በአማራ ክልል በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የሲሚንቶ እጥረቱ ተባብሶ መቀጠሉን ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

ሚያዝያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሁለት ወራት ጀምሮ በሲሚንቶ እጥረት ግንባታዎች እንዲቋረጡ መደረጉን በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችና በግንባታ ላይ የሚገኙ የህብረተሰቡ ክፍሎች ለዘጋቢያችን አስታውቀዋል፡፡ ችግሩ የህወሃቱ ንብረት በሆነው መሰቦ ስሚንቶና የሼክ አላሙዲን ንብረት በሆነው ደርባን ስሚንቶ መካከል ባለው ውዝግብ የተፈጠረ ነው ይላሉ ነጋዴዎች።  በዚህም የተነሳ ህብረተሰቡ ለአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ከ80 እስከ 100 ብር ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍል እየተደረገ ...

Read More »

የብሄራዊ ደህንነት መረጃ ሃላፊዎች ጥብቅ ፍተሻ እንዲካሄድ አዘዙ

ሰሞኑን በአዲስ አበባ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ነን ያሉ ሲቪል የለበሱ ግለሰቦች፣ ከደህንነት መስሪያ ቤት ነው የመጣነው በማለት በየክፍለከተማዎችና ወረዳዎች እየዞሩ፣ ለመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆነ ለግል ተቋማት ሃላፊዎች፣ ” ማንም ሰው ፣ የመንግስት ባለስልጣናም ሆነ መለዮ ለባሽ ወታደር፣ ፖሊስ ወይም ተስተናጋጅ ባለጉዳይ” ሽጉጥን ጨምሮ የትኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ ይዘው እንዳይገቡ፣ የመስሪያ ቤት ጠባቂዎች ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር እንዲያደርጉ” ትእዛዝ አስተላልፈዋል። እንዲህ ...

Read More »

አስመጪና ላኪዎች በዶላር እጥረት ተማረሩ

በሃገሪቱ የሚታየው ከፍተኛ የዶላር እጥረት አስመጪና ላኪዎችን ማማረሩን ዘጋቢያችን ምንጮቹች ዋቢ በማድረግ ከአዲስ አበባ የላከው ዜና ያመለክታል። የቡና ኤክስፖርት ከቆመ ወራት ተቆጥረዋል፣ በሃገሪቱ ያሉ ባንኮች ዶላር ሽያጭ አቁመዋል የሚለው ዘጋቢያችን፣ ከዲያስፖራው የሚገኘውን የውጭ ዶላር ገቢ ለማሳደግ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አዘጋጅቷል ብለአል። በአስመጪና ላኪ ስራ ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎች ዶላር ማገኘት ያልቻሉበት መንገድ አልተገለጸላቸውም። ይሁን እንጅ የቡና ዋጋ መውደቅ፣ የቆዳና ሌጦ ዋጋ ...

Read More »

የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት የውሳኔ ቀጠሮ ተራዘመ

በተራዘመ የፍርድ ሄደት የሚሰቃዩት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመፍትሄ አፈላላጊ የኮሚቴ አባላት ፣ የመጨረሻ ብይን ሚያዚያ 30 እንደሚሰጥ አስቀድሞ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ የብይኑ ቀን እንደገና ተራዝሟል። የመራዘሙ ዜና አስቀድሞ በኢሳትና በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የተዘገበ በመሆኑ፣ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አስገራሚ አላደረገውም። አገሪቱን የሚመራት የደህንነት መስሪያ ቤት ከምርጫው በፊት ምንም አይነት ውሳኔ እንዳይሰጥ ትእዛዝ አስተላልፎአል። በተለያዩ የማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን የተቃውሞ ጽሁፎችን በመጻፍ እንዲሁም ...

Read More »

የመጪው ምርጫ ተውኔት አስቂኝ ነው ሲል ዘጋቢያችን ገለጸ

በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር የኢህአዴግ ካድሬዎች እያደረጉት ያለውን የምርጫ ቅስቀሳና የካርድ እደላ የታዘበው ዘጋቢያችን የምርጫው ሂደት አስቂኝ ሆኗል ብሎአል። በከምሴ፣ ደብረብርሃን፣ ደብደረማርቆስና ሌሎችም ቦታዎች ካርድ ያለወጡ ሰዎች ኢህአዴግን እንደሚመርጡ ካርድ እየተሰጣቸው ነው። በአንድ ለአምስት፣ በአንድ ለአስር እንዲሁም በቡና ጠጡ መስተንግዶ ዜጎች በቡድን እንዲመርጡ እየተደራጁ ነው። የኢህአዴግ ካድሬዎች በዩኒቨርስቲዎች የቅስቀሳና የማደራጀት ስራ እየሰሩ ነው። ወሎ፣ ድብረብርሃን፣ ጅማና ሃዋሳ ዩኒቨርስቲዎች የኢህአዴግ መናሃሪ በመሆናቸው ...

