በቅርቡ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የታሰሩት ወጣቶች በሃሰት እንዲመሰክሩ ጫና እየተደረገባቸው ነው

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና ደቡብ አፍሪካ በግፍ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ለመዘከርና ቁጣቸውን ለመግለጽ ገዢው ፓርቲ በጠራው ሰልፍ ላይ የተገኙ ወጣቶች መንግስትን ሰድባችሁዋል በሚል ታፍሰው ከታሰሩ በሁዋላ፣ “ተቃውሞውን ያስነሱት በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ናቸው” ብላችሁ ካልመሰከራችሁ አትለቀቁም መባላቸውን የእስረኞች ቤተሰቦች ገልጸዋል። ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ቤተሰቦች ለኢሳት እንደተናገሩት፣ ወጣቶች ማታ ማታ በደህንነት ሃይሎች እየተጠሩ በታሰሩ ...

Read More »

74ኛው የድል በአል ተከበረ

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያን ወራሪውን የጣሊያን ጦር ድል ያደረጉበት 74 ኛ አመት በአዲስ አበባ ጀግኖች አባት አርበኞች በተገኙበት ተከብሯል። በአድዋ ጦርነት ወቅት ሽንፈትን የተከናነበው ጣሊያን፣  ከ40 አመት በሁዋላ ራሱን በዘመናዊ መሳሪያ፣ በገንዘብና በሰው ሀይል አደራጅቶ ኢትዮጵያን ቢወርም፣ አባት አርበኞች ለ5 አመታት በዱር በገደሉ ባደረጉት ተጋድሎ፣ የፋሽስት ሙሶሎኒን ጦር ድል በማድረግ የአገራቸውን ነጻነት አስመልሰዋል። ኢትዮጵያ ...

Read More »

ባለሃብቶች መስራት አልቻንልም አሉ

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ” የኢንዱስትሪውን  ልማት በተሳለጠ መንገድ ይዘን በመጓዝ የአምስት አመቱን ዕቅድ ለማጠናቀቅ  በስኬት ጎዳና ላይ ነኝ ” በሚል  የገዢው መንግስት ቢናገርም፤ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶች በርካታ ችግር እየገጠማቸው መሆኑን ተናገሩ፡፡ ሰሞኑን በተካሄደው የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት  ከከፍተኛ ባለሃብቶች ጋር ባደረጉት የውይይት መድረክ ላይ ፣ ባለሃብቶች  እንደገለጹት በባለስልጣናት ላይ የሚታየው የፍርሃት መንፈስ ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን በአንድነት እንዲነሱ ጥሪ ቀረበ

ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጀርመን የኢትዮጵያውያን የውይይትና የትብብር መድረክ ሜይ 2፣ 2015 ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የተገኙት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶና ታዋቂው ጸሃፊ እና ፖለቲካ ተንታኝ አቶ የሱፍ ያሲን፣ አገራችን ከገባችበት ችግር መላቀቅ የምትችለው  በአንድነት በመነሳት መሆኑን ተናግረዋል። አቶ የሱፍ ገዢው ፓርቲ ባመጣው የፌደራል ስርአት ሳንጣላ ተራርቀናል ያሉ ሲሆን፣ ልዩነታችን ለጥንካሬያችን መሰረት ...

Read More »

የኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች በድርጅታቸው ግራ ተጋብተዋል

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያንን ለመዘከር የወጣው ህዝብ ተቃውሞውን ወደ ኢህአዴግ መንግስት ካዞረ በሁዋላ፣ ገዢው ፓርቲ ተቃውሞውን ያስነሳው በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገለው ሰማያዊ ፓርቲ ነው በማለት የከፈተው ሰፊና አሰልቺ ፕሮፖጋንዳ የህዝቡን አመለካከት ሊቀይር አለመቻሉ ከፍተኛ ካድሬዎችን ስጋት ላይ ጥሎአቸዋል፡፡ በመስቀል አደባባይ የታየውን ህዝባዊ ቁጣ  ሰማያዊ ፓርቲ የቀሰቀሰው የመንደር ሁከት ለማስመሰል ...

