በመቶዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ወጣቶች ታፍነው ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰዱ

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ተይዘው በወረዳ 5 ቀበሌ 08/09 በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ እንዲቆዩ የተደረጉ ወጣቶች ዛሬ ጧት ላይ በሶስት አይሲዙ መኪኖች ተጭነው ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። ወጣቶቹ በቅርቡ በአዲስ አበባ የተደረገውን ተቃውሞ ተከትሎ ከየስፍራው የተሰባሰቡ ሲሆን፣ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ረብሻ ሊያስነሱ ይችላሉ በሚል በአደገኛ ቦዘኔ ስም የተያዙ ናቸው። ...

Read More »

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሃላፊ በኢትዮጵያ ስላለው  የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና ስለዲሞክራሲ ከኢህአዴግ መንግስት ባለስልጣናት ጋር መነጋጋራቸውን ገለጹ

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ምክትል የውጭ ጉዳይ ሃላፊዋ ውንዲ ሸርማን በቅርቡ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት በመንግስት ሚዲያ የኢትዮጵያን ዲሞክራሲና ምርጫ አድንቀው መናገራቸው ከየአቅጣጫው ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል። ዋሽንግተን ፖስት የተባለው ታዋቂ ጋዜጣ በርእሰ አንቀጹ ወንዲ ሽርማንን የተቸ ሲሆን፣ ባለስልጣኗም ጋዜጣው በተሳሳተ መንገድ እንደተረዳቸውና ትችቱ ተገቢ አለመሆኑን በጽሁፍ መልስ ሰጥተዋል። ባለስልጣኗ ኢትዮጵያ አስቸጋሪ በሆነበት አካባቢ አልሸባብን በመዋጋት፣ በደቡብ ሱዳን ...

Read More »

የግብጽ መከላከያ ስራዊት ሊቢያ ውስጥ ታፍነው የነበሩ ኢትዮጰያውያንን  ማስለቀቁ ተዘገበ።

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሬውተርስ የግብጽ መንግስታዊ  የዜና ማሰራጫን ጠቅሶ እንደዘገበው ፤ ሊቢያ ውስጥ ታግተው የነበሩና በግብጽ ጦር ጥረት ከታገቱበት የተለቀቁ 27 ኢትዮጰያውያን ዛሬ ሀሙስ ካይሮ አውሮፕላን ማረፊያ ገብተዋል። ኢትዮጰያውያኑ በግብጽ አውሮፕላን ተጉዘው ካይሮ ሲደርሱ በግብጽ ፕሬዚዳንት በአብደል ፋታህ አል-ሲሲ እና በሌሎች ከፍተኛ የግብጽ ባለስልጣናት አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤የአቀባበል ሥነ-ስር ዓቱ በግብጽ ሚዲያዎች የቅጥታ ስርጭት እንዲታይ ...

Read More »

ኢሳት አዲሱ ስርጭቱ መቋረጡን ተከትሎ የችግሩን ምንጭ ለማወቅ ጥረት በማድረግ ላይ ነው

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት በቅርቡ በዩቴልሳት ስርጭቱን በአዲስ መልክ ማሰራጨት ቢጀምርም፣ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ምክንያቱ በውል ባልተወቀ ሁኔታ ስርጭቱ ተቋርጧል። እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን የስርጭቱ መቋረጥ ምክንያቱ እንዲገለጽላቸው  ለሚያቀርቡት ጥያቄ አስተዳደሩ አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቓል። የኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት የኢሳትን ስርጭት በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ተጽእኖ እየፈጠረ ነው በማለት መገምገሙን መዘገባችን ይታወሳል። ኢሳት ...