Read More »

በአምቦ ተማሪዎች ታሰሩ

በምስራቅ አፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ሊግ ለኢሳት በላከው መግለጫ ፣ አምና በሚያዚያ ወር ከ79 በላይ የኦሮሞ ወጣቶች በአምቦና አካባቢዋ ከተገደሉ በሁዋላ፣ ባለፉት 10 ቀናት ደግሞ 50 የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መያዛቸውን ገልጿል፤፡ ከ20 በላይ ወጣቶች በድብደባ ጉዳት ደርሶባቸው በአምቦ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ። ድርጅቱ ባሰባሰበው መረጃ በእስር ላይ የሚገኙ 20 ተማሪዎችን ስም ይፋ አድርጓል። ወጣቶቹ የታሰሩት የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች በመሆናቸው ...

Read More »

በድሬዳዋ በጣለው ድንገተኛ ዝናብ የሰዎች ህይወት አለፈ

ሚያዚያ 27 ቀን 2007 ዓም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ገደማ በጣለው ድንገተኛ ዝናብ፣ እስካሁን ባለው መረጃ 9 ሰዎች በጎርፍ ተወስደዋል። ሟቾቹ ለገሃሪ እንደገበሬ በሚባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ናቸው። የ9 ሰዎች አስከሬን ተፈልጎ መገኘቱን ምንጮች ገልጸዋል። ድሬዳዋ ከዚህ ቀደም በደረሰ ጎርፍ በርካታ ነዋሪዎቿን ማጣቷ ይታወቃል።

Read More »

ሼክ አላሙዲን ጋዜጠኞችን ወቀሱ

በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሳውድ አረቢያዊ የሆኑት ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን በሸራተን አዲስ ተገኝተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ በስፍራው የተገኙትን የመንግስት ጋዜጠኞችና አንዳንድ የግል ሚዲያ ሃላፊዎችን ወቅሰዋል። ሼክ አላሙዲን በአሜሪካና በአውሮፓ የደሀ መሬት እየወሰዱ ነው እያሉ ስማችንን የሚያጠፉ ስራፈት ሚዲያዎች አሉ ያሉ ሲሆን፣ እናንተም የተባለው ትክክል ነው ወይስ አይደለም ብላችሁ፣ መርምራችሁ ለህዝቡ ማቅረብ ነበረባችሁ በማለት ለዘገባ የተላኩ ጋዜጠኞችን አብጠልጥለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን በሄድኩበት ...

Read More »

ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች የሚረገጡባት ዜጎች የሚሰደዱባት አስከፊ አገር ሆናለች ተባለ

በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በማካሄድ ላይ ባለው 56ኛው አፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና ህዝቦች መብቶች መደበኛ ጉባኤ ላይ ፣ አሪድ ላንድስ ኢንስቲቲዩት የተባለው ተቋም ባቀረበው ጽሁፍ ፣ ነጻነትን በማፈን የአለም ሻምፒዮን ከሆኑ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዳ መሆኗን ገልጿል። በኢትዮጵያ የሚባለውና የሚደረገው የተለያየ ነው የሚለው ድርጅቱ ፣ የአገሪቱ ህዝብ አማራጭ የመገናኛ ብዙሃንን እንዳያገኝ መታፈኑን ገልጿል። በአገሪቱ አስገድዶ መድፈር ወንጀል እየተስፋፋ መምጣቱን እንዲህ ...

Read More »

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የተያዙበት ሁኔታ ለህይወታቸው አስጊ ነው ተባለ

ሚያዝያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በከፍተኛ ህመም በመሰቃየት ላይ ሲሆኑ እስካሁን በዶክተሮች ለመጎብኘት አልቻሉም። አያያያዛቸው የከፋ መሆኑን በማስመልከት የእንግሊዝ መንግስት አስቸኳይ ደብዳቤ ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት መጻፉንም ምንጮቻችን ገልጸዋል። አቶ አንዳርጋቸው ያለፉትን ተከታታይ ወራት ጸሃይ የሚባል ነገር ሳያዩ ጨለማ ቤት ተዘግቶባቸው አሳልፈዋል; ከህመማቸው ጋር በተያያዘም ...

Read More »