ሰኔ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ በቅርቡ ከተነሳው የመልካም አስተዳደር ፣ የማንነትና የፍትህ ጥያቄ ጋር በተያያዘ ፍትህ አጥተው ያለፉትን ስምንት ወራት በእስር ቤት ካሳለፉ ትመካከል የ14 የቤተሰብ አባላት አስተዳዳሪ የሆኑት የ39 ዓመቱ አቶ ሻልሼሸዋ ከሞቱና የሌሎችም እስረኞች ህይወት አደጋ ላይ በመውደቁ እንዲሁም በአካባቢው ድጋሜ ግጭት ይነሳል የሚል ስጋት በመፍጠሩ 4 የአገር ሽማግሌዎች ጉዳዩን ለፌደራሉ መንግስት በድጋሜ ...
Read More »የጋዝጊብላ ነዋሪዎች ኢህአዴግ ክዶናል ሲሉ ተናገሩ።
ሰኔ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ከትግራይ ህዝብ በመቀጠል ኢህአዴግ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ከፍተኛ የህይወት መስዋትነት የከፈለው የሰቆጣና አካባቢዋ ነዋሪዎች ቢሆኑም፣ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ከገባ ጀምሮ እንደረሳቸው ገልጸዋል። ከሶቆጣ 48 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘዋ ጋዝጊብላ ወረዳ የሚኖሩ የቀድሞ ታጋዮች ለኢሳት እንደገለጹት፣ ለኢህአዴግ ልጁን ያልገበረ ሰው ባይኖርም፣ ባለስልጣናቱ ግን ውለታቸውን መርሳታቸውን ተናግረዋል። ከሰቆጣ ላሊበላ የህዝብ ትራንስፖርት አለመኖሩን ፣ ከአዲስ ...
Read More »በኬንያ በርካታ ሴቶች ታፍነው ተወሰዱ።
ሰኔ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ እንደፈጸመው በተጠቀሰው ጥቃት 48 ሰዎች በተገደሉ ማግስት፣ ሌሎች ተጨማሪ 12 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ከ12 ያላነሱ ሴቶችም በታጣቂዎች ታፍነው መወሰዳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ምፔኬቲኒ እየተባለ በሚጠራው የወደብ ከተማ ላይ የደረሰውን ተከታታይ ጥቃት አልሸባብ እንደፈጸመው እየተዘገበ ባለበት ወቅት፣ የአገሪቱ መሪ ኡሁሩ ኬንያታ ፣ ጥቃቱ በራሳቸው ባለስልጣናት የተቀነባበረና ከጎሳ ጋር የተያያዘ መሆኑን በመግለጽ፣ አልሸባብ ፈጸምኩ የሚለውን ጥቃት ...
Read More »ባግዳድ በሱኒ ታጣቂዎች እጅ ልትወድቅ መቃረቡን ተከትሎ አሜሪካ የኢምባሲ ሰራተኞችን እያስወጣች ነው።
ሰኔ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባልታሰበ ቅጽበት የተለያዩ የሰሜን ኢራቅ ከተሞችን እየተቆጣጠሩ የመጡት የሱኒ ኢስላሚክ ታጣቂዎች ፣ ዋና ከተማዋን ባግዳድን ለመያዝ በቅርብ እርቀት እየተፋለሙ ሲሆን፣ አሜሪካ የኢምባሲ ሰራተኞቹዋን ለማሸሽ ሽፋን የሚሰጡ ከ250 በላይ የጦር ሰራዊቷን መላኩዋ ታውቋል። የእግረኛ ሰራዊት ለመላክ እንደማትሻ ያስታወቀችው አሜሪካ፣ በኢራቅ ላይ ስለምትወስደው እርምጃ ውሳኔ ላይ አልደረሰችም። እስላሚክ ታጣቂዎቹ ባግዳድን ከተቆጣጠሩ ከሺያ ታጣቂዎች ጋር ደም አፋሳሽ ...
Read More »በሃረር ከፍተኛ የውሃ እና የምግብ ዘይት ችግር ተከሰተ
ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን ከስፍራው እንደዘገበው በከተማዋ በተለይም ቀበሌ 14፣ 15፣ 16፣ 17፣ 18 እና 19 እንዲሁም በሸንኮራ፣ ጀጎልና ቀለዳምባ አካባቢዎች ከፍተኛ የውሃ እጥረት በመከሰቱ ህዝቡ የጀኔሪካን ውሃ በውድ ዋጋ ለመግዛት ተገዷል። የክልሉ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ከአንድ አመት ከስድስት ወር በፊት ከሃረር በ75 ኪሜ ርቀት ላይ አሰሊሶ በሚባለው ቦታ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ካስቆፈራቸው 17 ...