Read More »

ፌደራል ፖሊስ በማእከላዊ እስር ቤት ታስረው የሚገኙት እስረኞች እርስ በርስ እንዲወነጃጀሉ እያደረገ ነው

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ባለፈው ታህሳስ ወር አርበኞች ግንቦት7ትን ሊቀላቀሉ ሲሄዱ መንገድ ላይ ተይዘዋል ባላቸው እሰረኞች ላይ ለደረጃ ምስክርነት አብረው ከታሰሩት መካከል እያሰለጠ ነው። አንዳንዶች ፖሊስ ራሱ ያዘጋጀውን ቃል በፍርድ ቤት ተገኝተው የሚሉ ከሆነ ከእስር እንደሚፈቱ ፣  ለመመስከር ፈቃደኛ ያልሆኑት ደግሞ እድሜ ልካቸውን በእስር ላይ እንደሚቆዩ እንደተነገራቸው ምንጮች ገልጸዋል። ሰለሞን አሞኘ የተባለው ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ ህዝቡ በቡድን ድምጽ እንዲሰጥ እያዘጋጀ ነው

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በግንቦት አጋማሽ ሊደረግ በታሰበው  ምርጫ ላይ  ገዢው ፓርቲ በቡድን ድምጽ የሚሰጡ ዜጎችን በማደራጀት ላይ መሆኑን በተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ መረጃዎች አመልክተዋል። ዜጎች ድምጽ እንዲሰጡ የሚደረገው ገዢው ፓርቲ አንድ ለአምስት እያለ በሚጠራው የአፈና ስርአት ውስጥ ሆነው ነው። የኢህአዴግ ካድሬዎች በድምጽ መስጫው ቀን በአንድ ለአምስት የተደራጁትን ሰዎች በአንድ ላይ ወደ ምርጫ ጣቢያ እየመሩ በመውሰድ ...

Read More »

ጠ/ሚኒስትር ናታኒያሁ ደማስ ፈቃደን አነጋገሩ

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተእስራኤላውያን ዘረኝነትን በመቃወም ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ እሁድ ተጠናክሮ ከቀጠለ በሁዋላ፣ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታኒያሁ ፣ የተቃውሞው መነሻ የሆነውን ወታደር ደማስ ፈቃደን አነጋግረውታል። ወታደር ደማስ በእስራኤል ፖሊሶች መደብደቡ በአገሪቱ የሚኖሩትን በተእስረኤላውያንን በእጅጉ አበሳጭቶ ለተቃውሞ አደባባይ አስወጥቶአቸዋል። ቤተእስረኤላውያኑ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነት እጥብቀው የተቃወሙ ሲሆን፣ ቁጣቸውንም የተለያዩ ጠርሙሶችና ...

Read More »

በጤናተቋማትአገልግሎትአለመሟላትየእናቶችሞትበእጥፍጨምሯል፡፡

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀገሪቱካሉት 879 በላይ  የጤናተቋማትውስጥመሰረተልማቶችየተሟሉላቸው 105 ብቻሲሆኑ፣ ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር በተያያዘ በየቀኑ 68 ሴቶች በየሰዓቱ ደግሞ 3 እናቶች ህይወታቸው እንደሚያልፍ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የአብዛኛው እናቶች ሞት የሚከሰተው በደም መፍሰስ፣ በተራዘመ ምጥና በከፍተኛ የደም ግፊት ነው። በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ መቶ ሺ እናቶች መካከል 420ዎቹ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጣሉ። በጤና ጥበቃ ሚኒስትር የእናቶችና ...

Read More »

በሱዳን በኩል ወደ ውጭ የሚወጡ ዜጎች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ ጨምሯል

ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በዚህ ሳምንት ብቻ 9 ሺ 405 ወጣቶች ድንበር አቋርጠው ወደ ሱዳን ሲጓዙ በድንበር ጠባቂ ፖሊሶች ተይዘዋል። ፋሲል የኔአለም ዝርዝሩን ያቀርበዋልበሰሜን ጎንደር ዞን ቆላማ ወረዳዎች በተደረጉ 2 የዳሰሳ ጥናቶች በቀን  ከ150-250  በዓመት ደግሞ ከ 54,000 እስከ 90,00 ኢትዮጵያውያን   ወደ  ሱዳን ይሻገራሉ፡፡ ጥናቱ በመላው አማራ ወይም በመላው ...

Read More »