Read More »

ሰመጉ ጥቃት እየደረሰበት መሆኑን አስታወቀ

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቀድሞው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ( ኢሰመጉ) የአሁኑ ሰመጉ ሚያዚያ 26 ቀን 2007 ዓም ባወጣው መግለጫ በአዋሳና አዲስ አበባ በሚገኙ የድርጅቱ ፅህፈት ቤቶች ላይ ጉዳት እንደደረሰበት አስታውቋል። መንግስት በተለያዩ ወቅቶች ላይ በድርጅቱ ላይ አፍራሽ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የጠቀሰው ሰመጉ፣ ሚያዚያ 24 ቀን 2004ዓም የሰመጉ የሃዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ በስራ ቀን ከጠዋቱ ...

Read More »

የአዲስ አበብ አስተዳደር ሰማያዊ ፓርቲ መስቀል አደባባይ ላይ የጠራውን ህዝባዊ ስብሰባ እንደማያስተናግድ ገለጸ

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 9/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ላይ ህዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ቢያቅድም ፣ ማካሄድ እንደማይችል ተነግሮታል። አስተዳደሩ ‹‹መስቀል አደባባይ ከፍተኛ የሆነ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበት ከመሆኑም በላይ በርካታ የተከማዋ ነዋሪ የሚተላለፍበት እና የከተማው ነዋሪ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥር ነው” በማለት ጥያቄውን አለመቀበሉን ገልጿል። መንግስት በቅርቡ በደቡብ አፍሪካና በአይ ኤ ኤስ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች በዲዛይንና ችግርና በሙስና ታክስ ከፋዩን ህዝብ ከፍተኛ ወጪ እያስወጡት ነው

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ ፕሮጀክቶች ብቻ በዲዛይንና በሙስና በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በመባከኑ፣ ግብር ከፋዩ ለአላስፈላጊ ወጪ ይዳረጋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለቤትነት በፌደራል የውሃ ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት አማካሪነት እና በፌደራል ውሃ ስራዎች ቁጥጥር ድርጅት ተቋራጭነት የግንባታ ስራው እየተካሄደው ባለው የርብ መስኖና ግድብ ፕሮጀክት ጥልቅ የዳሰሳና አዋጭነት ጥናት ...

Read More »

የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደቡብ ሱዳንና ኤርትራን ሊጎበኙ ነው

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሳሚ ሹክሪ ወደ ጁባ በማቅናት ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር የሚመክሩ ሲሆን፣ ወደ ኤርትራም በማቅናት በሽበርተኝነት፣ እና በአካባቢው ባሉ የጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ የግብጹ አል ሃራም ዘግቧል። ጉብኝቱ የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎች ከኢህአዴግ መንግስት ጋር አዲስ ግንኙነት መጀመራቸውን ባስታውቁ ማግስት እንዲሁም ሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ የአባይን ግድብ በተመለከተ አዲስ የትብብር ማእቀፍ በተፈራረሙ ማግስት ...

Read More »

በየመን የሚካሄደው ጦርነት እንደቀጠለ ነው

ሚያዝያ ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኤደንን ለመያዝ በሃውቲ ሚሊሺያዎችና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ሃዲ መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተካሄደ ሲሆን፣ 80 ሲቪሎች በጦርነቱ መሃል መገደላቸው ተዘግቧል። የሃውቲ ሚሊሺያዎች በቀድሞው ፕሬዚዳንት ታማኞችና በአረብ አገራት ጥምረት የአየር ሃይል ጥቃት የተነሳ እስካሁን የኤደንን ከተማ ለመያዝ አልቻሉም።የከተማ ነዋሪዎች በከፍተኛ የምግብና የውሃ እጥረት እየተሰቃዩ ነው።

Read More »

በመተማ በተቃውሞ ላይ የተሳተፉ 2 ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን 2007 ዓም የመተማ ከተማ ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ በሄዱ ቤት አፍራሾችና የወረዳው ባለስልጣናት ላይ ተቃውሞዋቸውን ለማሰማት ቢሞክሩም፣ የፌደራል ፖሊሶች በወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ 2 ነዋሪዎች በጥይት ተመትተው ሲገደሉ፣ 3 ደግሞ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ቆስለዋል። ከ50 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ባላስልጣናቱ ...

Read More »