Read More »በ10 እስር ቤቶች የተከሰተው ኩፍኝ 9 ሰዎችን ገደለ
ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቁጥራቸው ከ4000 በላይ በሚገመት ታራሚዎች ላይ የተከሰተው የኩፍኝ በሽታ በአማራና በኦሮምያ ክልሎች 9 እስረኞች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። “መንግሰት የጥበቃ አገልግሎት የሚሰጡ በቂ የማረሚያቤት ሰራተኛ የለኝም ፤ ቅዳሜ እና እሁድ ፤ የህክምና አገልግሎት አይሰጥም” በሚሉ ሰበቦች አደጋው እንዲባባስ እና ለእስረኞች ህይወት ማለፍ ምክንያት መሆኑ መረጃው ያመለክታል። የኢትዩጵያ የቀይ መስቀል ቡድን በሁለቱ ክልሎች በሚገኙ 16 ...
Read More »ፈንጅ አምካኝ ወታደሮች በብሄራችን የተነሳ አድሎ ተፈጽሞብናል ሲሉ ተናገሩ
ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዩ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ፈንጅ ያመክኑ የነበሩ ወታደሮች እስከዛሬ ለከፈልነው መስዋትነት ከ3 እስከ 7 ሺ ብር ብቻ እየተሰጠ፣ ብሄራችን እየተመረጠ ከመከላከያ እንድንሰናበት ተደርገናል ብለዋል። ሰሞኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጄኔራል ተክለብርሃን ወ/ዓረጋይ ወደ አማራ፣ ኦሮምያና ደቡብ ክልሎች ተዘዋውረው ወታደሮችን ያነጋገሩ ሲሆን “ጊዜው ለልማት እና ለስራ የሚነሳሱበት እንጅ አድማ በመምታት ነገር የሚያሰሩበት ...
Read More »ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩ ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው
ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በፌስ ቡክ ላይ የተለያዩ ጽሁፎችን በመጻፍ በወጣቶች ዘንድ ከፍተኛ ደጋፊ ያገኙት ዞን 9 እየተባሉ የሚጠሩ ወጣት ጸሃፊዎችና ጋዜጠኞች ባለፈው ቅዳሜ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም፣ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ማእከላዊ ተመልሰዋል። እጆቻቸውን በካቴናዎች የታሰሩት ወጣት ብእረኞች አካላዊ መጎሳቆል ቢታይባቸውም፣ መንፈሳቸው ግን ጠንካራ መሆኑን ዘጋቢያችን ገልጿል። መንግስት በፌስ ቡክ እና በተለያዩ የማህበራዊ የመገናኛ መንገዶች የሚሰራጩ ...
Read More »በኬንያዋ የወደብ ከተማ በርካታ ሰዎች ተገደሉ
ሰኔ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አልሸባብ እንደፈጸመው በተገመተው በዚህ ጥቃት 48 ሰዎች ተገድለዋል። የቱሪስት መዳረሻ በሆነቸው በላሙ ደሴት በደረሰው ጥቃት ሆቴሎችና መኪኖችም ተቃጥለዋል። ፖሊሶች ከታጣቂዎች ጋር ተኩስ መክፈታቸውን ተከትሎ ታጠቂዎች ወደ ጫካ ገብተው ማምለጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ የፖሊስና የደህንነት ተጠሪያቸውን በማስጠራት በቀጣይ ስለሚወስዱት እርምጃ መክረዋል። አልሸባብ በኬንያ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶችን እየፈጸመ ነው። ኬንያ ጦሩዋን ወደ ሶማሊያ አስገብታ ...
Read More »በጎደሬ ወረዳ አካባቢ በምትገኘው ጻኑ ግጭት ተቀሰቀሰ
ሰኔ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎደሬ ወረዳ አካባቢ በምትገኘው ጻኑ ሃሙስ ሰኔ 5 ፣ 2006 ዓም የተነሳው ግጭት ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት መሆኑን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የወረዳው ባለስልጣናት ከክልሉ ውጭ የሚኖሩ የሌሎች አካባቢ ተወላጆችን አካካቢውን ለቀው እንዲወጡ ማዘዛቸውን የሚናገሩት ምንጮች፣ በረካታ ነዋሪዎች ተፈናቅለው በአሁኑ ጊዜ ቴፒ ከተማ ውስጥ ሰፍረው እንደሚገኙ ታውቋል። በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደተጎዱ ባይታወቅም አንድ ...
Read More »