አንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በደብረማርቆስ እና በአዳማ ከተሞች  ደማቅ ሰልፎችን አድረገ።

ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድነት “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት!” በሚል መሪ ሀሳብ ትናንት እሁድ በሁለቱ ከተሞች ባደረጋቸው ሰልፎች በሺህዎች የሚቆጠሩ የየከተሞቹ ነዋሪዎች አደባባይ በመውጣት የ ኢህ አዴግ መንግስት እየፈጸማቸው ናቸው ባሉዋቸው ሀገራዊና አስተዳደራዊ በደሎችዙሪያ የተቃወሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ከብ መንግስታዊ ቢሮከራሲዎች እና እልህ አስጨራሽ ወጣ ውረዶች በሁዋላ በተደረጉት ሰልፎች በተለይም መሬት የመንግስት የፖለቲካ መሳሪያ መሆኑ እንዲያከትም እና ገበሬው የመሬት ባላቤትነት መብቱ ሙሉ በሙሉ እንዲረጋገጥለት ተጠይቁዋል።

መነሻውን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አደባባይ አድርጎ በአብማ ወደ መስቀል አደባባይ ባመራው የደብረማርቆሱ የተቃውሞ ሰልፍ በቅርቡ  በኦሮሚያ ክልል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከ አዲስ አበባ ማስተር ፐላን ጋር በተያያዘ ያነሱዋቸውን ጥያቄዎች ተከትሎ በተማሪዎቹ ላይ የሀይል እርምጃ የወሰዱ እና ያስወሰዱ ሀይሎች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።

መነሻውን ፖስታ ቤት አደባባይ አድርጎ እና  በበቀለ ሞላ መንገድ አልፎ ወደ ቀይ መስቀል በማቅናት በአስተዳደር ጽ/ቤት በዞረው የአዳማ ከተማሰልፍ የተሳተፉ ሰልፈኞች በበኩላቸው መንግስት በፈለገ ሰዓት ያለምንም ተለዋጪ አማራጪ  እና ካሳ ህብረተሰቡን እና ገበሬውን   ከመሬቱናከቤቱ  እያፈናቀለ ሜዳ ላይ የሚበትንበት አስራር በአስቸኩዋይ እንዲቆም ድም[አቸውን አሰምተዋል።

የከተሞቹ ስልፈኞች ከሲህም ባሻገር  ያለበደላቸው በየእስር ቤቱ የታጎሩ ፖለቲከኞች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ጋሴጠኞች እና የሶን 9 ጦማርያን እንዲፈቱ፣በህገ መንግስቱ እውቅና የተሰጣቸው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ እና የመደራጀት መብት በተግባር እንዲከበር፣ መንግስት ከሀይማኖቶች ላይ እጁን እንዲያነሳ ጠይቀዋል።

አንድነት ከወራት በፊት፦“የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት”በሚል መርህ በተለያዩ ከተሞች ሰልፎችን ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን፤አሁን “የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት”በሚል መርህ መካሄድ የጀመረው ሰልፍ የመጀመሪያው ዙር ዘመቻ ተከታይ እንደሆነ ከአስተባባሪዎቹ ገለጻ ለመረዳት ተችሎአል።

“የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት”በሚል መርህ የተጀመረው ሰልፍ  በተለያዩ ከተሞች በስፋት እንደሚቀጥልም ፓርቲው አስታውቆአል።