄክታር፣በአፍሪካህብረትቁጥር 2 ወደ 15 ...
Read More »በጋዜጣ አዙዋሪዎች ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩ ታወቀ
ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰማያዊ ፓርቲ ልሳን የሆነው ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ሃሙስ ምሽትላይ በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ጋዜጣ አዙዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች ታግተው አምሽተዋል፡፡የደህንነት ኃይሎች ‹‹ለማዞር የተደራጃችሁበትንና ፈቃድ የተሰጣችሁበትን ወረቀት አምጡ›› በማለት ወደ ጣቢያ ሊወስዱዋቸው እንደ ነበርና አዙዋዎቹም ‹‹መደራጀት አይጠበቅብንም ፣ጣቢያም አንሄድም›› ብለው የደህንነቶቹን ትዕዛዝ መቃወማቸውን ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ መንግስትን የሚተቹ ጋዜጦችና መጽሄቶች እንዲያዞሩ እንደማይፈልግና እሱ የሚፈልገውን ...
Read More »አንድነት በደብደረማርቆስ እና በአዳማ ለሚካሂደው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ እያካሄደ ነው
ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የድርጅቱ አመራሮች ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ሁለት ቀናት በርካታ በራሪ ወረቀቶች ተበትነዋል፣ ፖስተሮችን መለጠፍና በድምጽ ማጉያ መሳሪያ በመጠቀም ቅስቀሳ ተካሂዷል። የህዝቡ ስሜት አስገራሚ ነው የሚሉት አመራሮች፣ ህዝቡ ወረቀቶችን ያለምንም ችግር እየተቀበለ እንደሚያሰራጭ፣ በተለይ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ አመራሮች ገልጸዋል። የአንድነት ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ሰብሳቢ አቶ ዋለ ባየ በእሁዱ ሰልፍ ብዙ ህዝብ ወጥቶ ...
Read More »መንግስት በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ቦንብ የወረወሩትን መያዙን አስታወቀ
ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጸር ሽብር ግብረሃይል ለአንድ ተማሪ ህይወት መጥፋትና ከ15 በላይ ተማሪዎች መቁሰል ተጠያቂ የሆኑ ተማሪዎችን በተለያዩ ጊዜ አፈላልጎ መያዙን አስታውቋል። አበበ ኡርጌሳ፣ ኑረዲን ሃሰን፣ ኒሞና ጫሌና መገርሳ ወርቁ የተባሉት ተማሪዎች ቦንቦን ካፈነዱ በሁዋላ በተማሪዎቹ ላይ በፌሮና በድንጋይ ድብደባ መፈጸማቸውን ግብረሃይሉ ገልጿል። ኑረዲን ሃሰን የተባለው የኮምፒዩተር ሳይንስ ተማሪ በእስር ቤት ራሱን ማጥፋቱን መንግስት አክሎ አስታውቋል። ...
Read More »በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጰያውያን ስደተኞች የርሀብ አድማ ጀመሩ።
ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጀርመን-ባየርን ክልል የሚገኙ ወደ 60 የሚጠጉ ኢትዮጰያውያን ስደተኞች የረሀብ አድማ ለማድረግ የተገደዱት የኢትዮጵያ ስደተኞች ጉዳይ በጀርመን ካሉ አካባቢዎች በተለየ መልኩ በባየርን ክልል እና ፍርድ ቤት ተቀባይነት ስለማያገኝ ነው። በከተማ መሀል ላይ በመሰባሰብ ባለፈው ረቡእ የተጀመረው የኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች የረሀብ አድማ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት የሶሪያ፣የሊቢያ እና የኢራቅ ስደተኞችም በአድማው ከኢትዮጵርያውያኑ ጋር እየተቀላቀሉ ነው። ...
Read More »የቡድን 7 አገራት ከድሃ አገራት በህገ ወጥ መንገድ የሚወጣውን ገንዘብ ለመቆጣጠር በድጋሜ ቃል ገቡ
ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግሎባል ፋይናንሻል ኢንተግሪቲ ለኢሳት በላከው መግለጫ በእንዱስትሪ ሃብታቸው የበለጸጉት 7ቱ አገራት ከድሃ አገሮች እየተዘረፈ በምእራባዊያን ባንኮች የሚቀመጠውን ገንዘብ ለመቆጣጠር በድጋሜ ቃል ገብተዋል። የቡድን 7ቱንአገራትአቋምያደነቀውግሎባልፋይናንሻልኢንተግሪቲ፣ቃሉበተግባርመለወጥእንዳለበትአሳስቧል። ግሎባል ፋይናንሻል ኢንትግሪቲ ከኢትዮጵያ በ9 አመታት ውስጥ ከ11 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በህገወጥ መንገድ ወደ ውጭ መውጣቱን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። ወደ ውጭ የወጣው ገንዘብ ኢትዮጵያ በዚህ አመት ከመደበችው 8 ...
Read More »በሀረር ከተማ በርካታ ተማሪዎች ታሰሩ
ግንቦት ፳፰(ሃያ ስምን)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአቦከር መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የታሰሩት የሁለተኛ ደረጃ ፈተና ካጠናቀቁ በሁዋላ ከግቢያቸው በመውጣት መፈክሮችን እያሰሙ ወደ ማሃል ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ነው። ተማሪዎቹ “በሀረር ክልል የሚታየው አድሎ ይቁም፣ ፍትሃዊ አስተዳደር ይኑር፣ መንግስት በህዝብ ላይ የሚያደርሰው በደል ይቁም” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች እያሰሙ ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ አርፍደዋል። የክልሉና የፌደራል ፖሊስ በጋራ ተቃውሞውን የተቆጣጠሩት ሲሆን፣ ...
Read More »